>

እንዴት ብለህ ጠይቅ - ዋሽተውሃል !  (ኢዮብ መሳፍንት)

እንዴት ብለህ ጠይቅ – ዋሽተውሃል !

 ኢዮብ መሳፍንት

ወዳጄ የነገሩህን ሁሉ ዝም ብለህ አትቀበል፡፡ ጠይቅ፡፡ ለምሳሌ 67,000 ገበሬ ከአዲስ አበባ ተፈናቅሏል ሲሉህ እንደሚከተለው ጠይቅ…
የአዲስ አበባ ጠቅላላ ስፋት 530 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ይህ ማለት 53 ሺ  ሄክታር ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የአንድ ገበሬ አማካኝ ይዞታ 0.9 ሄክታር ነው (ሴንትራል ስታትስቲክስ ኤጀንሲ 1.2 ሄክታር ይላል ትንሹን እንውሰድ ብዬ የፋኦን ዳታ ነው የወሰድኩት)፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባ ሙሉዋን እንኳን ገበሬዎች ብቻ ቢኖሩባት ልትይዝ የምትችለው 58 ሺ ገበሬዎች ብቻ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ 67 ሺ ገበሬዎች ተፈናቅለዋል የሚለው የሀሰት ፈጠራ ነው፡፡ (ልብ በሉ የተባለው አባውራ ገበሬዎች ነው ስለዚህ ቤተሰባቸው ተቆጥሮ ነው የሚል ክርክር ተቀባይነት የለውም)፡፡ ቁጥር አይዋሽም፡፡
ሌላ ልጨምር ለ20 ሺ ገበሬዎች ኮንዶሚኒየም ተሰጥቷል የተባለው እነዚህ ገበሬዎች እውነት ከአዲስ አበባ በኮንዶሚኒየም ግንባታ ምክኒያት የተፈናቀሉ ቢሆን ኮንዶሚኒየሞቹ የከተማዋ 33 % ላይ ነው ያረፉት ማለት ነው፡፡ የከተማዋ 1/3ኛ ኮንዶሚኒየም ቢገነባበት የቤት ችግር ባልኖረብን፡፡ ወዳጄ ይህም ነጭ ውሸት ነው፡፡ በገበሬ ስም ቁማር አትጫወቱ፡፡ ኮንዶሚኒየሞቹን ያደላችሁት ለገበሬዎች አይደለም፡፡
ስለዚህ ልምከርህ ወሬ ሲነግሩህ እንዴት ብለህ ጠይቅ፡፡ የነገሩህን ሁሉ አትቀበል፡፡
Filed in: Amharic