>

አማራ ነኝ የሚል ሁሉ  አሁን ራሱን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ «ምን አለኝ»? የሚል  ጥያቄ ሳይሆን «ምንድን ነኝ»? የሚል ጥያቄ ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

አማራ ነኝ የሚል ሁሉ  አሁን ራሱን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ «ምን አለኝ»? የሚል  ጥያቄ ሳይሆን «ምንድን ነኝ»? የሚል ጥያቄ ነው!

አቻምየለህ ታምሩ

በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ይሁንታ በአገዛዙ የመሳሪያ ግምጃ ቤት የተከማቸውን መሳሪያ ታጥቆ ወለጋ የሸመቀው ኦነግ የሚባለው አሸባሪ ድርጅትና  ሽመልስ አብዲሳ በቤንሻንጉል የኦሮሙማን አላማ ለማሳካት ባሰማራቸው ልዩ ኃይሎች የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ትናንት  ጎጃም በነበረውና ብአዴን ባደረገው ትግል አዲስ ወደተፈጠረው ክልል እንዲካተት በተደረገው በመተከል የተፈጁት ከመቶ በላይ የሚሆኑ ንጹሐን አማሮች አስከሬን ሽታ ወደ ወረዳው እንደማያስገባ የግፉዓን ቤተሰቦች ከስፍራው እየተናገሩ ይገኛሉ።
አብዛኛዎቹ ግፉዓን ሴቶችና ሕጻናት ሲሆኑ አገርና መንግሥት ስለሌላቸው እስካሁን ድረስ አስከሬናቸውን በክብር የሚያሳርፍ  መንግሥት ነኝ የሚል አካል አልተገኘም። አማራ አገርና ሕዝብ ቢኖረው ኖሮ ከእምቦቀቅላ ሕጻናት እና  ሴት በጅምላ መታረድ በላይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚያሳውጅ  ብቻ ሳይሆን አገራዊ፣ መንግሥታዊና ሕዝባዊ አጀንዳ ባልኖረ ነበር።
አሁን ጥያቄው አማራ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ምን አለን የሚለው ሳይሆን ምንድን ነን የሚለው ነው መሆን ያለበት። ምንድን ነን? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሰዎች ነን የሚል ከሆነ እየደረሰብን ያለውን ውርደትና ንቀት መሸከም የሚችል ትክሻ ያለን ብቸኛ ሰዎች እኛ ብቻ መሆን አለብን!
ሰዎች ነን ብለን የምናስብ አማሮች ሁሉ ብአዴን የሚባል የአማራ ጠላቶች እንደራሴ እስካለ ድረስ የአማራ ውርደት እንደሚቀጥል ካላሰብን እየደረሰብን ያለውን ውርደትና ንቀት መሸከም የሚችል ትክሻ ያለን ብቸኛ ሰዎች እኛ ብቻ እንሆናለን።
ሁሉም ብአዴኖች አንድ ናቸው።  ብአዴኖች ሁሉ  የታገሉት “የአማራ ክልል” ከሚባለው ውጭ ያለ አማራ ሁሉ ነፍጠኛ፣ ትምክተኛና ሌሎችን ለመጨቆን የሄደ ወራሪ ስለሆነ እንደ አደገኛ  አውሬ እየታደነ እንዲገደል ነው። ይህን አላማውን በ1986 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ ላይ ጽፎታል።
የአማራ ሕዝብ በየቀኑ እየደረሰበት ካለው ውርደት ለመውጣት ፋሽስት ወያኔን በብርቱ እንደተፋለመው ሁሉ በእንደራሴነት የጫነበበትን የፋሽስት ወያኔን ነውረኛ ድርጅት ብአዴንም ከቀድሞ ጌታው ከፋሽስት ወያኔ እኩል መዋጋት አለበት።
ብአዴኖች ሁሉ የዐቢይ አሕመድ አተላ ተሸካሚ ሆኖ መኖር የሞቃቸው፤ በአስካሪስነት ዘመናቸው ባንዳ ሆኖ ከመኖር በቀር የሕዝባቸው ጉዳይ ቅንጣት ታህል አሳስቧቸው እንቅልፍ የማይነሳቸው፤ ኅሊናቸውን በዐቢይ አሕመድ ሙሉ ቁጥጥር ስር ያዋሉ ከርሳሞች፤ ዘወትር ለሆዳቸው ማደር የአእምሮ እረፍት የማይነሳቸው በድኖች፤ ባልበደላቸው የአማራ ሕዝብ ላይ የጠላቶቹን ሴራ ሲያስፈጽሙ ቀኑን ሙሉ ውለው ሌሊቱን ሙሉ ቢያድሩ የማይጠግቡ የፖለቲካ ጅቦች ናቸው።
ባጭሩ ሰዎች ከሆንን ፋሽስት ወያኔ፣ ናዚ ኦነግና የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሱት ያለው የዘር ማጥፋት አማራን ጠላት ያደረጉ ኃይሎችን አላማ ግንባር ቀደም መሳሪያ ሆኖ እያስፈጸመ ያለውን ብአዴን የሚባለው ስብስብ በአማራ ሕዝብ ላይ ተጭኖ እስከቀጠለ ድረስ በከፋ ሁኔታ እንደሚቀጥል፤ አማራው ወደፊትም ገና ብዙ ውርደት እንደሚጠብቀው ማሰባችንን በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል።
Filed in: Amharic