>

ከመምህር ዘመድኩን ጐን ነኝ! (ኤርሚያስ ለገሰ)

ከመምህር ዘመድኩን ጐን ነኝ!

ኤርሚያስ ለገሰ

መምህር ዘመድኩን በቀለ ፕሮግራሞቹን በዩቲዩብ ይዞ መምጣት ከጀመረ የመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ተከታትየዋለሁ። በዚህም፣
፩: ዘመድኩን በየቀኑ የተመለከትኩት ለሕሊና እስረኛው፣ ለባለማተቡ፣ ለሰላማዊ ታጋዩ እስክንድር ነጋ ሲጮህ ነው። እውነት ለመናገር የመምህር ዘመድኩንን ያህል ለዚህ “የአብይ አህመድ ግላዊ ቂም መወጣጫ” ለሆነው የፓለቲካ እስረኛ የጮኸ የለም። ይሄንን በድፍረት እመሰክራለሁ። ትላንት በእስክንድር የነገዱ ሰዎች አንድም ለእስሩ መረጃ ሲያቀብሉ፣ አሊያም እስክንድር ከኢትዮጵያ አይበልጥም እያሉ ሲያላግጡ፣ ወይም በዝምታ አገዛዙን ሲተባበሩ ባየንበት ጩኸቱ በየቀኑ ከአድማስ አድማስ የሚሰማው የዘመድኩን ነበር።
፪: መምህር ዘመድኩን ነውረኛው የአብይ አህመድ አቃቤ-ህግ ባለስልጣን (አቃቤ ህጉ ቴዲ አፍሮን ጨምሮ ሌሎች ላይ ስለፈፀመው ወንጀል ወደፊት በሰፊው እመለስበታለሁ)  ከእነ እስክንድር ጋር በአካል እንኳን ተገናኝቶ የማያውቅ ግለሰብን በክስ ፋይል ውስጥ ሲያካትት መረጃውን በአደባባይ በማውጣት ያጋለጠ ነው። አገዛዙ የሚይዘው የሚጨብጠው ሲያጣ ግለሰቡን ያለፈው ሳምንት በዋስ ፈቶታል። ለዚህም ክሬዲቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ ያለበት መምህር ዘመድኩን በመሆኑ በአደባባይ ምስጋናዬን አድርሻለሁ።
፫: መምህር ዘመድኩን ሐይማኖታዊ ግዴታውን እየተወጣ መሆኑን ብገነዘብም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ላይ የደረሰውን “ጄኖሳይድና ንብረት ውድመት” በቁጥር አንድ ያጋለጠ ነው። አንዳንዶች ከነአካቴው ሲደበቁ፣ ሌሎች አደጋውን ሲሸፋፍኑት፣ ደግሞ ሌሎች “ኦርቶዶክስ ከኢትዮጵያ አትበልጥም” ሲሉ ቁምስቅሉን ያየው፣ ለወገኖቹ አለንላችሁ በማለት በሚሊዮኖች አሰባስቦ የላከው መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው።
፬: በኦሮሙማ የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋትና ማጥራት ስራ በታቀደ መንገድ ሲፈፀም እስከዛሬም ያለማቋረጥ እሪታውን እያሰማ ያለው መምህር ዘመድኩን ነው። በአማራ ላይ ለደረሰው ጄኖሳይድ መጮህ አማራ መሆን እንደማይጠይቅ ቋሚ ምስክር የሆነው መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው።
፭: የአፋር ህዝብ በጐርፍ ሲጥለቀለቅና የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ ከቀዳሚ ደራሾቹ አንዱ መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው። በዚህ ድርጊቱም ለወገን ለመድረስ መስፈርቱ ሰው መሆንና ኢትዮጵያዊነት እንጂ የሐይማኖት ልዩነት እንዳልሆነ የተግባር ምስክር ሆኗል።
ሲጠቃለል የዘመድኩንን ዩቲዩብ መከታተል ከጀመርኩ ጀምሮ የተመለከትኩት ለግፉአን ጠበቃ ሲቆም፣ ለአብይ አህመድ ህሊና እስረኞች ሲጮህ፣ ለእምነቱ ግዴታውን ሲወጣ፣ ስቃይና መከራ የደረሰባቸውን ሲያጽናና እና የክፉ ቀን ደራሽ ሲሆን ነው።
 ይሄ ማለት ግን በሁሉም የዝግጅቶቹ ይዘትና አቀራረቦቹ እስማማለሁ ማለት አይደለም። አንዳንዴም የሚያቀርባቸው ምስጋናዎች( ለምሳሌ በአሜሪካን የኢትዮጵያ ኤምባሲ: የተጐነጐነው ሴራ አካል መሆኑን እገምታለሁ) ቢቀንሰው እመርጥ ነበር።
#i_stand_with_zemedkun_bekele_challenge
Filed in: Amharic