>

እነዚህ አቢያውያን እንደዚያ ቀልደኛ እረኛ እንዳይሆኑ እፈራለሁ! (አምባቸው ደጀኔ)

እነዚህ አቢያውያን እንደዚያ ቀልደኛ እረኛ እንዳይሆኑ እፈራለሁ!

አምባቸው ደጀኔ


“በጎቼን ቀበሮ በላብኝ” በሚል የውሸት ወሬ መንደርተኛውን እያስደነገጠ ሲደርሱለት ይስቅባቸው የነበረውንና በኋላ ግን ነገሩ እውነት ሆኖ የቀበሮ መንጋ በጎቹን ሲገነጣጥልለት ቢጮህ የሚደርስለት ያጣውን እረኛ የማያስታውስ በተለይ ምራቅ የዋጠ ዜጋ አይኖርም፡፡

የአቢይ አህመድን ሀሰተኛ ነቢይነት በተመለከተ ብዙ ተብሏልና አሁን አላነሳም፡፡ ሰሞኑንም አንድ ታዛቢ እነዚህን የመሪያችንን ቱሪናፋዎች ሰብሰብ አድርጎ ኢትዮሪፈረንስ ድረገጽ ላይ አውጥቷቸዋልና እዚያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡

“ካለበት የተጋባበት” እንዲሉ በትናንትናው ዕለት ከንቲባዋ ተናገረችው የተባለው የአምስት ዓመት ዕቅድ ግን በአስፈጋጊነቱ ወደር የለውምና በርሱ ላይ ትንሽ ማለት ወደድኩ፡፡ ይህ የአክራሪ ኦሮሞዎች አገዛዝ ሥርዓት ልክ እንደቀደመው የወያኔዎች አገዛዝ ሁሉ ኅልውናው የቆመው በውሸት ወሬና በሀሰት መረጃ ላይ ነው፡፡

“በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የአዲስ አበባን ሥራ አጥ ቁጥር ዜሮ እናደርጋለን፡፡” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡፡

በዚህ ንግርት ማለቴ ንግግር ያልሳቀ ምንም ነገር ሊያስቀው አይችልም፡፡ ይህን መሰል ዕቅድ አደጉ የተባሉ ሀገሮችም አያደርጉትም፤ ለሆነ  ስህተት የሆነ ቀዳዳ ወይም ክፍተት ይተዋሉ፡፡ ማይምነትና ድንቁርና ግን እስከዚህ ድፍረት ይሰጣል፡፡ ከዜሮ በፊት እኮ ብዙ አማራጭ ቁጥሮች ነበሩ፡፡ በሲሦ፣ በሩብ፣ በግምሽ … የሚባል ነገርም አሉ፡፡ ተንደርድሮ ግን ዜሮ አስገባለሁ ማለት ዕብደት ነው፡፡ ውሸት መልክና ልክ አለው፡፡ ግን  በውሸታምነትና በቆርጦ-ቀጥልነት ከአለቃው ምንዝሩ እያስከነዳ የመሄዱ ምሥጢር አልገባህ ብሎኛል፡፡ የአንድ ዘመን መሪዎች በሥነ ቃል እንደሚነገረው ልክ እንደባልና ሚስት ሁሉ ከአንድ ምንጭ የሚቀዱ ናቸው ማለት ይሆን?

የውሸት አስተማሪ አባቷ አቢይ በዚያ ሰሞን ከአምስት ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሉንና ይህም መጠን ዓለም በአንድ ዓመት ከምታጣው አንድ ሦስተኛውን እንደሆነ ቅንጣት ሳያፍር ተናግሯል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በየትኛው ጥናቱ እንዳረጋገጠው ባላውቅም ያን ያህል መጠን ያለው ችግኝ አሜሪካም ሆነች ቻይና እንዳልተከሉ ገልፆኣል፡፡ አዎ፣ ውሸትንና ቅራሪን ጭልጥ ነው፡፡ አቢይ የሚያፍረው እውነትን ቢናገር ነው፡፡ በስህተት እውነትን ቢናገር የሚያቅረው ይመስለኛል፡፡

አሁን የኔ ፍራቻ – እነዚህ አቢያውያን ሳት ብሏቸው እውነት ቢናገሩ ማን ያምናቸው ይሆን? ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡

የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ብአዴን አማራን አጋድሞ እያረደው ነው፡፡ ብአዴን በሠርጎ ገቦች እንጂ በአማራ የሚመራ ድርጅት አይደለም፡፡ በዚያ ውስጥ ያላችሁ አማራ ነን የምትሉ ምንም መልካም ነገር ለሀገር መሥራት ካልቻላችሁ በቶሎ ራሳችሁን ለዩ፤ ግለ-ታሪካችሁንም ከውርደት አድኑ፡፡ በዚህ ወንጀለኛ ድርጅት ውስጥ ሆናችሁ በኋላ ማቄን ጨርቄን ብትሉ ታሪክ አይሰማችሁም፡፡ “እንዲህ ላደርግ ብል እንዲህ ተብዬ፤ እንዲህ ላደርግ ስል እንዲህ ሆኖብኝ…” ማለቱ አያዋጣምና አሁኑኑ ከዚህ ወንጀለኛ ድርጅት፣ ከዚህ የከሃዲዎች ስብስብ፣ ከዚህ የድኩማንና የሆዳሞች ጥርቅም፣ ከዚህ የኦህዲድና የወያኔ ተላላኪ ወንጀለኛ ተቋም በአፋጣኝ ውጡ፡፡ ላስቲክ ሆዳችሁ በልቶ አይጠረቃምና ለሆዳችሁ ስትሉ አማራን እያስፈጃችሁ ያላችሁ የብአዴን አባላት ዛሬውኑ ተመለሱ፡፡ ነገ ጊዜ ላይራችሁ ስለሚችል አሁንን ተጠቀሙባት!

ፀረ አማራውን ሽመልስ አብዲሣን ባህር ዳር ወስዶ መሸለም ምን ይባላል? በመተከልና በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የሚያልቁ አማሮችን ዜና እንኳን እንዳይዘገብ መከልከል ምን ይባላል? አማራና ኦርቶዶክስን ለመፍጀት አራት ኪሎ ለተሰየመ የሰይጣን መንግሥት አድሮ ሕዝብን መፍጀት የዞረ ድምሩ ምን ሊሆን እንደሚችል መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ አልኩ ለማለት አልኩ እንጂ ክፉ ዐመል ካላስገደለ እንደማይለቅ አጥቼው አይደለም፡፡ መልምም የጭንቅ ዘመን ያድርግን!

Filed in: Amharic