>

ህገመንግስታችን የእብዶች ሰነድ ነው ስንል በምክንያት ነው!?!!  (ሙክታሮቪች) 

ህገመንግስታችን የእብዶች ሰነድ ነው ስንል በምክንያት ነው!?!! 

(ሙክታሮቪች) 

የኛ ህገመንግስት በተባበሩት የመንግስታት ህብረት መታገድ አለበት። እነ ክፍሌ ወዳጆ፣ ፋሲል ናሁምና እንድሪያስ ይህን የእብድ ሰነድ ማዘጋጀታቸው ያስደንቀኛል…!!!
 
ላስረዳ:—
በአለም ላይ 206 ገደማ ሀገሮች አሉ። በአፍሪካ 55 ሀገራት አሉ። ይህ በጣም ብዙ ነው እየተባለ ይተቻል። ሰሜን አሜሪካን ካናዳን ስፋት አስቡት፣ ሁለት ሀገር ናቸው። የኛው የደንቆሮ ስራ ህገመንግስት በአንቀፅ 39 ከሰማንያ በላይ ብሄርብሄረሰቦችን የመገንጠል መብት በመስጠት በአፍሪካ ላይ 80 ሀገር ለመጨመር የሚፈልግ ከፈሳቸው የተጣሉ የመንደር ጨቡዴዎች የነደፉት ሰነድ እንጂ ሀገር ማለት ምን ማለት ነው ብለው በሚያስቡ ሰዎች የረቀቀ አይመስልም።
በእኛው ህገመንግስት መሰረት የአለም ሀገራት ቢደራጁ፣ ህንድ ሀገር ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ሀገራት ይወጡታል። አፍሪካ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ሀገራት በላይ ይወጣቸዋል።
የእኛው ህገመንግስት የዘባረቀው ፍፁም የማይቻለውን ነው።
ለብሄር ብሄረሰብና ህዝብ ትርጉም በወጉ ሳያስቀምጥ የመገንጠል መብት ይሰጣል። ማነው ብሄር? ማነው ብሄረሰብ? ማነው ህዝብ?
ማንም አያውቅም! የፈለገህን መርጠህ መውሰድ ነው። ከወሰድክ በኋላ መገንጠል ትችላለህ!
የህገመንግስቱ መግቢያ ስለአብሮነት ይሰብካል። አንድ ነበርን እጣፈንተችን አንድ ነው እያለ የአብሮነት ጋብቻን እያበሰረ 39 ላይ ሲደርስ ልንፋታም እንችላለን ይላል። ሰው እንዴት በጋብቻው ቀን የፍቺ ውልን አብሮ ይፈርማል። ለመፋታት እያቀዱ መጋባት ግራመጋባት!
ኢማጂን አለ ዶክሌ ሃሃ
መብቱ ለሁሉም ተሰጠ እንበል። መቼም ቼክ ተሰጥቶህ አትመንዝር፣ ስጋ ተሰጥቶህ ቢላዋውን አታንሳ አትባልም። የተፈቀደ ነገር አይከለከልምና 80 ሀገሮች ሊፈጠሩ ነው በምስራቅ አፍሪካ 😀
በአፍሪካ ካሉት 55 ሀገሮች ላይ 80 ሲጨመሩ መቶ ሰላሳ አምስት ሀገሮች!
በተባበሩት መንግስታት መቼም መመዝገባቸው አይቀርም። ተመዝግበው አመታዊ ጉባኤ ሲደረግ አስቡት።
80 ሀገሮች ንግግር ሲያደርጉ፣ 55 አፍሪካ ሀገሮች ይጠብቃሉ። 150 ከአፍሪካ ውጭ ያሉት ተራቸው እስኪደርስ ያለውን መከራ።
ደራሼያ፣ ስልጤኒያ፣ ሀረሪያ፣ ሀዲያ ሪፐብሊክ፣ አርጎቢያ፣ ጌዶኦ ዴሞክሲያዊ ሪፐብሊክ
የኛዎቹ በቀድሞ ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር ውስጥ የነበሩ ሀገራት ርዕሰብሄራቸው ንግግር እንዲያደርጉ ተራ ሲደለደል ሲረባበሹ አለም በሳቅ ሊያልቅ ነው።
ዳውሮ አንደኛ ይናገር ሲባል በቁጠር እኔ ስለምበልጥ ይህ ለሀራችን ንቀት ነው ይላል ኦሮሞ። አማራ ልቅደም በአልፋቤት ይሁን ይላል። ስልጤና የም መጨረሻማ አንሆንም ሲሉ አርጎባ ከአማራ ቀጥሎ መናገር ስለሚፈልግ የአማራን ሀሳብ ሲደግፍ ቅማንትና ትግራይ ይቃወማሉ። ኝአንጋቶምና ሸካ መናገር እንጂ ቅደም ተከተሉ አያስፈልግም ሲሉ እነ ደራሼና ቀቤና በዕጣ ይሁን ይላሉ።
ይህ ክርክር አንድ ሳምንት በመውሰዱ የተባበሩት መንግስታት የመሪዎች ጉባኤ ሳይጀመር ይቀራል። አለም ይህን ውዝግብ እንደኮሜዲ ሲኒማ ፈንድሻና ፔፒሲ ይዞ ይደክማል 😀
ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ሀገራት የስማቸውን ታፔላና ባንዲራ ይዘው ሲወጣ አዲሶቹ 80 ሀገራት የሰልፉን እርዝመት በዕጥፍ ይጨምሩታል፣ ውድድሩ ወር የነበረው ወደ ሶስት ወር ያድጋል።
ፊፋም፣ ካፍም ይቸገራል 😀
የስፖርት ፌዴሬሽኖች “ውይይ ውይይ አንችልም” ብለው 80ዎቹ እንደገና በኮንፌዴሬሽን ተዋህደው እርስበርስ ማጣርያ አድርገው አንድ አሸናፊ ይላኩ የሚል ምክረ ሀሳብ ይመጣል ሃሃሃ ማን ከማን ያንሳል እየተባለ ይጨቃጨቃሉ።
ከቴፒ አከባቢ ሸካ ሀገር ተነስተው አዲሳባ ለመምጣት የሃያ ሀገራት ቪዛ ያስፈልጋል።
የሀገራቱ ብዛትና መጠጋጋት ለቱሪዝም እንደስትሪ አስቸጋሪ ይሆናል
ቱሪስቶች ማፕ ይዘው ይወዛገባሉ፣ ይቸገራሉ
አስጎብኚዎች ሀገር ማስጎብኝት ይቸግራቸዋል።
“This country is Gamo, Gamo is known ” እያላችሁ እንግዶቹን የያዘው መኪና ዳውሮ ገብቷል ሃሃሃ
ሌላው በሰማንያ አዲሶቹ ሀገሮች መካከል አስራምናምን የድንበር ጦርነት ተነስቶ ሰላም አስከባሪ ይጠፋል።
አለም ተወዛግቦ “ቆይ ይህ ሁሉ ሀገር እንዴት መጣ?” ሲባል የፌዴራሊስት ሀይል ነን ባዮች የሚያቆለጳጵሱት የእብዶች ሰነድ መሆኑ ይደረስበታል። ከዚያ ሰው ልክ እንደ 13 ቁጥር 39 ቁጥርን የመጥፎ እድል ምልክት ያደርጋል ሃሃ
ደንቆሮ ሰነድ!
Filed in: Amharic