>

ኅሊና የት ገባ! (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

ኅሊና የት ገባ!

 

(ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

 

 

ኢዜማ አምጦ የወለደው መግለጫ አ ሸባሪ ነው፤ የሚደንቀው አንድም የአገዛዙ ባለሥልጣን፣ ጠቅላይ ሚኒሰትሩንም ጨምሮ፣ የጸጸት ወይም የሐዘን መልስ አላሰማም፤ እኔ የቀድሞው ከንቲባ በፈቃዱ ሹመቱን የሚያስረክብ መስሎኝ ነበረ፤ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የተቀናጀ በሚመስል ዘዴ በሌላ ሚኒስቴር በሚኒስትርነት ተሾመ! ይህ አንዱ የአገዛዙ ዓይነ-ደረቅነት ነው፤ ዓይነ-ደረቅነቱን ሲያደርቀው የቀድሞው ከንቲባ በሚያሳፍረው ነገር እንደሚኮራ ነገረን! ምን ትሆናለችሁ እያለን ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የዱሮው ከንቲባ ጉዳዩ በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ በማለት ሀሳብ አላቀረቡም፤ ምናልባት ከኛ በላይ ማን አለ ብለው ይሆናል፤ በሌላ የሕግ ሚዛንና የሕዝብ ድምጽ በሚታወቅበት አገር የቀድሞው ከንቲባ ወይ ራሱን ያሰናብታል፣ ወይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሰናብተዋል፤ የኛ ጠቅላይ ሚኒስትር የምድሩን ጉዳይ ሁሉ እናንተ እንደፈለጋችሁ ብሎ እሱ በሰማይ ላይ ትላልቅ ፎቅ እየሠራልን ነው!

አልጨረስሁም!

Filed in: Amharic