>
5:13 pm - Sunday April 19, 8285

ይቅርታ ማለት ይህ ነው  ! (ሀብታሙ አያሌው)

ይቅርታ ማለት ይህ ነው  !

ሀብታሙ አያሌው

ለሊቱን ሁሉ አልጋየን በእንባ አጥባለሁ 
( አለቅሳለሁ )  በዕንባዬ መኝታየን አርሳለሁ ።” /መዝ 6*6/
ይህ ከጸጸትና ለመመለስ ከመጓጓት የመነጨ የዳዊት የንስሐ እንባ ነው ። የሚያነባው ከኃጢአቱ ነጽቶ አዲስ ሰው ስለመሆኑ ነበር ። መልሰኝ እጠበኝ እያለ ወደ ጌታ ጮኸ…
         “አቤቱ እንደቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደምህረትህም  ብዛት መተላለፌን ደምስስ ። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና …./
           መዝ 50/
✍ ነገር ግን ዛሬ እውነተኛው መንገድ ሳይገባቸው ትክክለኛውን ጸጸት ሳያውቁት መሳሳታቸውንም ሳያምኑ በልማድ ብቻ ንስሐ ንስሐ የሚሉ ብዙዎች ናቸው ። በቅድሚያ በኃጢአት ካላፈርንበት በበደላችን ካልተጸጸትንበት ቀጣዩ መንገድ አይቀናም ።
ደግሞም ከልብ ያልመነጨ በቃል ደረጃ ብቻ የተነገረ ከንቱ ፌዝ ይሆናል ። አንተ ግን የትናንትና ሥራህን መለስ ብለህ ስታስተውል በሚሰማህ ከውስጥህ በሚመነጨው እውነተኛ ጸጸት የንስሐ መንገድን ጀምር ።
ከጸጸት ጋር የነገን ሕይወት የመቀየር ቁርጠኝነትም ከአንተ ይጠበቃል ። ለንስሐ የሚያስፈልገው ጸጸት   የትናንቱን ሕይወት_እየረገሙ_ለመኖር_ብቻ_ሳይሆን ነገን በተሻለ መሰረት ላይ ጥሎ ከጌታ ጋር ለመኖር የሚያስችል መሆን አለበት ።
☞ ንስሐ ያለፈውን የኃጢአት ክንብንብ ማውለቂያና ወደ ኃጢአት የሚያመሩ ምዕራፎችን ሁሉ መዝጊያ ነው ። ምክንያቱም ንስሐ አንድ ያላዋጣን ኮንትራት መዝጋትና ሌላን ደግሞ እንደሞመከር ያለ ሳይሆን ያለውን ሁሉ ጥሎ አዲስ ሕይወት መጀመር ነው ።
ከኃጢአት ጋር የተገናኝ የትኛውም ውል ይፈርስበታል ። ከእግዚአብሔር ጋር የሚለያይ የጸብ ግርግዳ ነውና በንስሓ ይፈራርሳል ። በንስሐ በመመለሥ ዳግም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የእግዚአብሔር ቤት መሆን እነዴት ደስ  ያሰኛል ።
ንስሓ የአንተና የካህን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን የአንተና የእግዚአብሔር ግንኙነት ዳግም መታደስ እንደሆነም ተረዳ። ኢያሱ አካንን ይናገረው የነበረውን ነገር ተመልከት ።
             “ኢያሱ አካንን ፦ ልጄ ሆይ ለእስራኤል አምላክ
              ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ ለእረሱም ተናዘዝ
              ያደረከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው ።”
              ኢያ, ም 7 ቁ .19
የሥርየት ኃጢአት በካህኑ አንደበት ከእግዚአብሔር ታገኛለህ ። ከንሰሓ አባትህ ጋር ስለ ኃጢአትህ ብሎም በንስሐ ሥለመመለስህ ስትነጋገር እግዚአብሔርም በዚያ አለ ። አንድ ነገር ልብ በል ። በአጠገብህ እግዚአብሔር እንዳለ ዘንግተህ ኃጢአትህን ሸሽገህ ከፊሉን ብቻ ብትናዘዝ ልታገኝ የምትችለው ትልቅ ዋጋ እንዳመለጠህና አሁንም ክፋ ነቀርሳ በውስጥህ ተቀብሮ እንደቀረ አትርሳ ።
እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ መጽ ኢያ.1
ምንጭ ከብጹዕነታቸው ከአቡነ ሺኖዳ ፫
Filed in: Amharic