>

የአቢይ አህመድ ሌጋሲዎች (ይነጋል በላቸው)

የአቢይ አህመድ ሌጋሲዎች

ይነጋል በላቸው


መለስ ከሞተ በኋላ “የመለስ ሌጋሲዎች” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ ለድረገፆች ልኬ ለንባብ መብቃቱን አስታውሳለሁ፡፡ በነካ እጄ በቁሙ ስለሞተው አቢይ አህመድም ሌጋሲዎች ጥቂት ልበል፤ አንድ ሰው ባይሞትም ሌጌሲው ቢጻፍ ጉዳት ያለው አይመስለኝም፡፡ ከመግቢያው ጀምሮ ስለመረረው የአነጋገር ሥልቴ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ ትኁታን ወገኖቼን ከወዲሁ ይቅርታ መጠየቅ እወዳለሁ፡፡ የኔ የአነጋገር ነውረኛነት ግን ከዚህ ባለጌና ኢትዮጵያን በቁም እየቀበረ ካለ ሰውዬ ሰይጣናዊ ተግባር አይበልጥም፡፡

  1. ወደር የለሽ ውሸታምነት – ዓለማችን ከዚህ በፊትም ሆነ በኋላ አሁንን ጨምሮ እንደአቢይ አህመድ ያለ ውሸታም ቀዳዳ አይታ አታውቅም፡፡ ውሸቶቹን መዘርዘር አይጠበቅብኝም፡፡ ይህ አንዱ ሌጌሲው ነው፡፡ ሥልጣኑን ለማራዘም የማይዋሸው የለም፡፡
  2. ወደር የለሽ ማስመሰል – ዓለማችን መቼም ቢሆን እንደ አቢይ አህመድ ያለ አስመሳይ አይታ  አታውቅም፡፡ በአንድ ጊዜ እባብም ዕርግብም መሆን የሚሞክር ግን ሊሣካለት የማይችል ዋና አስመሳይ ነው፡፡ የተለዬ ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ሳይኖርበት አይቀርም፡፡ 
  3. የጨለማው ገዢ ወኪል – በዓለማችን እጅግ ብዙ የዲያብሎስ ወኪሎች አሉ፡፡ በተለይ በአፍሪካ ግን እንደአቢ ያለ ታማኝ ወኪል የለም፡፡ ለምሣሌ ኮሮናን ከማስፋፋት አኳያ በአፍሪካ ከሞሮኮ ቀጥላ ኢትዮጵያ ሁለተኛ እንድትሆን ከሴቴኒስቱ ጃክማ ጋር በመተባበር አቢይ ያደረገው ጥረት ለሁለተኛ የሁከት የኖቤል ሽልማት ሊያበቃው ይችላል (የጃክማ ዕርዳታ ባፍንጫየ ይውጣ ያለችውና 400 ያልሞላ የቫይረሱ ተጠቂ ያላት ኤርትራ አንድም ሰው በኮሮና እንዳልሞተ መረጃዎች ይጠቁማሉ – እንደሰሜን ኮርያ በዘዴ እያስወገዱ ካልሆነ በስተቀር)፡፡ እዚህ ላይ ኖቤል የጨለማው ገዢ ኃይላት ለወዳጆቻቸው ማበረታቻ የሚሰጡት ውድ ሽልማት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ቻይና በኮሮና በዓለም አንደኛ እያለች ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ የምትመደብ ነበረች፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ተገለባበጠና ኢትዮጵያ 49ኛ ሆናለች – ቻይና ደግሞ ከ1ኛ ወደ 53ኛ፡፡ በዚህም ውጤት ምሥጢራውያኑ ድርጅቶችና አቢይ ራሱ ሳይበሳጩ አይቀሩም፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን በቫይረሱ የተለከፈው የሕዝብ ቁጥር 90 ሽህ አካባቢ ቢሆንም የሞቱት ቁጥር ግን ምዕራባውያንን ሊያረካ የሚችል ብዛት የለውም፡፡ ስለዚህ ይበሳጫሉ፡፡ አቢይ እነእንቶኔ ከቬርሙዳው ቢሯቸው ደውለው ኢትዮጵያን በአንዴ የሚያጠፋ አንድ ትልቅ ድማሚት ልንቀብር አስበናል ቢሉት ምን ልርዳችሁ እንደሚላቸው ጥርጥር የለኝም፡፡ የሰይን ቁራጭ ብቻ ሳይን ራሱም ሰይጣን ነው፡፡ ድርጊቶቹ ሙሉ በሙሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩት ይህ ሰው ኢትዮጵያን ለማጥፋት መምጣቱን ብቻ ነው፡፡ ምናልባት “መንገድ ጠራጊው” ሳይሆን አይቀርም፤ መንገድ ጠራጊ ደግሞ ያገኘውን ነው የሚጨረግደው፡፡ የተላከበት ነዋ! (በነገራችን ላይ የአዲሱ መንግሥት አራማጆች ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ በተለይምና በዋናነት የፈረደበትን የሦስተኛውን ዓለም ሀገር ሕዝብ ጨምሮ በተለያዬ ዘዴ መፍጀትን በዕቅድ እየተገበሩ ናቸው፡፡)
  4. ፀረ- አማራነት – አቢይ አህመድ ሙልጭ ያለ ፀረ አማራ ነው፡፡ አማራን ፈጅቶ ካልጨረሰ የኅሊናም ሆነ የአካል ዕረፍት አያገኝም፡፡ 
  5. አላጋጭነት – አቢይ አህመድን የመሰለ በሕዝብ አላጋጭ ካለ፣ በሀገርና በወገን ስቃይ የሚደሰት ካለ እወራረዳለሁ፡፡ ፓርላማ ውስጥ በተጎለቱ አሻንጉሊቶቹ ፊት ከመለስ በበለጠ ብልግናና ነውረኝነት ደረቱን እንደፉኝት እየነፋፋ ሲያላግጥ ለሚሰማ ይህ ሰው ከየት እንደበቀለና እንዴትም እንዳደገ ለማወቅ መጓጓቱ አይቀርም፡፡ “አንበጦች የመደመርን ፍልስፍና ተግባራዊ ያደርጋሉ” ብሎ በመናገር ሣቅን ለማጫር መከጀል አንድም ዕብደት አሊያም በአንበጣ የተወረረው ሕዝብ ላይ በማሾፍ እርካታን ለማግኘት መሞከር ነው፡፡ አንድ ኪሎ ቡና ብር 200፣ አንድ ኩንታል ጤፍ ብር 5000 ገብቶ በኑሮ ውድነት እያበድን ሳለን እርሱ ግን “የኑሮ ውድነቱ እስከዚህም ነው፤ ለክፉ አይሰጥም…” የሚል ቃና ያለው ቀልድ መናገሩ በሕዝብ ምን ያህል እንደሚያሾፍ አመላካች ነው፡፡
  6. ዘረኛነት – አቢይ ከመጣ በኋላ ኢትዮጵያዊነት ወደ ኦሮሞነት በብርሃን ፍጥነት በመለወጥ ላይ ነው፡፡ 86ቱ ብሔር ብሔረሰብ ወደኦሮሞነት ካልተለወጠና የገዳ ሥርዓትን ካልተቀበለ  መኖር እንደማይችል በግልጽ እየተነገረና በተግባርም እየታዬ ነው፡፡
  7. ፀረ-ኦርቶዶክስነት – አቢይ ፀረ-ኦርቶዶክስ ነው፡፡ የምታውቁት ነው፡፡ ሥልጣኑን ሁሉ ለጴንጤዎች እያከፋፈለ ነው፡፡ የሀገርን ሀብት ሁሉ ለኦሮሞዎች ብቻ እያከፋፈለ ነው፤ ሌሎችን የበይ ተመልካችና ስደተኛ እያደረገ ነው፡፡ እያሰረና እየገደለም ነው፡፡ ይመቸው!
  8. ድህነትን አስፋፊነት – ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ ቤት ኪራይም ሆነ ቤት መሥራት ለሚሊዮኖች ህልም በመሆኑ ጎዳና ተዳዳሪነት ትልቁ የአቢይ አህመድ መታወቂያ ነው፡፡ በየአደባባዩና በየመብራቱ ስታልፍ የምታየው ጎዳና ተዳዳሪ ቢሰበሰብ አንድ ትልቅ ከተማ ይወጣዋል፡፡ ይህን እያዬ ይህ ወፈፌ መሪ ምን ሊሰማው እንደሚችል አላውቅም፤ ለነገሩ አስመሳይና ውሸታም ሰው እውነታን በመገልበጥ ስለሆነ የሚደሰተው አቢይ በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የሚሰማው ነገር አይኖርም፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ለቅጣት የመጣ ሰው ርሀብ ጥጋብ ነው፤ ጦርነት ሰላም ነው፤ ሥርዓት አልበኝነት ሥርዓታዊነት ነው፤ ጥላቻ ፍቅር ነው፡፡ ዐይኑ አንድን ነገር ገልብጦ ነው የሚያነበው፡፡ ሲዋሽ ደግሞ ለከት የለውም፡፡ ይህን ሰው ለኢትዮጵያ መስጠት ፈጣሪን መክሰስ ስለማይቻል እንጅ …(ሆ! ይህስ ይቅርብኝ!)   
  9. አስማጭነት – አቢይ እንደ ወንድሞቹ እንደነእስራኤል ዳንሣና እዩ ጩፋ ከናይጄሪያ ይሁን ከህንድ ባስመጣው ሰይጣናዊ መተት በርካታ ሀገር ወዳድ ዜጎችን ለነገ እንዳይጠቅሙ አድርጎ እያበከታቸው ነው፡፡ እነምሕረት ደበበ፣ እነ ዳንኤል ክብረት፣ እነ ሲሳይ አጌና፣ እነግዛው ለገሠ፣ ታበ፣ አገ፣ መመ፣ ፋየ፣ብነ፣ አጽ፣ ስንቶችን ቆጥሬ … እነዚህ ሁሉ የት እንደገቡ አይታወቅም፡፡ በስማም እንደተባለባቸው ሰይጣን ፀጥ ረጭ ብለዋል፤ በራሳቸው ወይም በሰውው አፍረው የተሸሸጉ ይመስላል፡፡ ሰይጣን መጥፎ ጠላት ነው – የተመረጡትን ሁሉ ያሳስታል፡፡ ስለዚህ ቆመናል የምትሉ ሁሉ ተጠንቀቁ፡፡ ሰው ካልሞተ ማመስገን የማንችልበት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን፡፡ ስንትና ስንት የመላእክት ሠራዊት፣ ሊቀ ሣጥናኤልን አምነው ገደል ገብተዋል፡፡ አሁን ዓለምን እየገዛ ያለው አመንክም አላመንክም ሰይጣን ነው፤ እነአቢይ ደግሞ የሰይጣን አማኞችና ተላላኪዎች ናቸው፡፡ አንዱና ዋናው ምልክትም በወያኔ ጊዜ እንኳን ሊደረግ ያልተሞከረ ነገር፣ ዛሬ የድንቅ ኢትዮጵያውያንን የፌስቡክና የዩቲዩብ ገፆች ከዕይታ ውጪ ማድረግ እየቻሉ ነው፡፡ የሰይጣን ታዛዥ የሆነ ሰው ሀገር ገምቢን ሃሳብ ማስወገድ ዋና ሥራው ነው – ይህ ለዜጎች ማሰብ እንዳልሆነ የምናውቀው የአባትና የልጅን ጋብቻ ጨምሮ የሰውና የእንስሳትን የትዳር ጥምረትና የመሳሰለው የብልግና ፊልም ሁሉ በነፃነት እንዲተላለፍ መፍቀዳቸውን ስናይ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምትል ገና ብዙ አሣር አለብህ! ግን አጥብቀህ ጸልይ – በቅርብ ያልፋል፡፡
  10. ምን ለውጥ ላመጣ እደክማለሁ ግን፡፡ በቃኝ፡፡ ይሁንና ወዮ ለዚህ ሰውዬ! መጨረሻው ከሂትለርና ከሙሶሊኒም የከፋ ነው፡፡ ንገሩት፡፡
Filed in: Amharic