>

እነ እስክንድርን "በሽብርተኝነት" መክሰስ...!!! (መስከረም አበራ)

 እነ እስክንድርን “በሽብርተኝነት” መክሰስ…!!!

መስከረም አበራ

* በዓለማችን ብዙ አይነት አንባገነኖች ተከስተዋል – የአብይ ግን ለየት ይላል….!!! 
* የነ እስክንድርን ክስ አነበብኩት።  ለጃዋር ጓደኛ የመፈለግ ስልጣን አይዞህ ያለው መባዘን እንደሆነ ሞኝ ያልሆነ ሁሉ የሚያውቀው ነው!!!
 የሞጣ ስም የተጠቀሰበት ቦታ ብዛት እስክንድርን ከሞጣው መስጊድ ቃጠሎ ጋርም ለማነካካት ያሰበ እኩይነት በውስጡ አዝሏል።
 ትግሬና የኦሮሞን የለየ የብሄር ጥቃት የሚለው ኦሮሚያ ለተደረገው ዘር ተኮር ጥቃት ከሌላ ቦታ ተመሳሳዩን ያደረገ ጓደኛ ፍለጋ መላላጥ ነው። በጣም የሚገርመው የጋሞ ወጣቶችን ለማነካካት የተደረገው መላላጥ ነው።
 ባጠቃላይ የክሱ መንፈስ የጃዋር/በቀለን የክስ መዝገብ ከእስክንድር/ስንታየሁ የክስመዝገብ ጋር መሳ የሆነ የወንጀል ክብደት መስጠትና የሁለቱን እጣ ፋንታ አቆራኝቶ ማሰር ነው።
 ከዛስ? ከዛማ “ሁለቱን እኩል ሚዛን ወንጀለኞችን” “በማያዳላው” መንግስታዊ ይቅርባይነት  ፈታናቸው ምስጋናም ይገባናል የሚል ዜማ ይከተላል። ይሄው ነው!
 የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም ያውቃል ግን ሁሌም ገዥወች ማንኛውንም ነገር የሚለኩት በእርሳቸው ሀሳብ እና በካድሪዎቻቸው እውቀት ልክ ስለሆነ መውረዳቸው ሁሉ ከፍታ ይመስላቸዋል ።
በዓለማችን ብዙ አይነት አንባገነኖች ተከስተዋል!የአብይ ግን ለየት ትላለች! ሕዝብን እንዴት አታሎና አምታቶ መግዛት እንደሚቻለው በአንድ ጊዜ በሆነ ቦታ ያነበበ ጥራዝ ነጠቅ ያስመስለዋል! አንብቦ ሊሆን ይችላል የማኪቬሊ ፍልስፍና ግን በወጉ አልገባውም!። ልክ እንደ ሰባዎቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተማምቶበታል ማለቱ ይቀላል መሰለኝ።
Filed in: Amharic