>

"በኢትዮጵያ ውስጥ በእስላምና በክርስቲያን መካከል ልዩነት አለ የሚል ቢኖር እሱ የኢትዮጵያ ጠላት ነው!!!" ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ

“በኢትዮጵያ ውስጥ በእስላምና በክርስቲያን መካከል ልዩነት አለ የሚል ቢኖር እሱ የኢትዮጵያ ጠላት ነው!!!

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
አቻምየለህ ታምሩ

ኦነጋውያኑ እነ አሕመዲን ጀበል፣ ለማሰብ ፈቃደኛ ያልሆነው ትውልድና ባገሩ ላይ ያሳመጹት ተከታያቸው እውነት ቢሆንም እንኳን “ሊሆን አይገባውም” ብለው አቋም ቢይዙበትም፤  ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ ፋሽስት ጣሊያን ጀምሮ የተወውን ኢትዮጵያውያንን በሃይማኖትና በነገድ ለያይቶ የማባላት ፕሮጀክት በመንግሥትነት ተሰይመው ከማስቀጠላቸው በፊት የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ ሃይማኖቶች ልዩነት ያራምደው የነበረው እምነት የሚከተለውን ይመስል ነበር፤
” በኢትዮጵያ እስላም፤ ክርስቲያን፤ ሌላም ሃይማኖት ያላቸው ሁሉ ወንድማማቾች ስለሆኑ አንዳቸውም ካንዳቸው ልዩነት የላቸውም።. . . በዓለም ላይ ያለው የእስላምና የክርስቲያን ሃይማኖት ብቻ አይደለም። ብዙ ልዩ ልዩ ሃይማኖት አለ። . . . ይሁን እንጂ ስለአገራቸው ሲሠሩ ልዩነት ሳይኖራቸው ነው።. . . በቤተ ክርስቲያን ጸሎትና ስንግደት ሲደረግ በመንጊድም የሚደረገው ይኸው ነው። . . . [በኢትዮጵያ ውስጥ] በእስላምና በክርስቲያን መካከል ልዩነት አለ የሚል ቢኖር እሱ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።”
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
መስከረም 1945 ዓ.ም.
አስመራ 
[ምንጭ፡ ጋዜጣና ማስታወቂያ ማሥሪያ ቤት(1945)፣ አዲሲቱ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ገጽ 206-207]  
_______________________________
በነገራችን ላይ ዛሬ ሕዝበ ክርስቲያኑ መስቀልን እንዳያከብር በአፓርታይድ አገዛዙ እየተደረገ  ያለበት አካባቢ በፋሽስት ጣሊያን ዘመን እንዳያከብር እየተደረገ ባለበት አካባቢ ነው።  ይህ የሚያሳየው በፋሽስት ጣሊያንና በዛሬው አገዛዝ መካከል ልዩነት አለመኖሩን ነው። ሆኖም ግን ዛሬ መስቀል እንዳይከበር የተከለከለበት አካባቢ እንዳይከበር የሚከለክሉት ባለጊዜዎች ከ400 ዓመታት በፊት ዛሬ እንዳይከበር እየከለከሉ ወዳሉበት አካባቢ በወራሪነት ከመግባታቸው በፊት የጥንት ባለርሥቱ  በነገድ ልዩነት ሳይወሰን በግዕዝ ቋንቋ  በነገድ “መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ” እያለ የመስቀልን በዓለ ለዘመናት ያከብር ነበር።
 
 
ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የኢትዮጵያን እስልምና ለዓለም ለማስተዋውቅ  ከመስጂድ ጋር ሆነው ያሳተሙት የፖስታ ቴምብር!
የፖስታ ቴምብር መንግሥታት አገራቸውን በዓለም ዙሪያ ከሚያስተዋውቁባቸው ዘዴዎች ውስጥ አንዱ ነው። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ኢትዮጵያን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋውቅ እስከ 1966 ዓ.ም. ያሳትማቸው ከነበሩት የፖስታ ቴምብሮች መካከል አንዱ ከታች  የታተመው  ክርስቲያኑ ነጉሠ ነገሥት ከመስጂድ ጋር ሆነው የሚታዩበት ቴምብር ነው። በቴምብሩ መደብ ላይ የሚታየው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ያሳተመው የምጽዋ መስጂድ ንጉሡ ራሳቸው በገንዘባቸው ያሰሩት መስጂድ ነው። በመንበረ ዳዊት የተቀመጡ፣ በሃይማኖታቸው ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ የሆኑት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያን  እስልምና ለዓለም ለማስተዋወቅ ከመስጂድ ጋር ሆነው የፖስታ ቴምብር ያሳተሙ በዓለም ላይ ብቸኛውና የመጨረሻው ክርስቲያን ንጉሥ ናቸው።
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሙስሊም ዜጋቸው ቁርኣንን በቋንቋው እንዲማር በገንዘባቸው ቁርኣንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጎም ያደረጉ፣ ሙስሊም ዜጎቻቸው እንደሃይማኖታቸው ሥርዓት እንዲዳኙ የሸርያ ፍርድ ቤት በአዋጅ ያቋቋሙ፣ ጎዴ ላይ የተሰራውን የመጀመሪያውን መስጂድ ጨምሮ በመላ አገሪቱ በርካታ መስጂዶችን በገንዘባቸው ያሰሩ  በአለም ላይ  የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ክርስቲያን ንጉሥ ናቸው። ዛሬ ላይ ክርስቲያኑ መስጂድ ሲሰራ፤ እስላሙ ቤተክርስቲያን ሲሰራ ገንዘብ የሚያዋጣው የንጉሡን አድራጎት በመከተል ነው።
እነ አሕመዲን ጀበል ግን በሃይማኖት ስም በሚደርቱት የኦነግ ፕሮፓጋንዳ ለማጣራትና በራሱ አስቦ ምርምሩ ወደሚወስደው ድምዳሜ ለመድረስ ፈቃደኛ ያልሆነውን መንጋቸውን በበሬ ወለደ “ንጉሡ ለአሜሪካኖች ገንዘብ ከሰጣችሁኝ እስላሞችን አጠፋቸዋለሁ” አሉ እያሉ ነጉሡን እስልምናን ለማጥፋት ሲሰሩ እንደኖሩ  በማስመሰል  «ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615 – 1700 የጭቆናና የትግርል ታሪክ » ፤ «ሦስቱ አጼዎችና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች» ወዘተ… የሚሉ የቅስቀሳ ድርሰቶችን ሲደርቱ የስናፍጭ ቅንጣት ታህል ሚዛናዊ ለመምሰል ብለው ክርስቲያኑ ንጉሥ የኢትዮጵያን እስልምና ለዓለም ለማስተዋወቅ  ከመስጂድ ጋር ሆነው  ያሳተሙትን የፖስታ ቴምብር ትውልዱን በአገሩ ላይ እንዳያምጽ ስለሚያደርግባቸው በግርጌ ማስታወሻ እንኳን ማስታወስ አይፈልጉም።
Filed in: Amharic