>

የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ  እና የፍትህ ተቋሙ ጉድ...‼ (አሻራ ሚዲያ)

የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ  እና የፍትህ ተቋሙ ጉድ…‼

አሻራ ሚዲያ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … 
ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ (ኦሮሞ)
 
➙የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት … አቶ ሰሎሞን አረዳ (ኦሮሞ)
 
➙የፌዴራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … አቶ ብርሃነ መስቀል ዋጋሪ (ኦሮሞ)
 
➙የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት …
 አቶ ፎአድ ኪያር (ትግሬ)
 
➙የፌዴራል ዳኞች የተወከለ … 
አቶ ተኽሊት ይመስል (ትግሬ)
 
➙የዳኞተ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ …
 አቶ ዘሪሁን ጌታሁን (ኦሮሞ)
በዚህ የስልጣን ቅርምት መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በተረኞቹ የተወረረ ነው።
°°°
የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ራሱን የቻለ የመንግስታዊ ተቋም ሲሆን ኃላፊነቱም የዳኞች ነፃነት እና ተጠያቂነት የተባሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ የነፃ ዳኝነት ማንበሪያ ምሶሶዎች ሳይዛነፉ ለማስኬድ የተቋቀመ ራሱን የቻለ የፍርድ ቤቱ አስተዳደር አካል ነው፡፡ ይህ ጉባኤ የዳኞችን ሹመት፣ ዝውውር፣ ደመወዝ (ጥቅማ ጥቅም) እና የዲሲፕሊን ጉዳይ የመወሠን ስልጣን አለው፡፡ ልክ ለአስፈፃሚው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ሁሉ፤ለፍርድ ቤቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ብለን በቀላሉ ልናመሳስለው እንችላለን፡፡
°°°
በአውሮፖ ህብረት የዳኞች ጉባኤ ትስስር ኮሚቴ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ለፍርድ ቤቶች reform የማይተካ ሚና እንዳለው፤ ፍርድ ቤቶች በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መመራት እንዳለባችው ያስገነዝባል፡በኢትዮጵያም ነፃ ዳኝነት ለማቋቋም አስፈላጊነቱ ታምኖበት በህገመንግስቱ ውስጥ በአንቀጽ 78 እና 79 ላይ እውቅና ተሠጥቶታል፡፡
°°°
ህገመንግስቱ ጥቅል ህግ በመሆኑም ራሱን ችሎ አዋጅ ቁጥር 684/2002 መሠረት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዝርዝር ተቋቁሟል፡፡ በአዋጁ መግቢያ ላይም “ነፃ የዳኝነት አካል ነፃነቱ የሚረጋገጠው ተቀማዊ እና ዳኝነታዊ ነፃነቱን መጠበቅ ሲቻል በመሆኑ፤ ይህንንም ለማድረግ ፍርድ ቤቶች ከማናቸውም አካል ተጽዕኖ ነፃ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር መቻል ያለባቸው በመሆኑ” ሳቢያ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተቋቀመ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
°°°
የጉባኤው አባላት ስብጥር እነማን መሆን እንዳለባቸው በአዋጁ አንቀጽ 5 ላይ ሠፍሯል፡፡ የጉባኤው ሰብሳቢም የጠ/ፍ/ቤቱ ፕሬዜዳንቷ እንዲሆኑ ይደነግጋል፡፡ ከሌሎች የተወካዮች ምክር ቤት፣ አስፈፃሚው አካል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመጡት ተወካዮች ውጭ ከፍርድ ቤቱ የሚወከሉት በጉባኤው የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንቶች፣ የከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ብሎም ከዳኞች የተወከሉ አንድ ዳኛ እንደሆነ ሠፍሯል፡፡
°°°
ከላይ የተመለከተው የህጉ ሃሳብ ሲሆን በዚህ በህግ እውቅና ተሰጦት ፍርድ ቤቱን በሚመራው ትልቅ ተቋም ላይ “regional and cultural inclusiveness” መኖር እንዳለበት በተለይም እንደኛ ሃገር power sharing arrangement በሚከተሉ አገራት ህገመንግስት ከዲሞክራሲያዊነት መርሆች መካከል አካታችነት እና አሳታፊነት (inclusiveness and participatory) ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው በብዙ የፖለቲካም ሆነ የህግ ሊህቃን ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡
°°°
ማንኛውም የዳኛ አመራር (ዳኛ) ህዝብን ማገልገል ያለበት ያለአድሎ ሁሉንም ህዝብ በእኩልነት መሆኑ የሚስተባበል አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ህዝብ ለተቋማቱ እኩል ተሳትፎ እንደማንኛውም ብሄር ሊኖረው ይገባል፡፡ በተቋሙ ያለው ተሳትፎ ተመጣጣኝነት እንደተባለው ብቻውን ራሱን ችሎ መሠረታዊ የዲሞክራሲ መርህ ሆኖ ስለሚቆም ማለት ነው፡፡ ብልጽግና ግን በተረኝነትና በሰልቃጭነት የሚጓዝ ይሉኝታ ቢስ ፓርቲ ነው። ከዚህ በላይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም።
ለተጨማሪ መረጃዎች
Filed in: Amharic