>

" ጉ ራ  ብ  ቻ " . . .  — ዘረኝነት ዘረኝነትን ሊያጠፋ አይችልም ! (አሰፋ ሀይሉ)

” ጉ ራ  ብ  ቻ ” . . . 

— ዘረኝነት ዘረኝነትን ሊያጠፋ አይችልም !

አሰፋ ሀይሉ

“የተማረ ሆኖ – እውነቱን የማይገልጥ
ባለ ጸጋ ሆኖ – ገንዘቡን የማይሰጥ
ደሃ ሆኖ መስራት – የማይሻ ልቡ
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች
ለምንም አይረቡ።”
  (- ክቡር ከበደ ሚካኤል፣ የዕውቀት ብልጭታ)
ዘረኝነት ዘረኝነትን ሊያጠፋ አይችልም፡፡ የኦሮሙማዎቹ ዘረኞች – የአማራዎቹን እንከፎች ከጎናቸው አሰልፈው – የትግሬዎቹን ዘረኞች እንዋጋለን ስላሉ – በኢትዮጵያ ሠማይ ሥር የሚቀነስ ዘረኝነት የለም! በጭፍን ጥላቻቸውና በዘረኝነታቸው ወያኔን በሺህ እጥፍ የሚያስከነዱት የቄሮው ዘረኞች – በወያኔ ላይ ጦርነት ቢያውጁ ባያውጁ አንዱ ከሌላው የሚሻሉ ሆነው መቅረብ አይችሉም፡፡ ጦርነት – ሁሉም ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ፀጉራቸው በዘረኝነት የተነከሩ ጥልቅ ኋላቀር ኃይሎች የመሆናቸውን ሀቅ ሊያስቀረው አይችልም፡፡
ለኦሮሙማው የዘር የበላይነት አጀንዳ ትልቅ ሥጋት የጣለባቸውን ተቀናቃኛቸውን ወያኔን ለማዳፈን ከፈለጉ – ልክ ወያኔ ደጋግማ እንዳደረገችው – ኦሮሙማዎቹም የራሳቸውን ያደራጁትን የኦሮሙማ ጦር አዝምተው – ተረኛ አሸናፊ ዘረኞች መሆናቸውን በማያወላዳ ቋንቋ ሊያሳዩን ይገባል፡፡ እንጂ – እንደለመዱት በኢትዮጵያ ሕዝብና በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ተጠቅመው – ጠባቡን የኦሮሙማ ዕቅዳቸውን ሊያሳኩ ሲነሱ እጁን አጣጥፎ ጭዳ በሬ የሚሆንላቸው ህዝብ ከዚህ በፊት እንደለመዱት በቀላሉ የሚያገኙ አይመስለኝም!!
“አስከበረን ስንል – ሀገሬ ተዋርዶ
በየቀኑ ሀዘን – ዕለት ዕለት መርዶ
በሜንጫና ጥይት – ሰርክ እየቀነሰው
ስንት ቀርቶ ይሆን – ከተደመረው ሰው፡፡”
  (- ገጣሚ ሙሉቀን ሰ.፣ እኩል ይሆናል)
የሶማሌ ተቀናቃኛቸውን – በአብዲ ኢሌ ስም – በኢትዮጵያ ጦርሠራዊት አማካይነት ድባቅ የመቱት የኦሮሙማ ኃይሎች – የጌዲኦ ተቀናቃኞቻቸውን በኢትዮጵያ ጦርሠራዊት እያዘመቱ የመቱት ኦሮሙማዎች – የአማራን ተቀናቃኛቸውን በአሳምነው ጽጌ ስም በእንከፎቹ እየተመሩ ባህርዳር ላይ ጉብ ብለው በኢትዮጵያ ጦርሠራዊት ያስመቱት ኦሮሙማዎች – አሁን ደሞ ትልቅ ተቀናቃኝ የሆነባቸውን የትግራይ ወያኔ ኃይል – ዳግም በኢትዮጵያውያን አንጡረ ሀብት የተገነባውንና የሚተዳደረውን ጦርሠራዊት ተጠቅመው ለማዳፈን ቢነሱ – የቱን ያህል ዓላማችን ይሰምርልናል ብለው እንደሚያስቡ አይገባኝም? ከራሳቸው ቱልቱላዎች ውጪ – ለተረኛ ዘረኞቹ ወግኖ – ሌሎችን ዘረኞች ሊዋጋ የሚወጣላቸውስ ሰው ያገኛሉ ወይ ለመሆኑ?
የትኛው ዘረኛ ቢያሸንፍስ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘረኝነት ጣጣ ነፃ ሊሆን የሚበቃው? ጦርኃይሉን የኦሮሙማውን ተቀናቃኞች ማዳፈኛ መሣሪያ ማድረጉንስ እስከመቼ ይቀጥሉበትና፣ እስከምን ጊዜ ድረስስ ይህ መንገድ ያዋጣቸው ይሆን? ጦርሠራዊቱ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ ንብረት ነው? ወይስ የተረኞቹ ኦሮሙማዎች መጫወቻና ተቀናቃኞቻቸውን ማዳፈኛ መሣሪያ? ይህ የተበላበት ብልጠት ሁሌ ይቻላል ወይ? ጦርኃይሉ የኦሮሙማ አጀንዳ አስጠባቂ እንዲሆንላቸው ከአናቱ ላይ በተሾሙ ጥቂት የኦሮሙማው ጦር-አዛዦችስ አማካይነት – ሁሌ ለጠባቡ አጀንዳችን ስትል ሂድና ተዋደቅ፣ ሂድና ተዋጋ፣ ሂድና ሙት፣ ሂድና እነ እገሌን ምታ – እየተባለ ለሁልጊዜውም ያለምንም ማንገራገር ‹‹ሳይጠሩት አቤት? ሳይልኩት ወዴት?›› እያለ ሰጥ ለጥ ብሎ ቁማራቸውን እውን ለማድረግ ይታዘዝላቸዋል ወይ ለመሆኑ? ይሳካላቸዋልስ ወይ ሁሌ? አንድዬ ይወቅ፡፡ አይመስለኝም ግን፡፡
“መርዝም መድሃኒት ነው ሲሆን በጠብታ
እንዲሁም ለተንኮል አለው ቦታ ቦታ
ምን ቢሰለጥኑ ቢራቀቁ በጣም
ሁልጊዜ ደጋግሞ ብልጠት አያዋጣም።
በጅ የተበተቡት ተንኮል ዞሮ ዞሮ
ማጋለጡ አይቀር እጅና እግር አስሮ ።
መጽሓፉም ይለናል ሲያስተምረን ጥበብ
ብልጥ ሁን እንደባብ የዋህ ሁን እንደርግብ
ስለዚህ በብልጠት ተንኮል ስትሰሩ
በዝቶ እንዳይገላችሁ ገርነት ጨምሩ …”
  (- ክቡር ከበደ ሚካኤል፣ የቅኔ ውበት)
የኦሮሙማው ኃይሎች – የፌዴሬሽን ምክርቤት፣ የተወካዮች ምክርቤት፣ የብልጽግና ምክርቤት፣ የምናምን ምክርቤት እያሉ – የኢትዮጵያ ህዝብ በደሙ ወያኔን እንዲወጋላቸውና – ወያኔ ድባቅ ስትመታ – ያለተቀናቃኝ የኦሮሙማ ቁማራቸውን በልተው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተረኛ ዘረኞች ሆነው ለመንገሥ ያደረባቸው ከንቱ ምኞት – እስከምን ድረስ ያስኬዳቸው ይሆን? ወያኔ ለሥልጣኗ ያሰጋትን ኦነግን ድባቅ እንደመታችው፣ ወያኔ ለዘረኝነት አጀንዳዋ ያሰጋትን ኢህአፓን በአሲምባ እንደቀበረችው፣ ኦሮሙማዎቹና ዳግማዊ ኦነጎቹስ ለምን በመቶ ሺህዎች ያደራጁትን የራሳቸውን የወደፊቷ ኦሮሚያ ነፃ አውጪ የኦሮሙማ ጦር አንቀሳቅሰው አዝምተው – ተቀናቃኝ ሆና ያስቸገረቻቸውን ወያኔን ለምን ወደ መቃብሯ አይሸኟትም? እና የበላይነታቸውን አያረጋግጡም?
የሽብር ዓላማቸውን በሀገር ላይ ለመንዛት – በጎን ንፁሃንን እያረዱና እያሳረዱ ያሉት ኦሮሙማዎቹ – ተረኛ ዘረኝነታቸውን አልቀበል ላልነው ለሁላችንም ኢትዮጵያውያን – ተረኛ ገዢዎች መሆናቸውን አምነን ፀጥ ለጥ ብለን እንድንገዛላቸው – ለምን በራሳቸው የኦሮሙማ ኃይል ተጠቅመው – ወያኔ ድሮ ኦንግን ድባቅ መትታ እንዳሳየችን – በተግባር ወያኔን ድባቅ መትተው አያሳዩንም? ወይስ በሌላው የኢትዮጵያ ልጅ ደምና አጥንት ነው የቋመጡለትን የኦሮሙማ መንግሥታቸውን በኢትዮጵያ ለመትከል ያቀዱት? የመጨረሻው ምኞታቸውና ቁማራቸው ይህ ከሆነ – በእውነት የመጨረሻዎቹ ጅሎች አይደሉም ብሎ – ከልቡ የሚከራከር ጤነኛ ሰው ይገኛል ብዬ አላስብም፡፡ ይሄ ይሆን ወይ የመካከለኛ ጊዜ ቁማራቸው ለመሆኑ?
ለመሆኑ እውነት እንነጋገር ከተባለ – በሀገር አማን አንድ ተኩስ እንኳ ባልተሰማበት ሜዳ ላይ ‹‹ነፍሴ አውጭኝ›› ብሎ ሣሩን እየነሰነሰ – በቢሾፍቱ እሬቻ ወደ ገደልና ጢሻ እየሮጠ ተሰባብሮ ያለቀ ፈሪ የፈሪ መንጋ – በምን ተዓምር እና በምን ልቡ ይሆን – አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ ሰሜን አቅጣጫ ተጉዞ – ከወያኔ ጋር ጦርነት የሚገጥመው? የአድዋን ተጓዦች እያጣጣሉ – የአድዋን ታሪክ እያፈራረሱ – የአድዋን ጉዞ ለመድገም፣ የአድዋን ድል ለመድገም ማለም – ከንቱ የቁም ቅዠት አይደለም ወይ ለመሆኑ? ወይስ ቢሾፍቱ ላይ ቁጭ ብለው – በአናት በሾሟቸው የኦሮሙማ አዛዦች አማካይነት የኢትዮጵያን አየር ኃይል ወደ ሰሜን ሰድደው ወያኔን ሊያስደበድቡ አስበው ይሆን? . . .
ወይስ . . . የኢትዮጵያን ህዝብ ‹‹ና ተዋጋልን!›› ብለው ለጠባቡ የኦሮሙማ አጀንዳቸው ስኬት ዳጣ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል? ወይስ በብአዴን እንከፎቻችን ታግዘን – በወያኔ ላይ የቆየ ቂሙን ቆስቁሰን – የፈረደበትን የአማራውን ህዝብ እና የአማራውን ልጅ – የጦርነት እሳት ውስጥ አስገብተን እንማግደዋለን – ብለው አስበዋል? እንደዚህ ካሰቡ መቼም – በእውነቱ ጅል ዓይነደረቅ ዘረኞች ብቻ ሳይሆኑ – ከጅልም የባሱ ዘረኛ ደናቁርት ቁማርተኞች ሆነዋል ማለት ነው! . . .
እንዲህ የሚሉና ሌሎች ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ሃሳቦች – ደግመው ደጋግመው በሃሳቤ ገዝፈው ተመላለሱብኝ ይሄን ሰሞን፡፡ ብልጠት ሲበዛ ከእንቆቆም በላይ ይመራል፡፡ ብልጠትም ዓይነደረቅነትም ልክ አለው፡፡ የኦሮሙማዎቹ ‹‹ጨፍኑ-እናሞኛችሁ›› ውሎ እያደር ዓይን ጎልጉሎ እያወጣ እያየነው ነው፡፡ ደምና አጥንታችንን ለኦሮሙማው አጀንዳ ገብረናል፡፡ ከአሁን በኋላም በወያኔ ስም የኦሮሙማውን ተቀናቃኝ ለማጥፋት ሲባል – የኢትዮጵያ ህዝብ ደምና አጥንት የሚገበርበት ታሪክ የሚያበቃበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡
እንደማስበው – ብዙ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን – ከወያኔ የምንጠላው መለመላ አካሉን፣ ዘሩን፣ ማንነቱን አይደለም፡፡ ሌላ ቀርቶ የቆረበበትን ኮሙኒስትነቱንና ዝርፊያውንም አይደለም፡፡ ከምንም በላይ ከወያኔ ላይ አጥብቀን የምንጠላው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የረጨውን አስፀያፊ ዘረኝነቱን ነው፡፡ አዕምሯቸውን የደፈነባቸውን የዘረኝነት ሞራ ገፍፈው በትክክል የወደፊቱን ማየት የሚችሉ የትግራይ ልሂቃን ራሱ – ወያኔ በኢትዮጵያ ምድር የዘራችው ዘረኝነት – ውሎ አድሮ ወደፊት እንደ ድንጋዩ በዚያው በትግራይ በረሃ ላይ አድርቆ የሚያስቀራቸው ከማንም በፊትና በላይ ራሳቸውን የትግራይን የወደፊት ህዝቦች እንደሆነ አሳምረው ማየትና ማሰብ እንደማያቅታቸው – እርግጠኛ ነኝ፡፡
ከወያኔ ላይ ዘረኝነትን አጥብቀን የምንጠላው – ትግራዮችን ስለምንጠላ አይደለም፡፡ ትግራዮችም ወንድሞቻችን ስለሆኑ – የነገው ዓለም፣ የነገዋ ኢትዮጵያ ለሁላችንም እንድትበጀን በማለም ነው፡፡ እና ከወያኔ ነገሮች ሁሉ እጅግ አስፀያፊውም፣ አውዳሚውም ነገር የወያኔ ዘረኝነት ነው፡፡ የኦሮሙማው ተረኞች ደሞ – ይሄን በወያኔ የተረጨላቸውን የዘረኝነት መርዝ – ከወያኔ ከራሱ በላይ ማሰቢያቸውን እስኪነጥቃቸውና ንፁሃንን ከመሬት እየተነሱ እስኪያስጨፈጭፋቸው ድረስ – ለአርባ ዓመታት ተግተውታል፡፡ የኦሮሙማዎቹ ዘረኞች – የዘረኝነትን ክፉ መርዝ ተግተው ተግተው ኖረው – አሁን በዘረኝነታቸው የወያኔን ዘረኞች ራሱ የሚያስቀኑ ቀንድ ያበቀሉ ፊታውራሪ ዘረኞች ሆነዋል፡፡
እና የወያኔውን ጊዜ-ያለፈበት ዘረኛ – በአዲስ በጥላቻ በታወሩ እና ከወያኔም በባሱ የኦሮሙማ ዘረኞች ለመተካት ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኦሮሙማው ጋር ተባብሮ ወያኔን ሊወጋ የሚነሣው? ይህ – የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ አብሾ ጠጥቶ በቁሙ እንዲሰክር ካልተደረገ በስተቀር – ንክች የማያደርገው የዓለም የመጨረሻው ነፈዝ እንኳ በጅልነት ሊነዳበት የማይችል የኦሮሙማው ቁማርተኞች ምኞት የወለደው ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ ይህ – በሥልጣን ሰመመን የወደቁት – እና ዘወትር በሌሎች ደምና በሌሎች ኪሣራ የሥልጣን ቁማራቸውን እየበሉ የመገንጠል ጉዟቸውን ፍጻሜ ላይ ለማድረስ የሚመኙት – የቄሮው ኦሮሙማ ኃይሎች – የህልም እንጀራ ነው!
ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይሆናል፡፡ አሁን አሁንስ በቃ የወሬ ጎተራ ሆነን ቀረን፡፡ በግርግር ሥልጣን ተይዞ ሀገሩ የወሬ ፋብሪካ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ወሬ፣ ነገ ወሬ፡፡ ወሬ ደከመን፡፡ ወሬ ጠላን፡፡ ጉራ ተረፈን፡፡ ጉራ ብቻ፡፡
“አልደክምም ቃሌ ነው – እያልኩኝ ፎክሬ
ያንን ጉራ ሁላ – ቀን አራደው ዛሬ
ያን ጉራ ሁላ – ጉራ ሁላ
ያን ጉራ ሁላ – ትታ ነፍሴ
ወኔዬ ከዳኝ – ወንድነቴ
ወድቆ ጨነቀኝ – ኩራቴ!
“የጠዋት ሃሳብ ጤዛ – ነው ሲነጋ ረጋፊ
ወትሮም በአፍ ይፈጥናል – ቀድሞ ተሸናፊ
ላያድን ቃል ብቻ
ምን ያደርጋል ዛቻ
ጉራ ብቻ!
“ስልቻ ቀልቀሎ – ቀልቀሎ ስልቻ
ቦታ ቢለዋወጥ – ወጥ ላያጥም ጉልቻ
ልቤ ዛሬም ወደህ – ልትሆን መተረቻ
ታዲያ ምን አመጣው – ያንን ሁሉ ዛቻ
ጉራ ብቻ!
“ታላቅና ታናሽ – ምላስ እና ሰምበር
ያስገምታል ሥጋ – ሞቶ ለሚቀበር
ወርቅ የዘጋው ሳጥን-  ቁልፍ የሌለው መፍቻ
ምን ያደርጋል ወድቀው – አለሁ ማለት ብቻ
ጉራ ብቻ!”
  (- ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን፣ ጉራ ብቻ)
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ! ፈጣሪ እንደሚበጀን ያበጃጀን! የሚበጀውን ያምጣልን!
ኢትዮጵያ በጥፍራቸው ከያዟት ዘረኞች አገዛዝ ተላቃ – ለዘለዓለም በፍቅር ትኑር!
“ጊዜ ሰጥቶን ሁሉን ለማየት ያብቃን” – የስንብት ቃሌ ነው!
Filed in: Amharic