>

አብርሀም ሊንከን እና ዶ/ር አብይ አህመድ (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

አብርሀም ሊንከን እና ዶ/ር አብይ አህመድ

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ


አብርሀም ሊነከነ 16ኛው የአሜሪካ ፕረዛዳንት ሲሆን ሊንከን ፕረዛዳንት በነበረበት ጊዜ አሜሪካ በእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበረች፤ እንዲሁም ሀገሪቱ ከፍተኛ በሆነ በግብረ-ገብነት እና በፖለቲካ ቀውስ ትናጥ ነበር፡፡ በእንዲህ አይነት ቀውስ ውስጥ ሊንከን የአሜሪካን አንድነት በመጠበቅ፣ ተንሰራፍቶ የነበረውን የባሪያ ንግድን በማስቀረት፣ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የተሳካለት መሪ ሁኖ ስሙ በመልካም ሲነሳ ይኖራል፡፡ ሊንከን በእርስ በርስ ጦርነት ደክማ የነበረን ሀገር ወደ ህብረት በማምጣት የተዋጣለት ታላቅ መሪ ሁኖዓል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ዶ/ር አብይ አህመድ መለስ ዜናዊ በጎሳ ፖለቲካ ሊበታትናት የተቃረበችን ሀገር እንደ አብርሀም ሊንከን አንድ ያደርጓታል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ በለውጡ የመጀመሪያዎቹ ወራት ‘ቲም ለማ’ እየተባለ የሚጠራው የለውጥ ቡድንም ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ የአብዛኛው ህዝብ ድጋፍ ተችሮዓቸው ነበር፡፡

ዳሩ ግን የለውጡ ቡድኑ አንድ አንድ እያሉ ከለውጡ ሜዳ መንሸራተት ጀመረ፡፡ የሀገራዊ አንድነት ስሜት እና ወኔ አላቸው ያልናቸው አቶ ለማ መገርሳ በብሄር ፖለቲካ ተነድፈው የአዲስ አበባን ‘ዲሞግራፊ‘ ለመቀየር ሲታትሩ አይተን ተስፋ ቆረጥንባቸው፡፡ በለውጡ ማግስት ዶ/ር አብይ አህመድ የወሰዷቸውን አንኳር አንኳር እርምጃዎችን አይቸ፣ ዶ/ር አብይን ከአብርሀም ሊንከን ጋር ደምሬዓቸው ነበር፡፡ ሁኖም ግን ዶ/ር አብይ ከገፅታ ግንባታ ውጭ ትልቁን የሰውን ልጅ ደህንነት ስለዘነጉት እና የፍትህ ስርዓቱ መዛባቱን ስለተረዳሁ ከለውጡ ሜዳ መውጣታቸው ተሰማኝ፡፡  ዶ/ር አብይ ‘እንደሚያሻግሩን ’ ነግረውን ሳይሻገሩት በቀሩት ኢትዪጲያውያን አዘንሁ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶ/ር አብይ የህዝቡ ድጋፍ አሁንም እንዳላቸው ሲያወሩ ሰማሁና ገረመኝ፡፡ እርሰዎ በሚያስተዳድሩት ሀገር ሰውን ያህል ፍጡር በግፍ እየተገደለ፣ እየተሰደደ፣ ንብረቱ እየወደመ፣ ባቀናው ሀገር አገርህ አይደለም እየተባለ፣ ንብረት እየተዘረፈ፣ ሰው ወጦ መግባት ተስኖት እያለ እንዴት የህዝብ ድጋፍ እንደሚኖረዎ ያስባሉ? 

Filed in: Amharic