>
5:13 pm - Sunday April 18, 2027

ኢትዮጵያን ከውድቀት ለማዳን ደረጀ መላኩ ( የሰብአዊ መብት ተሟጋች )

ኢትዮጵያን ከውድቀት ለማዳን

ደረጀ መላኩ ( የሰብአዊ መብት ተሟጋች )

Tilahungesses@gmail.com

  መንደርደሪያ                                                       መስከረም 2013

ሳንቀሰፍ ምክር ቢጤ በተለይም ለወጣቱ


እርግጥ ነው ወጣቱ ትውልድ አገር ተረካቢም ትኩስ ኃይልም ነው ።

አገርም የማዘመንና ኃላፊነቱንም የመወጣት ብቃትም ችሎታም ፈጥኖ የማዳበርና በሠላም አብሮ ለመኖርም መስራት የሚያስችል ሥልት መንደፍ የሚያስችል ከስሜት ከሚፈፅማቸውም ውጪ የተደራጀ ክፍት አዕምሮም አለው ።

ነገር ግን ይህ ወጣት ትውልድ በአንዳንድ ሥፍራዎች ተመርቶም ይሁን ፈፅም ተብሎ በምግባሩ እየሰራ ያለውና የወረሰው ልዩ ባሕርይ ቢኖር የገዢና የጨቋኞች አስተዳዳሪዎቹን ( አምባ ገነንነትን፣ የበላይነትን፣ ሰውን መብት መጋፋትን ፣ ተራጋጭነትን፣ ዕብሪትን፣ ጥጋበኝነትን ፣ ማንአለብኝነትን ፣ ፍርደ ገምድልነትን በኃላፊነት አለመጠየቅን…. ) መሆኑን የሚፈፅማቸው ምግባሮቹ ያረጋግጣሉ ።

ከፋሺስቶችና ከሰንካላ ካድሬዎቹ አገዛዛቸው ጋር የገጠመውን ግብግብና የፈፀሟቸውንም መልካም ተጋድሎውንም አንረሳም ። ያ ብቻ በቂ አይደለም ። 

ከሁሉም በላይ ከፊቱ የተደቀነውን በተስፋ የመኖር ሕልም ሳያጨልም መቀጠሉ ትልቅ ዋጋና ከበሬታ አለው ። 

የተገኘ ድል ያሻግራል እንጂ አያራብሽም ። 

ስኬትም ጉዞ እንጂ ለረብሻና ለሁካታ ለውድመትና ጥፋት መዘጋጀትም ማለት አይደለም ።

ወጣትነት ለምን ብሎም ጠያቂነትና ተመራማሪነት እንጂ የጀሌነትና ተከታይነት ደረጃን መጎናፀፍ አይደለም ። 

የተጋተውንም ቅርሻት መሰል አፈ ታሪክ ተቀብሎም በየቦታው ማላዘን አይደለም ። 

ለሕዝብ አንድነት ተቆርቋሪነት እንጂ አዋኪና ጋሬጣነት መሆንም ማለት አይደለም ። 

ከማኅበረሰቡ ወይም ከሕዝቡ የአብሮነትና የጋራነት መንፈስን ፣ ለችግር ደራሺነትን ተደጋጋፊነትን፣ ጥቃትን በጋራ መመከትን፣ መከባበርንና መቻቻልን ፣ መመካከርን ለግጭት ሥፍራ አለመስጠትንና ግጭትን ለመፍታት ማኅበራዊ ደንቦችንና መንገዶችን …ወዘተ ለመማርና ከዕለት ኑሮው ጋር ለማዋሃድ ” ማስተር ” ያደረገውና ጊዜም ያጠፋበት አይመስልም ። 

በሃሳቡ የቀለለና የወረደ ወጣት ለአገሩም ሸክምና መከራ አባር ጠሪ ነው ።

ለዴሞክራሲ የሚደረጉ ትግሎች ለእከልነትና፣ ለፍትህና ለነፃነት የሚደረጉ እንጂ አንዱን ክፍል ለበላይነትና አምባገነንነትን በሌላ መልኩ የሚተክል ሥርዓትም ለመመሥረትና ለማቆምም አይደለም ።

ወጣትነት ለመግባባትና በፍቅር ለመደሰት እንጂ ለትንቅንቅና ለግጭት ተጣድፎ የማያባራ የሰው ሕይወትን ለመቅስፍና ደም ለማፍሰስ ፣ ጎራም አበጅቶ ለመከሳከስና ለመጠራረብ መደራጀትም አይደለም ።

በመጨረሻም ወጣት ሆይ !

በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለህን ልዩ ሚና ተገንዝበህ ፣ለውጥ ናፋቂነትህን አውቀህ ፣ አንተነትክን ለመቅረፅ የለፋብህን ማኅበረስብ ዕዳውን እንዴት ልክፈል ? ብለህ ታገል እንጂ በግፍና ጭካኔ ተመርተህ ለመጠፋፋት አትደራጅ ።

ነገ ኅሊናህን ይወቅስሃል ። 

እልህንና እምቢተኝነትን ለጨቋኞች አሳያቸው እንጂ ለመሰሎችህ ላይ ጫና ለመፍጠር ፈፅሞ አትጠቀምበት ።

በራስህ ክፉና ደጉን ሩቁን የማየትና የመለየት ንቁህን አዕምሮ አሰራው ።

ሌሎች የሰሩትን አስከፊ ምግባርስ ለመፈፀም የክፉዎችና ሥልጣን ናፋቂዋችም የጥፋት ኃይል ሆነህ ስምህንም አታጉድፍ ።

ከማኅበረሰብህ የወረስካቸው ጠባዮች ፣ ከጨካኞቹ ካገኘኸው መጥፎ ምሳሌ ሁልጊዜ ዋጋና ክብር አላቸው ። 

እነርሱን ጠብቅም መርህም አድርጋቸው ። 

ተጠቀምባቸው እንጂ አትላተምባቸው ፡፡ የነገው ሀገር ተረካቢ ወጣቱ ትውልድ ከሰለጠነ ፖለቲካ አኳያ መሰለፍ አለበት፡፡ ኢትዮጵያን የህግ በላይነት፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባት ሀገር እንድትሆን በቅንነት ከተሰለፈ ኢትዮጵያን ከሞት መታደግ ይቻለዋል፡፡

 

ምን ይሻላል ?

 

በዛሬው ጽሁፌ ላይ ለመዳሰስ የምሞክራቸው ሁለት አንኳር ነጥቦች ታሪክና የብሔራዊ ማንነት ጽንሰ ሃሳቦችን በተመለከተ ይሆናል፡፡ በነገራችን ሁለቱ ጽንሰ ሃሳቦች ማለትም ታሪክና የብሔራዊ ማንነት (history and national identity )  አንዳቸው በአንዳው ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡

በ18ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የጀርመኑ ጸሃፊ ጎይቴ ስለ ታሪክ የሚከተለውን ሃሳብ አስፍሮ ነበር፡፡

‹‹ እንደ ታሪክ የተጻፈልን ነገሮች፣ ሁነቶች፣ውሸቶች ወይም ድርጊቶች ሁሉ በእውነት የተፈጸሙ ላይሆንኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጥንት ዘመን የተፈጸሙ ድርጊቶች፣ ወይም የነበሩ ሁነቶችን ታሪክ መዝግቦ ላያስቀምጠቸው ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻግር  ከብዙ አመታት ተፈጽመው ከነበሩ ሁነቶች መሃከል በታሪክ ተመዝግበው የሚገኙት ሁነቶች በጣም ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አብዛኞቹ ሁነቶች ዛሬ ላይ በታሪክ ድርሳናት ላይ ላይጻፉ ይችላሉ፡፡ በታሪክ ላይ የተቀመጡ ነገሮች ሁሉ ፣ ማለትም ታላላቅ ወይም ታናናሽ ድርጊቶች  ትክክለኛ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ››

በሌላ አነጋገር ታሪክ በስህተት የታጀለ ሊሆን ይችላል፡፡ ታሪክ ሁል ግዜ ይጻፋል፣ ተደጋግሞ ይጻፋል፡፡ ታሪክ የሚጻፈው ደግሞ ዛሬን ትላንት ለማድረግ ነው ሲል ነበር የጀርመኑ ጸሃፊ ጎቴ ስለታሪክ ያለውን ሃሳብ ያሰፈረው፡፡

ታሪክን መማር አንድን ግለሰብ ወይም ህብረተሰብ፣ ወይም ቡድንን ተጠያቂ ለማድረግ አይደለም፡፡ ማንም ሰው ወይም የህብረተሰብ ክፍል ወደዚች ምድር ከመምጣቱ በፊት ለተፈጠሩ ስህተቶች ወይም በደሎች ተጠያቂ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን አንድ ግለሰብ ወይም የህብረተሰብ ክፍል የሀገሩን ታሪክ ማወቅ ካልቻለ ባለፉት እረጅም ዘመናት ወይም አመታት የተሰሩ ስህተቶችን ደግሞ ሊሰራ ይቻለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ ለዚህ ነው ታሪክ እጅጉን ጠቃሚ ነው የሚባለው፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጨቃጨቁ ምሁራን ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያላቸው ብያኔ እጅጉን የተለያየ ነው፡፡ ላለመስማማት ቢቻል እንኳን ያባት ነበር፡፡ ብዙዎቻችን ታሪክ ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ የምንፈልግ አይመስልም፡፡ ከዚህ ባሻግር ብዙዎቻችን በትክክል ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጉጉት የለንም ማለት ይቻላል፡፡ ያለፉ ታሪኮቻችንን በተመለከተ ወደ አንድ አቅጣጫ ለማሰብ ገና ብዙ ይቀረናል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለን ስምምነት አንድ አምሳል አንድ አካል ለመሆን ባያስችለንም ወደ መሃል መንገድ ላይ በመምጣት መስማማት ግድ ይለናል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጥመውን የኢትዮጵያ የታሪክ አካል ብቻ በመቀበል፣ ሌላውን ለእርሱ የማይጥመውን ትክክለኛ ታሪክ አይደለም ማለቱ የሚያዋጣ አይመስለኝም፡፡ በታሪክ እውነታዎች ላይ መስማማት ግድ ይላል፡፡ አንዳንድ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ጸሃፊዎች የሚያዘጋጇቸው የታሪክ መጽሐፍት የሁለት የተለያዩ ሀገራት የታሪክ መጽፍት ይመስላሉ፡፡ ሁለቱም ምሁራን ኢትዮጵያዊ ሆነው የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ ያላቸው አረዳድ እጅጉን የተለያየ ነው፡፡ አንደኛው የታሪክ ጸሃፊ የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ጠቅሶ ሲጽፍ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ምሁር በበኩሉ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከመቶ አመት አመት ወዲህ ይጀምራል ብሎ ይከራከራል፡፡ በእውነቱ ያማል፡፡ ሁለቱም ኢትዮጵዊ  የታሪክ ምሁራን የሁለት ሀገራትን ታሪክ የሚጽፉ ይመስላሉ፡፡

ለአብነት ያህል የዳግማዊ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ካለፈ ከመቶ አመት በላይ ቢሆነውም፤ የአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ትርጉም በተመለከተ በዛሬው ዘመን አጨቃጫቂ ሆኖ መቅረቡ ሲስተዋል የኢትዮጵያን እድል አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡ ስለ አጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት በተመለከተ የጭቅጭቅ መድረክ የሚከፍቱት በአብዛኛው የፖለቲካ ሰዎች ናቸው፡፡ እነኚሁ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ስልጣናቸውን ለማጠናከር ሲሉ ታሪክን ከራሳቸው መጀመር ፍላጎታቸው ነው፡፡ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያየነው ይሄንኑ ነው፡፡ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን የብዙ ሺህ አመታት ታሪክ በመካድ ‹‹ የኢትዮጵያ ታሪክ ከመቶ አመት ›› በላይ አያልፍም በማለት እኩይ የፖለቲካ አላማውን ይዞ የተነሳው የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል ነበር፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ነው በተለይም ከማእከላዊው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ የብዙ ሺህ አመታት ታሪክ በይፋ የተነበገረው፡፡

ፖለቲከኞች በተለይም ከጎሳ ፖለቲካ አኳያ የተሰለፉት የሚወክሉትን ጎሳ አባላት ለማማለል ሲሉ የህብረተሰቡን ስስ ልቦና ለማግኘት በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማጉላት ታሪክን ለእኩይ ስራቸው ይጠቀሙበታል፡፡ ለአብነት ያህል አጼ ምኒሊክ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ስልጣኔ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ገሸሽ በማድረግ ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ አስተባብረው በታሪካዊው የአድዋ ጦርነት ፋሺስት ጣሊያንን ድል በመንሳት ለአለም ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ፋና ወጊ ስለመሆናቸው ወዘተ ወዘተ አንዲት ቃል ሳይተነፍሱ በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ያለተከሰቱ ህጸጾችን ጎላ አድርገው በማውጣት እንደተከሰቱ በማድረግ የአሁኑን ትውልድ በየጊዜው የማሳሳት ድርጊት ሲፈጽሙ ይስተዋላል፡፡ ብሔራዊ ማንነትን ከብዙ ምእተ አመታት በፊት ከተፈጸሙ ስህተቶች ጋር  በማገናኘት መተርጎም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ እከሌ የሚባል ጎሳ እከሌ በሚባል ጎሳ ላይ ያልፈጸመውን ግፍ አጋኖ በየመድረኩ መደስኮር አሁን ላለው ትውልድ የሚጠቅመው አይመስለኝም፡፡ የሚያዋጣው ባለፉት ዘመናት የተፈጸሙ ስህተቶችን ለማረምና ለወደፊቱ እንዳይፈጸሙ በእውነት መሰረት ላይ ሆኖ ቁጭ ብሎ በሰከነ መንፈስ መነጋገር ነው፡፡ እዚች ላይ አንባቢውን ማስታወስ የምፈልገው ቁም ነገር ቢኖር በታሪክ ሂደት ውስጥ የተፈጸሙ ስሁት ስህተቶች አይነገሩ ማለቴ አይደለም፡፡ የእኔ አስተሳሰብ በጥንት ዘመን የተፈጸሙ ስህተቶች  የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሁኑ የሚል ነው፡፡ የታሪክ መማሪያ ቢሆኑ ግን ጠቀሚታቸው ጉልህ ይሆናል የሚለው የግል አስተያየቴ ነው፡፡ አውሮፓውያን የጥንት አባቶቻቸው ከፈጸሙት ስህተት ተማሩ እንጂ የጥንት አባቶቻቸውን ዝንት አለም ሲረግሙ አልተሰተዋሉም፡፡ በጎደለው የአባቶቸቻው ስራዎች ላይ የአይምሮ፣አካላዊና መንፈሳዊ ሃይላቸውን በመጠቀም ሞሉበት ወይም የራሳቸውን እያሳረፉ ወደ ስልጣኔ ገሰገሱ በአድገት ጎዳና ላይ ነጎዱ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልጣኔ ሰማየ ሰማያት ላይ ደረሱ ወይም ወደ ጠፈር ሳይቀር መጠቁ፡፡ የጀርመኑ ታላቁ ቢስማርክና የጣሊያኑ ጁሴፔ ጋሪባልዲ የሃገራቸውን  አንድነት በማስከበራቸው በዛሬው የሁለቱም አውሮፓዊ ሀገራት ትውልዶች ልብ ውስጥ ተቀመጡ እንጂ የእርግማን መአት አልወረደባቸውም፡፡ እርግጥ ነው ቢስማርክም ሆነ ጋሪባሊድ የሀገራቸውን አንድነት አስከብረው ያለፉት በጦርነት ነው፡፡ ሁለቱም ንጉሶች በየሀገሮቻው ዜጎች

የሚወደሱት መልአክ ስለነበሩ አይደለም፡፡ ሁለቱም ከሥህተት ነጻ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን የሰለጠኑት የጣሊያንና ጀርመን ዜጎች የአይምሮ ሃይላቸውን በመጠቀም፣ በጊዜው የተፈጸሙትን ስህተቶች የታሪክ  መማሪያ በማድረግ ወደፊት ለመገስገስ ችለዋል፡፡ እዚህ እኛ ሀገር ደግሞ ከታሪክ አኳያ ያለን ልዩነት እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ስለዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ሁነት በአንዳንድ ምሁራን ያለው ልዩነት ሰፊ ነው፡፡ ይህ በእውነቱ ለመናገር የኢትዮጵያን እድል አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡ ማንም 

እንደሚያውቀው ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ለአለም ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ቀንዲል መለኮስ እና በጊዜው  የቅኝ ገዢዎችን ቅስም የሰበረውን የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ህዝብ በማስተባበር ያስመዘገቡ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊነት ስልጣኔ ያስጀመሩ ታላቅ ንጉሰ ነገስት ነበሩ፡፡ ይህ ሲባል ንጉሰ ነገስት አጼ ምኒሊክ ከሥህተት ነጻ ነበሩ፤ ተግባሮቻቸው ምሉሄ በኩልሄ ነበሩ ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና አክራሪ የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሰርተው ያለፉትን ታላላቅ ቁምነገሮችን ከል በማልበስ 

በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ ስህተቶችን ፈልጎ በማግኘት ወይም ያልተፈጸሙ የታሪክ ስህተቶችን  እንደተፈጠሩ አድርጎ በአደባባይ በመናገር ፣ ወይም በታሪክ ያልተፈጸሙ የፈጠራ ስህተቶችን 

እንደተፈጸሙ አድርጎ በማቅረብ ትውልድን ሲያደናግሩ ማየት የተለመደ ነው፡፡ እነኚሁ ኢትዮጵያዊ  በደል ደርሶብን ነበር የሚሉት ከብዙ አመታት በፊት ነበር፡፡ ያ ዘመን አልፏል፡፡ አለም ተለውጣለች፡፡ 

ኢትዮጵያም የተለወጠች ይመስለኛል፡፡ ዛሬ ለእኛ የሚበጀን አዲስ ትርክት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የሚያስልጋት አዲሱ ትርክት ማጠንጠን ያለበት በእኩልነትና ፍትህ መሰረት ላይ ነው፡፡ ከብዙ ዘመናት  

እነ እከሌ በደልውን ነበር ዛሬ ደግሞ እነ እከሌ ተረኞች ናቸው፡፡ የሀገሪቱን ብሔራዊ ኬክ በዋነኝነት 

መቁረስ አለባቸው የሚለው ትርክት፣ ከነበርንበት የፖለቲካ ወይም የታሪክ ማጥ ሊያወጣን 

አይቻለውም፡፡ ነገሩ ውሃ ወቀጣ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

እስቲ አሁን ደግሞ  የብሔራዊ ማንነት ጽንሰ ሃሳብን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት 

ላይ ያሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን በወፍ በረር እንቃኝ፡፡ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት በሚል እሳቤ

በኢትዮጵያ ሶስት አይነት የፖለቲካ ሃይሎች ውድድር ላይ ያሉ ይመስለኛል፡፡ እነኚህም የሚከተሉት 

ናቸው፡፡

1ኛ. የዜጋ ሀገር (the civic nation, ) 

የዚህ አስተሳሰብ አቀንቃኞች መሰረታቸውን ያደረጉት በዜግነት ፖለቲካ ላይ ያደረጉ ሲሆኑ፣ 

የጎሳ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ አይበጃትም ባይ ናቸው፡፡ ( በነገራችን ላይ መሰረቱን በጎሳ ላይ ያደረገ 

የፌዴራልም ይሁን አሃዳዊ የመንግስት አወቃቀር ከዜግነት ፖለቲካ ተጻራሪ መሆኑን መታወቅ 

አለበት )

2ኛ.መሰረታቸውን ጎሳ ወይም ብሔረሰብ ላይ ያደረጉ ክልሎች (a community of nation states 

በአሁኑ ዘመን በኢትዮጵያ አስር ክልላዊ መንግስታት ሲኖሩ መሰረታቸውም ቋንቋና ጎሳ ላይ 

እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ሃያሲዎች የሄዱበት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ከዜግነት ፖለቲካ ተጻራሪ 

የሆነ ጽንሰ ሃሳብን ይዟል፡፡

3ኛ. የአንድ ጎሳ መኖሪያ ብቻ የሆነ ሉኣላዊ ግዛት መኖር አለበት የሚል አስተሳሰብ ያላቸው 

የፖለቲካ ሃይሎች የሚያራምዱት አደገኛ የፖለቲካ አካሄድ፡፡ ለአብነት ያህል በትግራይ ክልል 

የፖለቲካ ፊትአውራሪዎችና አክራሪ እና ጽንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚያደርጉትን 

እንቅስቃሴ በአንክሮ መመልከት ይቻላል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የፖለቲካ አስተሳሰቦችን ገቢራዊ ለማድረግ ሲሉ እያንዳንዳቸው( ከተራቁጥር 

  1. 3 ) የተጠቀሱት የፖለቲካ ሃይሎች በራሳቸው መገናኛ ብዙሃን ህዝቡን መቀስቀስ 

ከጀመሩ ሰነበቱ ( በራሳቸው የፖለቲካ ፍለስፍና አኳያ ብሔራዊ ማንነትን ለማንበር ማለቴ ነው፡፡) ሆኖም ግን ይሁንና የብሔራዊ ማንነት የኢትዮጵያን አንድነት ባማከሉ መልኩ ገቢራዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ለምን መልሱን ህሊና ለፈጠረባችሁ እተወዋለሁ፡፡ በእኔ በኩል የኢትዮጵያን ጉዳይ በአንክሮ ስመለከት አንዳንድ ክልሎች ኢትዮጵያን የራሳቸውን ( የየክልላቸውን ማንነት ማለቴ ነው ) ማንነት እንድትጠብቅላቸው የሚሰሩ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ለአብነት ያህል የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለፌዴራሉ ህግ አልገዛም በማለት በአደባባይ የሚያደርገውን ፉከራ ማየት ይቻላል፡፡ አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞችም የሚያሳዩትን ያዙኝ ልቀቁኝ ድንፋታ የአይምሮ ሚዛኑ ያልተሰበረ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚያውቀው ጉዳይ በመሆኑ

እዚህ ላይ መዘርዘሩ ጊዜ ማባከን ይመስለኛል፡፡ የበለጠ እና ፍንትው ብሎ በኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት ላይ  የሚታየው እውነታ ግን የኢትዮጵያን አንድነትና የሀገር ህልውና ለማስጠበቅ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል በአንድ በኩል፣ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ የበለጠ የራስ ገዝ ነጻነት ለማግኘት የሚደረግ የፖለቲካ ትንቅንቅ ጎምዛዛ እውነት 

ነው፡፡ 

ከላይ ካሰፈርኳቸው አንኳር አንኳር ሃሳቦች በመነሳት የሚከተሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች ማንሳት ይቻላል፡፡

እኛ ማን ነን ? የእኛ ማንነት መሰረቱ ምንድን ነው ?  ስለ ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና ወይም ትርጉም ያለን ግንዛቤ ምን ይመስላል ? በብሔራዊ ማንነት ትርጉም ላይ ያለን ግንዛቤ ከእድሜና ከጎሳ ስብጥር አኳያ ምን ይመስላል ?( ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወጣቱም ሽግሌውም፣ ጎልማሳው፣ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ የሚገኙ የጎሳ አባላት ሁሉ )  ለፖቲከኞች ምቾት ስለማይሰጡ ብቻ እነኚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች ማንሳት ጊዜው አይደለም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ለኢትዮጵያ አይበጃትም፡፡ በአሁኑ ግዜ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ለኢትዮጵያ አንድነትና ህልውና ሲል ለተጠቀሱት ጥያቄዎችና ሌሎች ጥያቄዎችን በተመለከተ  መልስ ለማግኘት የውይይት መድረክ እንዲከፍት ሳስታውስ በአክብሮት ነው፡፡

ሁሉንም ልጆቿን በሚያስማማ መልኩ ኢትዮጵያ ዳግም አንድነቷ ይመለስ ይሆን ?

በእኔ አስተሳሰብ አብዛኛው የወጣቱ ክፍል የማንነት ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም በተመለከተ ያለው ግንዛቤ ጥልቀት ያለው አይደለም ( ላይላዩን ይመስላል )፡፡ ከዚህ ባሻግር በተለያዩ አካባቢዎች የተወለዱ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ከአካባቢያቸው ውጪ ስላሉ ጎሳዎች ማንነት ያላቸው ግንዛቤ ምሉሄበኩልሄ አይደለም፡፡ በአጭሩ ወጣቱ ትውልድ ስለ ኢትዮጵዊ ማንነትና የጎሳ ማንነት በተመለከተ ስላላቸው ተመሳሳይነትና ልዩነት ጥልቀት ያለው እውቀት ደካማ ነው፡፡ ወጣቱ ትውልድ በልዩነት ላይ ብቻ እንዲያተኩር የተሰራበት ይመስላል፡፡ ( ይህ የግል ምልከታዬና አስተሳሰብ ነው፡፡)  መሰረታዊ ጥያቄው ግን ይህ ለምን ወይም እንዴት እውን ሆነ ? የሚለው ቁምነገር ይመስለኛል፡፡

በነገራችን ላይ የሀገር ግንባታ እጅግ ውስብስብ፣ ጭቅጭቅ ያለበትና ውድድር የበዛበት እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ከዚህ ባሻግር የሀገር ግንባታ ሁሉም የዛች ሀገር ዜጎች የሚያዋጡት ማንነት ፣ ባህል ፣ ታሪክ እና ቋንቋን ይጨምራል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ሁሉንም የሚያስማማ ራእይ፣ መድረሻ ያላት አይመስልም፡፡ ሁሉንም ልጆቿን የሚያስማማ አላማ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀራታል፡፡ እንደ አንድ ታላቅ ህዝብ ወይም ማህበረሰብ በሁሉም ነገሮች አኳያ መልካም ለመሆን የተዘጋጀን አይመስልም፡፡ እኛ የመረጥነው ቀላሉን ነገር ማለትም በመሬት ላይ የህልም እንጀራ ለማግኘት ነው፡፡ እኛ የመረጥነው እርስበርስ ለመናቆር እንጂ ጠንክሮ ለመስራት አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ የበላይ ለመሆን ነው ትግላችን፡፡ የስራ ጀግና ለመባል የሚጥሩ ሰዎች ኢምንት ናቸው፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ሀብት ለመሰብሰብ እሩጫው በዝቷል፡፡ ብርብር ስንል ብር ብለን እንዳንቀር ስጋት አለኝ፡፡ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት የፖለቲካ ስልጣናቸውን ለህዝብ ጥቅም ሲሉ እነማን መልካም ስራ አከናወኑ እነማን ለራሳቸው ጥቅም ቆሙ ህሊና ያላችሁ ጠይቁ፡፡ ለማናቸውም የፖለቲካ ስልጣንን በአግባቡና ህጋዊ መንገድ መጠቀም ለሀገር ግንባታው ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህ ባሻግር የጎሳ ፖለቲካ ይቺን ታሪካዊት ሀገር እያደማ ስለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ወያኔ የቀደደው የጎሳ ቦይ አሁን ድረስ ማጠፊ አልተበጀለትም፡፡ በእኔ አስተሳሰብ የጎሳ ፖለቲካ በእኛ ዘመን ታላቅ የሞራል እንቅፋት መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና እንዴት ነው የአንድን ሀገር ማንነት መገንባት የሚቻለው ?

ከየት እንጀምር  መልካም ነው፡፡ በእኔ አስተሳሰብ የማንነታችን መሰረት ከድንበር ባለፈ መስፋት አለበት፡፡ የማንነታችን መሰረቱ፡-

  • ሁሉም ወገኖች በተስማሙበት ህግ መሰረት የተሰመረ መሬት፣ ሁሉም ወገኖች ያለገደብ የሚንቀሳቀሱበት የጋራ ድንበር
  • የሀገሪቱ ሉአላዊነትን ያስከበረ፣ ማናቸውም የሀገሪቱ ዜጋ በማናቸውም የገሪቱ ግዛቶች በነጻነት የሚኖርበት ግዛቶች መፍጠር
  • የሃይማኖት፣ የጎሳ ልዩነት … ወዘተ አለማድረግ የጎሳና ሃይማኖት እኩልነት በእውነት መሰረት ላይ እንዲቆም መስራት
  • በግዛቶቹ መሃከል ያለው ድንበር ልክ በአንድ መኖሪያ ቤትና በሌላኛው መኖሪያ ቤት መሃከል እንዳለው አይነት መሆን ይገባዋል፡፡
  • ከጎሳ ማንነት ላይ ይልቅ ኢትጵያዊ ማንነተን የሚያስቀድሙ ዜጎችን ለማፍራት  ከተማ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ ( በመልክ ጥቁር)፣ በአሰቃቂ ሁኔታበሌላ አሜሪካዊ ዜጋ ( በመልክ ነጭ የሆነ ፖሊስ) በመገደሉ ምክንያት የተቃወሙት የአሜሪካ ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ የሰለጠኑት አውሮፓውያን እና አውስትራላዊያን ነበሩ፡፡ እባካችሁ በሰውነት ደረጃ ለመቆም  እንጣር፡፡
  • በሰውነት ደረጃ ላይ እንቁም፡፡ በአሜሪካን ሀገር ሚኒያፖሊ በምትባል
  • የሀገሪቱን ብሔራዊ ኬክ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚካፈሉበትን የዲሞክራቲክ ስርአት ህዝቡ መፍጠር ወይም መመስረት የህለውና ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ማንም ሰው ወይም ጎሳ ወደኋላ መቅረት የለበትም፡፡ እርግጥ ነው ከላይ የጠቃቀስኳቸው ነጥቦች ብሔራዊ ማንነትን ለመገንባት በቂ አይደሉም፡፡ የቀረውን ጨምሩበት፡፡ ሰላም፡፡
Filed in: Amharic