>

በመተከል አማራ ላይ የተካሄደው ፍጅት ብአዴን በፕሮግራም ይዞ የታገለለት ዓላማ ነው! (አቻም የለህ ታምሩ)

በመተከል አማራ ላይ የተካሄደው ፍጅት ብአዴን በፕሮግራም ይዞ የታገለለት ዓላማ ነው!

አቻም የለህ ታምሩ

ጎጃም የነበረው መተከል አማራ የሚታረድበት ቄራ የሆነው ብአዴን ፕሮግራም ቀርጾ ባደረገው ትግል ነው። መተከል ከጎጃም ተወስዶ እንዲህ አማራ የሚታተድበት ቄራ የሆነው አማራው ከሌሎች ነገዶች ጋር ተሰባጥሮ የሚኖርባቸውን አካባቢዎች ሁሉ የአማራው ጉድ ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራሙ ላይ «ነፍጠኛውና ትምክህተኛው አማራ ሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችን ለመጨቆን በወራሪነት የሰፈረባቸው የሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦች ክልሎች ከነፍጠኞች ነጻ ለማድረግ እንታገላለን» ባለው መሰረት ነው። በመሆኑም መተከል የአማራ መታረጃ ቄራ የሆነው ብአዴን በፕሮግራም ደረጃ ባደረገው ትግል ነው።
ከሰሞኑ ከወደመተከል እየሰማነው ባለውና ከመቶ በላይ በሚሆኑ አማሮች ላይ የተፈጸመው ፍጅትም የተካሄደው ብአዴን ባለፈው ሳምንት ከሽመልስ አብዲሳ ጋር ባሕር ዳር ጠርቶ ካባ የሸለመው አሻድሊ ሐሰን ግፉአኑ ራሳቸውን እንዳይከላከሉ ካደረገና ባካባቢው የነበረው ፖሊስ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ካደረገ በኋላ ነው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው ብአዴን ለሺመልስ አብዲሳና ለአሻድሊ ሐሰን የሸለመው ካባ ትርጉሙ አማራን አስፈጁ፣ ነፍጠኛን ስበሩ፣ ከቀየው ጠራርጋችሁ አስወጡ፣ በርቱ ተበራቱ ከጎናችሁ ነን ማለት ነው።
ባጭሩ የመተከሉ እልቂት ብአዴን በፕሮግራሙ የታገለለት ፍጅት ነው። የፍጅቱ መንስኤ የሕወሓትን አማራን የማጥፋት ፕሮግራም እንዲያስፈጸም የተፈጠረውና በአማራ ላይ ፍጅትና የዘር ማጥፋት የሚፈጽሙትን አለማቀፍ ወንጀለኞች ካባ የሚሸልመው ቀንደኛው የአማራ ባለደም ብአዴን ነው። አማራን ሊያጠፋ የመጣ አካል በምንም ምክንያት አማራን ሊያድነንና ሊታደግ እንደማይችል ከዚህ በላይ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም።
በመሆኑም አማራም ሆነ ኢትዮጵያ የሚድኑት በልቶ ማደርን ብቻ የሕይዎት መመሪያቸው ያደረጉ የአማራ ርግማኖችና አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ የተፈጠሩ ሆዳም አማሮች ነውረኛ ድርጅት የሆነው ብአዴን ሲወገድ ብቻ ነው።
Filed in: Amharic