>

ከአብን የተላለፈ መግለጫ

ከአብን የተላለፈ መግለጫ

ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ከተሞች በሚካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የሚያዙ መፈክሮች ከዚህ በታች የተገለፁት ሲሆኑ ከእነዚህ መፈክሮች ውጭ በሰልፉ ላይ ማስተጋባት ፈፀሞ የተከለከለና ድርጅቱን የማይወክሉ መሆናቸውን እንገልፃለን፡፡
1) የአማራ ህዝብ ሰቆቃ ይብቃ !
2) ለሀገር ሰላም ሲባል ያሳየነው ትዕግስት እንደ ፍርሐት መቆጠር የለበትም !
3) ዘር ማጥፋት በይርጋ የማይታገድ አለም አቀፍ ወንጀል ነው !
4) ለሀገር ጥቅም እንጅ ለልዩ ጥቅም አንታገልም !
5) የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ፍላጎትም አቅምም የሌለው መንግስት ስልጣኑን በአስቸኳይ ያስረክብ !
6) ለአማራ መሳደድ መነሻ የሆነው ህገ መንግስት በአስቸኳይ ይሻሻል !
7) አንበጣ ሲደመር እህል ያጠፋል መሪ ሲታወር ሀገር ያፈርሳል !
8)ብልፅግናው ቀርቶ ህልውናችን በተጠበቀ !
9) የአማራ ደም ለቁማርተኞች የስልጣን ማቆያ ሲባል በከንቱ አይፈስም !
10) ወንጀል በስሙ ይጠራ ! የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ግጭት በሚል ማድበስበስ ይቁም !
11) ከአማራ ህዝብ ጎን መቆም ሰብዓዊነት እንጅ ዘረኝነት አይደለም !
12) የአማራን ህዝብ ሰቆቃ ለማውገዝ ሰው መሆን በቂ ነው !
13 ) ኢትዮጲያ የሁላችንም መሆን ካልቻለች የማናችንም የመሆን እድል አይኖራትም !
14) ስልጣን የህዝብ ማገልገያ መሳሪያ እንጅ መገልገያ መሳሪያ አይደለም !
15) እያንዳንዱ የክልል መንግስት በውስጡ ለሚኖሩ ዜጎች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት !
16) የአማራ ብልፅግና ፦ ስልጣን ላይ ለመቆየት አማራውን በማስያዣነት ያቀረበ ድርጅት ነው!
በሌላ በኩል የሰልፉን ሂደት በተመለከተ፦
**************************************
❗️የሰልፉ መነሻ እና መድረሻ ቦታዎችን እንደየአካባቢው ሁኔታ መለየት እና በቅስቀሳ ወቅት ለህዝቡ ማሳወቅ!
❗️ከተዘጋጁት መፈክሮች ውጭ ሌሎች መፈክሮች እንዳይያዙ መከላከል እና ይዞ ከተገኘም የሰልፉ አስተባባሪዎች እንዲረከቡ!
❗️የሰልፉን ሰላማዊነት ለማስጠበቅ የሚሰሩ እና የሚከታተሉ ወጣቶችን መልምሎ ስምሪት መስጠት!
❗️ዱላን ጨምሮ ምንም አይነት መሳሪያ የሰልፉ ተሳታፊዎች እንዳይዙ አስተባባሪዎች ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ!
❗️የሰልፉን ደህንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በጥምረትና በመግባባት መስራት!
❗️በሰልፉ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶችም ሆነ አደረጃጀቶች መሳተፍ እንደሚችሉ ነገር ግን ተጨማሪ ጉዳዮችን ላይ ከአስተባባሪዎች ትዕዛዝ መውጣት እንደሌለባቸው!
አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ!
—–
በተያያዘ መረጃ:-
አማሮች ከሰልፍ አልፈው 
  ሰይፍ ቢያነሱ አይፈረድባቸውም…!!!”
 አቶ ኦባንግ ሜቶ
“ባለፉት ሁለት ዓመታት ዘራቸው እየተቆጠረ ብቻ በመቶወች የሚቆጠሩት ታርደዋል፣ በሺወች የሚቆጠሩት ተፈናቅለዋል፣ የብዙወች ንብረት ወድሟል። መንግስትም ዘላቂ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ነገሮችን እያድበሰበሰ እያለፈ ለብዙወች አሰቃቂ ሞት ምክንያት ሆኗል!!”
ጥቁሩ ፈርጥ
Filed in: Amharic