>

ለታከለ ኡማ  እስር ቤት እንጂ ሹመት አይገባውም... (ጌታቸው ሽፈራው)

ለታከለ ኡማ  እስር ቤት እንጂ ሹመት አይገባውም...

ጌታቸው ሽፈራው

~95 ሺህ ቤቶችን እና  214 ሺህ ካሬ ሜትር የአዲስ አበባን ቁልፍ ቦታ ለአንድ ብሔር የሸጠ ወንጀለኛ (ይህ በትንሹ የቀረበ እንጅ የተዘረፈው በእጅጉ የላቀ ነው)
~200 ሚሊዮን ብር ያለ ማንም ተያዥ ለሚፈልጋቸው አካላት የበተነ
~ ዘረፋውን የተቃወሙትን የሕዝብ ልጆች  ሲያሳስር የከረመ
~ ሌብነቱንና ዘረፋውን “ልማትና ብልጽግና” እያሉ ቡራኬ እንዲሰጡ የራሱን አክቲቪስትና የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኞች በሺህዎች የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ እየከፈለ የገጽታ ግንባታ ሲያሠራ የኖረው ታከለ እስር ቤት መግባትና ተጠያቂ መሆን ሲገባው ይበልጥ ወደሚዘርፍበት መሥሪያ ቤት ተዛውሯል። በሌላ ዙር የዘረፋ ተግባር ተሰማርቶ የአገሪቱን የማዕድን ሀብት እንዲዘርፍ ተመድቧል።
ታከለ ኡማ ከሚንስትር ድኤታዋ እና ከዘርፍ ዳይሬክተሩ  ጋር በመሆን የሌብነቱን መንገድ ጀምሮታል። ሦስቱም ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የለየላቸው ኦነጋዊያን ናቸው። በምን የሥራ ታሪካቸው (track record) ነው እነዚህ ሰዎች የዚህችን ድሃ አገር የማዕድንና የነዳጅ ሚኒስቴርን እንዲመሩ የተደረገው?
እነ ታከለ በምን በጎ የኢንቨስትመንት ታሪካቸው ነው ማዕድንና ነዳጅን ያህል ትልቅ ነገር እንዲመሩ የሚደረገው?  ታከለ ይህን ሁሉ ሲሰራ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እያወቁት ነው። ታከለ የነዳጅና ማዕድን ጉዳይ የሚቆጣጠረው እጥረት እንዲፈጥር ነው ወይንስ እንዲያዘርፍና እንዲዘርፍ?
ታከለ ለሰራው ወንጀል እስር ቤት እንጅ የሚዘርፍበት ሌላ ስልጣን አይገባውም።
Filed in: Amharic