>
5:13 pm - Wednesday April 19, 0890

"ታከለን በማስጨነ...ቅ ተብሎ የቀረበብን ክስ አስቂኝ ነው...!!!" (ስንታየሁ ቸኮል)

“ታከለን በማስጨነ…ቅ ተብሎ የቀረበብን ክስ አስቂኝ ነው…!!!”

ስንታየሁ ቸኮል
ለመስከረም 12 በዕለተ ማክሰኞ ….የዋስትና መብት ይሰጥ ወይስ ይቅር የሚለውን ለመወሰን ተቀጥሯል።
ግን ….በችሎቱ እነ እስኬ ምን አሉ !
ስንታየሁ ...ታከለን በማስጨነ…ቅ ተብሎ የቀረበብን ክስ አስቂኝ ነው። ***” ታከለ በመንግስት ስልጣን ተቀምጦ ሲባልግ ማስጨነቅ ስራችን ነው”። የድሃ ኮንዶሚኒየም ሲዘረፍ ..መሬት ሲወረር ….ታሪካዊ ቅርስ ሲፈርስ….ድሃ ሲፈናቀል ታከለን ማስጨነቅ ስራችን ነዉ።”
“ፍትህ የሚገኘው በቅድሚያ ከፈጣሪ ነው።” ቀጥሎ ከጭቁኑ ህዝብ……ከዛም የፖለቲካ ጫና እንዳለባችሁ እያወቅን በናንተም ተስፋ አንቆርጥም።
አስቴር …..” የዚህ አገር ፍትህ የተለየ ነው። ፍትህ ተብሎ የሚፈፀመው ወንጀለኞችን ሸሽጎ በእኛ በንፁሃን ላይ ነው።”
እስክንድር ..…”  እኛን አስሮ ሊደረግ የሚታሰብ ምርጫ የባሰ የቁልቁለት መንገድን የሚወስድ እንጅ …እነሱ የሚሉትን ፍትህና ሰላም እኩለነት የሚያመጣ አይደለም።”
አስካለ …..” እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ የታሰርኩት ለምን የባልደራስ አመራር ሆንሽ ተብየ ነው።የሴቶች እኩልነትን አራምዳለሁ የሚል መንግስት ሴቶችን ወደ መድረክ እንዲመጡ የሚፈቅደው የራሱ ደጋፊና አባል ሲኮን ብቻ ነው ወይ ? “
Filed in: Amharic