>
5:13 pm - Thursday April 20, 3415

"የቀን ጅቦች" ....በቀንና ለሊት ጅቦች ሲተኩ....!!! (መርእድ እስጢፋኖስ)

“የቀን ጅቦች” ….በቀንና ለሊት ጅቦች ሲተኩ….!!!

መርእድ እስጢፋኖስ

I was born by the river in a little tent
O,just like a river,i’ve been running ever since
It’s been a long time coming
But i know a change’s gonna come,oh,yes it will

ይህ ዘፈን ሲሰማ በብዙ አሜሪካውያን ዘንድ ቶሎ ወደ አይምሮቸው የሚመጣው ዶ/ር ማርትን ሉተር ኪንግ ናቸው።ሪቨራን ማርትን ሉተር ኪንግ ለአሜሪካውያን ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ብቻ ሳይሆን አረአያነታቸው ለመላ አለም የጥቁር ህዝቦች ጭምር ነው ማለት ይቻላል። ድ/ር ኪንግ በዛን ዘመን ባይመጡ ኖር ደቡብ አፍሪካዎችም ማንዴላን ባላገኙ ነበር።
1950 መጨረሻ ና60 ቹ መጀመሪያ በመላው አለም የነጻነት ትግል የተጀመረበት ወቅት ነበር።አብዛኛዎቹ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ሲሆን የታገሉት እንደ usa አይነት ሀገር ደግሞ ከዘር መድሎ ለመላቀቅ ነበር።በተመሳሳይ ወቅት ሌላ ታዋቂ የነጻነት ታጋይ ነበረ።ማልኮም ኤክስ የተባለ ።በእድሜ ከዶ/ር ኪንግ ያንሳል።በትግል ስልልትም ማልኮም ፈጽሞ ይለያል።ማልኮም የዘረኝነት ትግሉ tit for tat ወይም ነጻነትን በሀይል እና በጉልበት መውሰድ የሚል ነው።
ድ/ር ኪንግ በሰላማዊ ትግል ብቻ የሚል ነው።የኪንግ መነሻና ምርድረሻ ሰውነት እና እግዜብሄር ሲሆን ።ማልኮሜክስ ግን ሶሻሊዝምና የቆዳ ቀለም ነበረ።
ሪቨራን ማርትን ሉተር ኪንግ ፦ሰው ሁሉ በፈጣሪ ዘንድ እኩል ነው። በሀገራችንም ከነጭ እኩል ልንቆጠር ና ልንከበር ይገባል ይሉ ነበር። እኩል ተጠቃሚ መሆን አለብን በማለት ይከራከራሉ።ሉተር ኪንግ ዘንድ ፈጣሪ ነጭም ጥቁርም አልነበረም።
  ማልኮሜክስ ፈጣሪ ነጭ አርጎ ካማሰቡ የተነሳ አላህን ፍለጋ ወደ ሳውዲ ዘልቆ ሁሉ ነበር። እስላም ከክርስቲያን ይልቅ መለስተኛ ዘረኛ ነው የሚል ሀሳብም ያራምዳል።ስለዚህም ሀይማኖቱን ቀይሯል ።በሌላ መለኩ የካርል ማርክስና የሌንን እኩለነት ጽንሰ ሀሳብንም የደግፍ ነበረ።በጥቅሉ ማልኮሜክስ ለአሚሪካ ጥቁሮች ነጻነት መስዋትነት የከፈለ ሰው ነው። በአሜሪካ ጥቁር ህዝብም ሲታወስ ይኖራል።    ዶ/ር ኪንግ ግን በሁሉም አሜሪካዊ ይከብራሉ። በነጩም።በኔቲቭ አሜርካን በብራውኑም በላቲኑም….ብቻ በሁሉም አይነት(from all walk of life) ይሉታል ፈረንጆቹ።ይከበራሉ።የሁለቱን ታጋዮች ልዩነት ለማስረዳት በቀላሉ ዶ/ር ኪንግ ችግሩንም መፍትሔውንም ያውቃሉ።ማልኮሜክስ ግን ችግሩን ብቻ ነበር የሚውቀው እንደ ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች።
ድ/ር ኪንግ ሰበዊ መብታቸንን ፡ሰው የሰጠን ሳይሆን ከፈጣሪ ነው ።ነጬች ውስጥ ያለ ፍላጎት ጥቁር ላይም አለ። ሰው በቀለሙ ሳይሆን በባህሪውና በስራው ይለካ ።ዛሬ ሀያል የሆነ ነግ ይደክማል ዛሬ ገዥየሆነ ነገ ይገዛል።ዛሪ ብርቱ የሆነ ነገ ልፍስፍስ ይሆናል ስለዚህም ያ ቀን መጥቶ የተራ ጉዳይ እንዳይሆን ዛሬ ወንድሞቻችን ነጮች ከጎናችን ቁሙ።ለነጻነትና ለእኩልነት አግዙን የሚል ሰውነት ላይ ያጠነጠነ ጥሪ ያደርጉ ነበረ። በመሆኑም ድምጻቸው ተሰማ። ነጮቹ ለጥቁሮች የመብት ጥያቄ ለመቆም ቻሉ። ማርቲን ሉተር ኪንግ ….”ከነአንን እንደሙሴ አላያት ይሆናል ነገር ግን የተስፋዋ ምድር እንገባለን ይሉ ነበር” ይህ የተስፋ ቃላቸው ተፈጽሞ አሜሪካ የጥቁር ፕሬዝዳት እንድታይ እድል ፈጥሯል።
“Oh,just like a river i’ve been running ever since” .መስከርም 3 ቀን የዛሬ 27 አመት እስክንድር ነጋ ጋር ቀጠሮ ነበረኝ። ቀጠሮችንም አራት ኪሎ በሚገኘው ቤተሰቦቹ ቤት ነበረ። በቀጠሮችን መሰረትም በትክክለኛው  ሰአት ውጭ በራቸው ላይ ቆሞ አገኘነው። ወደ ውስጥ እንድንገባ ጋብዞን ወደሳሎን ዘለቅን ና አረፍ አልን።ሻይ ቡና ተባልን።ወሬም ተጀመረ። በዚያው ዙሪዬን ቅኝት ሳደግ በሳሎን ውስጥ እጅግ ቅልጥፍ ባለችው አነስተኛ የመስታዋት መጽሀፍ መደርደሪያ ላይ የመድሀንያለም ምስል ባንድ በኩል፡በሌላ በኩል የቅድስት ድንግል ማሪያም ምስል ….በምሀል መጽሀፍ ቅዱስ ተቀምጧል።
ከዛ ወረድ ብሎ ባለ መደርደሪያ ላይ ደግሞ የተለያዩ ኢትዮጵያ የታሪክ መጽሀፍት ሲኖሩ በቀጣዩ መደርደሪያ ላይ ግን የዶ/ር ኪንግ የዶ/ር ማንዴላ የጋንዲ መጽሀፍቶች ነበሩ።
አዎ ከዚህም ሌላ ለስላሳ የድሮ የእንግሊዘኛ ሙዚቃም በሥሱ ይሰማል። የሳም ኩክ (change gonna come )ነበር። በተደጋጋሚ ስለ ሰማነው ትኩረቴን ነጠቀኝ። በጣም ይወደዋል ማልት ነው ስል አንሾካሽኩ አብሮኝ ለመጣው ጓደኛዬ።ጉዳያችንን ጨረሰንና ልንወጣ ስንል የዶ/ር ኪንግን መጽሀፍ ብዋስ ብዬ ጠየኩ።” በጣም ይቅርታ አርግልኝ በዚምድር ላይ የማላውሳቸው መጽሀፎች እነዚህ ናቸው”።ሌሎቹን መዋስ ትችላላችሁ አለን በደማቅ ፈገግታ።መጽሀፍ ቅዱሴንም አትችሉም ሲለን በተጨማሪ ተሳሳቅን።በዚሁ ተለያየን።ይህ እንግዲህ በወያኔ ለሁለተኛ ጊዜ ታስሮ በተፈታ 5 ቀኑ ለይ ነው።
እስክንድር ቀጥሎ ቀጥሎ እንደዥረት በትግሉ እይፈሰሰ ነው።ኢትዪጵስ የመጀመሪያዋ ጎህ ቀዳጅ የነጻ ፕሬስ ጋዜጣ።ዘ ሀበሻ እንግሊዘኛ ጋዜጣ፡ ወንጭፍ፡ ምንይልክ ፡አስኳል ሳተናው።የመናገርና የመጻፍ ነጻነት አብዮትን ያወጀ ሰው ነው እስክንድር።
ሁልጊዜ ሳገኘው” ለውጥ ” በደጅ ቆማ የምታንኳኳ ይመስለኛል። በቋንቋና በዘር የተካፋፈለችው ኢትዮጵያ አይኔን ከፍቼ ስገልጥ ብን ብላ ጠፍታ….. “ነጻነት፡እኩልነት፡ብልጽግናን” እሴቷ ያደረገች ኢትዮጵያን ያየሁ የመስለኝና ነብሴ በደስታ ትሞላለች።ግን ደግሞ ሆኖም አያውቅም።አመታት ተቆጠሩ።( chenge gonna come)
ወያኔም አፈር ልሳ እየተነሳች ትግሉም ጥቂቶች መስዋት እየሆኑበት ቀጠለ።እስክንድር ለ7ኛጊዜ ታስሮ እንደተፈታ በሁልተኛ ቀኑ መድሀንያለም በተክርስትያን ተሳልሞ ሲወጣ አገኘሁት ከስቷል ገርጥቷል በዛለይ በወያኔ ድብደባ የተጎዳ ክንዱ ህመሙ ተሰምቶት በስካርፕ ቢጤ ሸብ አርጓታል።
እንደተያየን የተለመደ ደማቅ ፈገግታውን ሳይ ከስር ቤት የውጣ ሳይሆን እዛው መድሀንያለም በተክርስቲያን የኖረ ነው የመሰልኝ። እዚህ ፈገግታውና መንፈሱ ላይ ምን አልባትም የመድሀኔለም እጅ ይኖርበት ይሆን ስል አሰብኩኝ። እንዴት አይነት ጥንካሬ ነው?።እንዴት አይነት አይበገሬነት ነው?።አወራን ከስር ቤት እንደውጣ ሳይሆን በሚወዳት አራዳ ክፍለ ከተማ ሲዘዋወር እንደከረመ አይነት ነበር ስሜቱ።አሁንስ አልኩት የሀገሪቱን ሁኔታ አንስቼ ” ለውጥ ይመጣል “አለኝ። የሁላችንም ኢትዮጵያ ትመጣለች አለኝ።ያቺ የምትናፍቀኝ ህልሜ እንደገና ብቅ አለች፡”ነጻነት፡እኩልነት፡ብልጽግና”ልክ እነደ ማርከስ ዲ ላፋየት በ ፍሬንች ረቮሉሽን እንዳመጧት … ዘመናዊ ሀገር ላ ፍራንስ። ኦ እንዴት ያለ ህልም ይሆን?። ወራቶች አልፍ….
ለስምንተኛ ጊዜ ታስሮ እንደተፈታ አገኘሁት።ይሄ ህይወት መቆሚያው የት ነው ስለው? በቅርቡ በቃ ዲሞክሪሲያዊት ኢትዮጵያ ፡የሁላችንም ሀገር እየመጣች ነው አለኝ(change gonne came).      ሌላውስ ይቅር “እጅህን ብትታከም አልኩት” ፡”አዎ አሁንስ አስቸገረኝ አለኝ”ምን ወሰንክ ታዲያ” ስለው በቃ አሁን የመጪው 2005 ምርጫ ይለፍና እታከማለሁ አለኝ።ለራሱ የሚሆን ጊዜ እንኳ የለውም ይሄ ሰው።”ሁላችንም ለዲሞክሪሲያዊት ኢትዮጵያ ሌት ተቀን መስራት ያለብን ጊዜ ነው አለኝ።
ያን ምሽት እንደገና ያቺ የሁሉም ኢትዮጵያ መጣችብኝ ነብሴ በሀሳብ ሀሴት አደረገች።
አልቀረም 2005 በደጅ ቆማ የምታንኳው ኢትዮጵያ የመጣች መሰለ …በቃ ግንቦት 15/ 2005 በሩን ከፍተን እናስገባታለን ሁላችንም ተሰብስበን እራት አብረን እንበላለን።ብለን ስንጠብቅ በሩ በነ ዶ/ር ብርሀኑ  ተዘግቶ ሳይከፈት ቀረ።
መስከረም 2006 እስክንድር አሁንስ አልኩት በቃ ትግሉ ይቀጥላል አልኝ change is gonna came.ቀጣዩ ከባድ ነበር ።ወራቶች አለፉ ።እስክንድር ለ9ነኛ ጊዜ ወደስር ቤት ተነዳ እናም ወያኔ 18 አመት ፈርደችበት።
2018 እስክድር ከስድስት አመት እስር በኋላ ተለቀቀ።ከእስር በወጣ 7 ወር አገኘሁት”እስኬ አሁንስ? ታከም ለ ቤተሰብም ጊዜ ስጥ ስለው።ከተገናኘንበት ሰአት ጀምሮ የነበርው ፈገግታ ጠፍቶ፡” የሚፈለገው ለውጥ መምጣቱን ገና አላወቅንም አሁንም ለውጡ እንዳይቀለበስ ማገዝ አለብን አልኝ”
ወራት ቆይቼ ከምኖርበት ክፍለ ሀገር ተመልሼ ተገናኘን።አሁን የአገራችን ሁኔታ ችግር ላይ ውድቋል ቄሮ የተባለው የኦሮሞ ስብስብ ንጹሀንን በብራዩ ላይ አርዱ።የጠ/ሚ አብይ መንግስት ምንም እንዳልተፈጠረ ነገሩን ቀልል አድርገው አይቶት አለፈ። (የሚገርመው ግን የትላንቶቹ ኢዜማዎች ድምጽ ማጥፋት ነበር።)
እንዲያውም ይህ ሁኔታ አግባብ አደለም ያሉ የአዲስ አበባ ውጣቶች ጫት በመቃም እና ሺሻ በማጨስ ወንጀል ተለቅመው ውደ ጦላይ ተውስደው ውሉ ያለየለት “መደመር”ሲማሩ ከረሙ በመከራ ና በእናቶቻቸው ጸሎት ተመለሱ።አራጆቹ እና ዘራፊዎቹ ግን ኑሮቸውን ቀጠሉ። ወንጀል ማለት ምን እንደሆነ የማያውቅ እና ለማወቅ የማይፈልግ መንግስት መጣ።ጉድ ነው።
ይህን ተከትሎ” አዲስ አበባን” ራሷን ለመዝረፍ የቄሮ የጎበዝ አለቃ ጀዋር መሀመድ ና በቀለ ገሪባ በግልጽ ቅስቀሳ ጀመሩ ።ይህ ብቻ አይደለም ይሄ አዲስ አባባ ደሴት አይደለችም የሚል ማስፈራሪያ ሁሉ ሰጡ።አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኦህዴድ አዲስ የዘርፋና የሰፈራራ ፕሮግራም በመላ አዲስ አበባ ጀመረ።ቀበሌ አመራርን 75% ወሰደ፥አገር ውስጥ ገቢ ንም፤ ኪርይ ቤቶች፥ ፖሊስና ትራፊክ በሙሉ በሚባል ደርጃ ተቆጣጠረ   በዚህ ጊዜ ነበር እስክንድር በድጋሜ ያገኘሁት። ባለቤቱ እና ልጁን ለማየት ሊሄድ ትኬት መቁረጡን አውቃለሁ።ሻይ ቡና በምንልበት መሀል ጉዞ ወደ አሜሪካ መቼ ነው የምትሄደው? ስለው “ቀርሁ” አለኝ አጭር መልስ ነበር።
የአዲስ አበባ ህዝብ ትልቅ መከራ ላይ ወድቋል አለኝ። በርቀት ወያኔ ያፈረሰችውን የቀድሞ እሪ በከንቱ ባሻ ወልዴን እያየ።change gonne come የሁልጊዜ ተስፋ ስንቅ……እስክንድር
በሳምንቱ “ባልደራሱ ተቈቋመ” አዎ ” long time comming ….”እኔም ወደመጣሁበት ክ/ፍል ክፊለሃገር ተመለስኩ።መንፈቅ ሆነኝ።አ.አ ተመለስኩ ለእስክንድር ስደውል usa መሆኑ ተነገረኝ።የቤተሰቦችን ደስታ አስቤ ደስ ብሎኝ ጨክኜ ደውልኩኝ።አገኘሁት ጠቅላላ ሰላምታ ለቤተሰቡ አቀረብኩ።”በእለቱ ሊመለስ እንደሆነ ነገረኝ “ለምን ?ህክምናውስ ? አከታትዬ ጠይኩ” ይደርሳል”እንደተለመደው”ሁልጊዜ መንገድ ላይ ነው”ፍትህን ፍለጋ ጉዞ ላይ ነው”። “ዛሬ ደግሞ “ሽኝት ስለሆነ ልጁና እናቱ ሰርካለም ፋሲል እንደተርበሹ ነገርኝ።ሰርካለም ትችለዋለች። የሷም አለም ስለሆነ ….ልጁ ግን አሳዘነኝ።
አዎ “ናፍቆቴ”የስክንድር ሀቅ ነው።የእስክንድር የ30 አመታት የህይወት ታሪክ ነው።እንዴት ከባድ ይሆንበት ይሆን?…. ወደዚች ምድር ከመጣ ጀምሮ ህይወት እንደስሙ ናፍቆት ሆናበታለች። አባቱን ጠግቦ የማየት እድል የሌለው ነው።ማየቱም ይቅር በእንደ አሁኑ አይነት አጋጣሚ ድማጹን እንኳ መስማት አይችልም ብርቁ ነው።የ “born crime” መጽሀፍ ታሪክ ይሆንብኛል አንዳንዴ ።በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ጊዜ ከነጭና ጥቁር ያለመገባትም ይሁን ያለመውለድ ህግ ከተላለፉት እናትና አባት የተገኘው የአፍሪካ ኩራት የሆነው የሌት ሽው(late show ) አዘጋጅ ትራቨር ኖሀ ታሪክ ጋር ይመሳሰልብኛል…. የተዋጣለት ተመሳሳይ ባይሆንም ናፍቆቴ…. born crime ነው። በማያቃት አለም ባልሰራው ጥፋት 9 ወር ታስሯል።ናፍቆቴ የዘረኝትነት ሰልባ ነው ገና ሳይፈጠር። አዎ የናፍቆቴ ህይወቱ ናፍቆት ነው።የታጋይ ልጆች እጣፋንታ ተመሳሳይ ነው።የሉተር ኪንግ 4 ልጆች እድል እንደዚ ነበረ።በቂ ጊዜ ከባታቸው አላገኙም።የማንዴላ ልጆችም እንዲሁ ነበሩ። ነገር ግን ታሪክ በዘመናቸው ሁሉ ያባታቸውን ፍቅር እስካሁን እየመገባቸው ነው። አባቶቻቸው።በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆች አባት እንደሆኑ ሲውቁ የዛኔ ገና አባታቸው ለምን ጊዜ እንዳልሰጧቸው በሂደት መረዳት ችለዋል።
ዛሬ እስክንድር ለእስረኛ ጊዜ እንሆ ታሰረ።ቀድሞም “እንዴት ?”የሚለው ሳይሆን “መቼ ” ይታሰራል የሚለው ነበር የቀረው። የኖቤል ተሽላሚው ጠ/ሚ በአዲስ አበባ ምክንያት ጦርነት እንደሚገቡ በ እጅ አዙር ለስክንድር መልክት ሲልኩ ሰንብተዋል።ጠ/ሚ አብይ አዲስ አበባ የሳቸውና የኦሮሞ ነች ባይ ናቸው።ለምን አስፈለገ?
አዲስ አበቦችን እሳቸው ከአጋሮ መተው መብት የላችሁም ሲሉ ትንሽ አልከበዳቸውም።እናም እሳቸውም እንደቀድሞ መንግስቶቻችን።በሴራ ፖለቲካ የአዲስ አበባ ድምጾችን በተፈበረከ ክስ አሰሯቸው።አራጆችን ዘራፊዎችን ገዳዮችን ግን ለምያዝ 2 አመት ፈጀባቸው። እሱም ለይስሙላ ነው።በቅርቡ ለመልቀቅ እይደተዘጋጁ ነው።እንደ አምባሳደር ማይክ ሬነር ከሆነ። አብይ የሚጫወቱት duble standard መቼ እንደሚለቃቸው አልገባንም
እስክንድር የአዲስ አብቤዎች አሁን በለው መንግስት እንደውራሪ የመቆጠራቸው ሁኔታ ነው ለባልደራስ ያበቃው።ጠ/ሚ አብይ ትልቁ አጀንዳቸው አዲስ አበባን አርገው ነው የተነሱት።እወህቶችን የቀን ጁቦች ብለው ሰደቡ።ይህን ባሉ ሁለትኛው ወር አስተዳደራቸው የቀንም የሊሊትም ጅብ ሆነ።የሌሊት ጅብ ደግሞ ምልክት እንኳ አይተውም።ወረራ ዘረፋውና ማስፈራቱ ሲበዛ ነው እስክንድር ለአዲስ አበባ ህዝብ ብቻውን የቆመው።
ኢዜማዎች ዘግይተውም ቢሆን መንቅሳቀሳቸው ደህና ነው።እስከዛሬ የት ነበሩ ?4 ጊዜ ብላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እልቂት ተፈጽሞ አንድ መግልጫ እንኳ አልሰጡም ነበረ።ለምን?
የስልጣን ጥማት ያንበርከካቸው ስለሆኑ ነው።
እስክንድር ፍትህን አፍቃሪ ነው።ይህ ደሞ አስተዳደጉ ግድ ይለዋል።አባቱ የተከበሩ የህግ ባለሞያ ነበሩ። የኢትዮጲያን የህግ ባልሞያዎች ማህበር ከአቶ ተሾመ ገ/ማርያም ቦካን ጋር በመሆን ያቋቋሙ የሩትገርስ ዩንቨርስቲ ምሁር ናቸው። እስክድር ይቤተቦቹ ጡሩ አቅምም በውርስ ደርጃ ቢኖረውም የሱ ፍላጎት አይደለም ።ስልጣንም አይፈልግም። ፍትህን እያየ በማደጉ ለሰፊ ህዝብ ራሱን አሳልፎ የሰጠ የኢትዮጵያ ልጅ እዲሆን ግድ ብሎታል።አንዳንድ የዘመኑ ገዥመደብ ሰዎች ያለባችሁን ብዥታ ላጥራላችሁ ብዬ ነው።ለአማራውም ሲከራከር ቢታይ የዘመኑ ጠባብ ፖለቲከኞች አማራን ሰልባ ሰላደረገ ነው።ነገ ኦሮሞ ሲበደል ቢመለከት እስክንድር ያው ነው አቋሙ ።
[ ] የአዲስ አበባ ህዝብ በራሱ እጅ የራሱን ሻማ ይለኩስ ነው ።ጥያቄው
[ ] የአዲስ አበባ ወጣት ብድርና መደራጀት ተከልክሎ የአማራ ክልል ውጣት የኦሮምያ ክልል ቄሮ የበሉትን 24ቢልን ብር በላይ የIMF ገንዘብ እዳውን ከፋይ አታርጉት ነው።
[ ] ሀጎስም ይምጣ ጨሜሳ የአዲስ አበባ ተውላጅ ያስተዳድር ነው። አዲስ አበባ የሁሉም ብሄር ናት ነው።(ይህን ሲሰሙ ጠ/ሚ ወባቸው ይነሳል) ይላሉ ወስጥ አዋቂ ምንጮ።)
[ ] አዲስ አበባ በራሷ ቻርተር ትተዳደር ነው ሌላው እንደ ነሎንዶን ፓሪስ ናይሮቢ ፕሪቶርያ [ ] የፖልቲካ social engineering ይቁም ነው ተጨማሪ ጥያቄ።የሰፈራ ፕሮጋራም ከአሩሲ ከሀረር ከወለጋና አምቦ እያመጡ አ.አ ማስፈር ይቁም።የአዲስ አበባ ወጣት እንደሌላው ክልል ተደራጅቶ ብድር መሬት ይሰጠው ነው ጥያቄው።ከኢትዮጵያ ስራአጥ ውጣቶች ውስጥ 17 % የእዲስ አበቤዎች ናቸው።የስራ እድል ይፈጠርላቸው ነው።
ትላንት የጨለማ ዘመን ያሉን ጠ/ሚ አዲስ አበባ ለይ አፍጠው ሲሞዳሞዱ አገሪቱ በየአቅጣጫው እየፈረሰች ነው።አትፈርስም ይሉናል ማለዳ ማለዳ።የማያፈርስ ስራ ግን እየሰሩ አይደለም።ስለጨለማው ዘመን በበለጠ ጨለማ መተካቱን ማመን ያስፈልጋል መጀመሪያ ብርሀንን ለመፈለግ።ጠ/ሚ አብይ እንጦጦ አዲስ አበባ የሰሩትን በየቀኑ ቢደግሙብን ምን ዋጋ አለው። የዘረኝነት፥የዲሞክራሲ ፥የፈትህ የእኩልነት ጥያቄ እንጂ መለስ ዜናዊ በስራ የኢትዮጵያን ታሪክ የቀየሩ ናቸው እኮ…….እኛ መለስ ዜናዊ በድለውናል። ጠ/ሚ አብይ ግን እንድንናፍቃቸው ሊያረጉን አይገባም……
. እስክንድርን ከነጃዋር ጋር መታሰሩን የዥን አፍሪክ ታዋቂ ጋዜጠኛ ማጋፉሊ ቻፓንዳ እንዳለው ጠ/ሚ አብይ የመደመር ሳይንሳቸው ከመደበኛው ውጭ መሆኑን ነው። እንዳውም እስክንድር ሂሳብ ማወራረጃና ባላንስ(balance) መጠበቂ አድርገውታል ሲል ይተቻል።ኢትዮጵያ መደመርም ይሁን ምን በትኛውም ሂሳብ የከፋ ሁኔታ ለይ ነች ይለናል። አብይ ዛሬም እስታድየሙ ውስጥ ብቻችውውን የተጫወቱ ነው።ተጫዋች የለም ዳኛ የለም ተመልካችም የለም።just one man play.
አዎ ዛሬም እስክንድርን ባገኘው የሚለኝን አውቀዋለሁ። ለውጥ ይመጣል ነው። ፍትሀዊ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትመጣለች ነው። ታሽንፋለች ነው። change gonne come ,yes it will.” አዎ ተስፋው ይቀጥላል……አምላክ ይጠብቅህ እስክንድር ።
ትንሿ እስክንድር ነኝ
Filed in: Amharic