>

የአማራ ነፍስ ዋጋው ስንት ነው...??? አሳዬ ደርቤ

የአማራ ነፍስ ዋጋው ስንት ነው…???

አሳዬ ደርቤ

ሳምንቱን ሙሉ በተናጠል የምንፈልገውንና ከሌሎች የሚሰጠንን አጀንዳ ማንጸባረቁ እንደተጠበቀ ሆኖ ለየት ባለ መልኩ ደግሞ በየትኛውም ተባራሪ አጀንዳ ሳንጠለፍ የህዝባችንን ጥያቄዎች ይዘን በጋራ የምንዘምትበት ቀን ሊኖረን እንደሚገባ ተስማምተናል፡፡ ስለሆነም፡-
.
➛ያለአግባብ ለታሰሩ ወንድሞቻችን ፍትሕን የምንጠይቅበት
➛ደብዛቸው ለጠፋ እኅቶቻችንን ድምጻችንን የምናሰማበት
➛በየስፍራው የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን የምናስብበት
➛የብአዴን እድሜ ጠገብ እንቦጮች ተነቃቅለው ለወገናቸው የሚያስቡ አመራሮች ወደፊት እንዲመጡ የምንታገልበት
➛በጎጥና በሃይማኖት ሊከፋፍሉን ለሚሞክሩ ሃይሎች ሕብረታችንን የምናሳይበት
➛በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በስሙ ይጠራ ዘንድ የምንሟገትበት
➛ግፈኞች የፈጸሙብንን በደል ለሌላው ኢትዮጵያዊ የምናሳውቅበት
➛በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የሃይል ጥቃትና ኢኮኖሚያዊ መገለል እንዲቆም የምንጠይቅበት
➛የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ይቋቋሙ ዘንድ የግላችንን ጥረት የምናደርግበበት
➛በክልላችን ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ዙሪያ የምንመክርበት
➛የተሻለ ወቅትና ሥርዓት በትግላችን እስኪመጣ ድረስ የሚከማች በደል እንጂ የምንረሳው ግፍ አለመኖሩን የምናሳይበት
➛የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ድምጻችንን የምናሰማበት…. የሶሻል ሚዲያ የዘመቻ ቀን ‹‹ዘወትር ቅዳሜ›› እንዲሆን ተወስኗል፡፡
.
Filed in: Amharic