>

መስማት የማትፈልገው፣ መናገር የማልፈልገው፣ ግን የግድ መነጋገር ያለብን እውነት! (አሰፋ ሀይሉ)

መስማት የማትፈልገው፣ መናገር የማልፈልገው፣ ግን የግድ መነጋገር ያለብን እውነት!

 
አሰፋ ሀይሉ

 

ምን መሠለህ? የቄሮው መንግሥት ባለጊዜዎች በሙሉ እኮ የሚነሱህ አንድ ቁልፍ ነገር – ለሁሉም ነገርህ፣ ለጤናማ አስተሳሰብህ፣ እሺ ብለህ ሌሎችን ለማድመጥም ለመተባበርም እጅግ አስፈላጊ የሆነውን – ቅ ን ነ ት – የሚባለውን ነገርህን እኮ ነው የሚነሱህ! 
ከዋናው ኖቤል ተሸላሚው ቄሮ ጀምሮ – አንዱ በቅቤ ምላሱ፣ ሌላኛው በጉርሻው፣ ሌላኛው በቁማሩ፣ ሌላኛው በገጀራው፣ ሌላናው በሜንጫና በድንጋዩ – ሁሉም ያለውን ሁሉ መሣሪያ ጨብጦ – የምታያቸው አንተን ጨፍነው ሊላጩህ ሲፍጨረጨሩ እኮ ነው! እጅግ በወረደ ብልጠት – እጅግ በወረደ ሼም የለሽነት ሁሉን ነገርህን ለእኛ እና ለእኛ ለሚሉት አካል ሙልጭ አድርገው ሊወስዱ ሲሽቀዳደሙ እኮ ነው የምታያቸው፡፡ በአራቱም ማዕዘን የምታየውኮ ይሄንን ነው! እና ይሄን ስታይ ነው ‹‹ቅንነትህ›› ከውስጥህ ብን ብሎ የሚጠፋብህ!
ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም፣ ከነገወዲያም ታያቸዋለህ፡፡ ጨፍኑ ላሞኛችኋቸውን ታያለህ፡፡ ሲዘርፉ ሲያዘርፉ ታያለህ፡፡ ሲገድሉ ሲያስገድሉ ታያለህ፡፡ ሲያስሩ ሲያሴሩ ታያለህ፡፡ በየቦታው የዘረኝነት መርዛቸውን ሲረጩ ታያለህ፡፡ በየቦታው ፀረ-ኢትዮጵያዊውን ኃይላቸውን ሲያጠናክሩ፣ ሲያደራጁ፣ ምሰሶና ማገር ሆነው ሲከላከሉ ታያለህ፡፡ ፀረ-ኢትዮጵያዊውን ኃይል በአደባባይ እያደራጁና እያስታጠቁ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለውን ሁሉ ከክልልና ከመንግሥት መዋቅር ውስጥ እያፀዱ፣ እያፈናቀሉ – በፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ በፀረ-ነፍጠኝት፣ እና በዘረኝነት የሰከረ ትውልድና የቄሮ ኃይላቸውን ሲያጠናክሩ፣ ሲያሰባስቡ፣ ትውልዱን በትምህርት ካሪኩለምና በቀበሌ የኦሮሚያ ዜግነት ኮሚቴ ጭምር ሲያዘጋጁ፣ ሲኮተኩቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለሪፈረንደም መንገድ ሲጠርጉ፣ ሌላውም ይህንኑ እንዲያደርግ በእጃዙርም በፊትለፊትም ሲገፋፉና ሲያደፋፍሩ ትመለከታቸዋለህ፡፡ በተግባር ዕለት በዕለት እየሆነ ያለው እውነታ ወደድክም ጠላህም ይሄ መሆኑን ትመለከታለህ፡፡
ይሄንን ባሉበት አፋቸው ደሞ ዓይናቸውን በጨው እጥብ አድርገው – ቆሽትህን አሳርሮ በሽተኛ ሊያደርግህ በሚደርስ የድርቅና ደረጃ – ‹‹ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ›› እያሉ አንተ ልትሞትላት ዓይንህን የማታሽላትን ሀገር ስም እየጠሩ በላይህ ላይ ጆካ ለመጫወት ሲቧትሩ ታያቸዋለህ፡፡ አንዳንዴ በመሬት ላይ፣ በተግባር ምን እያደረጉ እንደሆነ በአራት ዓይኖችህ እያየህ የምትረዳው ነገር እንዳለም እንዳያስቡ አዕምሯቸውን የደፈነባቸው ይመስለኛል፡፡ ወይም በጣም አራዳ የሆኑና በነፍስህ የተጫወቱብህ ስለሚመስላቸው – አንቱ ከእነሱ በላይ እነሱ እያደረጉ ያሉትን ነገር የማትባንን፣ ልትረዳው የማትችል አድርገው ይገምቱሃል መሰለኝ ሳስበው፡፡ እና እውነቱን እያወቅከው – ‹‹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!›› ይሉሃል፡፡ ያሉህን ‹‹እሺ›› ብለህ፣ ከነገር ሠላም ይሻላል ብለህ፣ ጎንበስ ጎንበስ ስትልላቸው – ድሮ ልጅ እያሱ ‹‹የአባቴን ሙክቶች አንጋልዬ ብሸናባቸውስ ማን አባቱ ሊናገረኝ!›› ይል ነበር እንደተባለው – እነዚህም ዓይንህ እያየ ‹‹አንጋልዬ ካልሸናሁብህ›› ይሉሃል፡፡ በድርጊታቸው ሁሉ፡፡
ነፃ ሆነው እኮ፣ አንተንም ነፃ አድርገው ከተማን አይደለም፣ ሀገርን ለጥቅማቸው እንዲያመቻቸው አድርገው መምራት ቢችሉ እኮ – እየመረረህም ቢሆን ትችለዋለህ እኮ! ወያኔን መሸከም የቻለ፣ ተረግጦ ተወቅጦ መገዛት የለመደ የኢትዮጵያ ህዝብ – እነዚህን ባለጊዜዎችም እኮ የሚሸከምበት ትከሻ መቼ አጣ? እነዚህ እኮ ለተገዢነት ራስህን አመቻችተህ ‹‹እሺ የፈለጉትን ያድርጉን›› ብለህም እኮ ነው ከምትቋቋመው ከትዕግስትህም ከሰብዕናህም ከልክህም በላይ የሚሆኑብህ፡፡
አብሯቸው የኖረውን አማራ እየመረጡ እኮ በመቶዎች በሜንጫና በገጀራ እየተለተሉ እንደገደሉት፣ በዱላና በድንጋይ ቀጥቅጠው ሰባራና ቁስለኛ እንዳደረጉት፣ በሺህዎች የሚቆጠርን አማራ – የራሳቸው ፖሊስ፣ ሚሊሻና ወታደር ባለበት ዓይኑ እያየ ‹‹በሉት!›› እያለ ከኋላ – የአማራውን፣ የጋሞውን፣ የትግሬውን፣ የኦርቶዶክሱን፣ ወዘተ ነጥለው እየመረጡ ቤት ንብረቱን እኮ እያቃጠሉ – ሌላው እኮ በጥፋታቸው ደረጃ እና ልክ – ለአንዳችም በቀልና ቁጣ እኮ አልተነሳሳም፡፡ ሁሉም ዶሮ እንኳ እንዳልሞተበት ዝም እኮ ነው ያላቸው፡፡ ግን ይህም ለእነሱ በቂያቸው አይደለም፡፡ መቼም አይበቃቸውም፡፡ የሚጠረቁም አይነቶች አይደሉም፡፡
ሌላውን ተወው፡፡ እዚሁ በመሐል አዲሳባ ላይ ሆነህ እኮ እልም ካለ ጫካ ተሸክመው ያመጡትን የጠባብነት ስንክሣር አንተ ላይ አምጥተው በግድ ሊያራግፉብህ ሲሞክሩ ታያቸዋለህ፡፡ ቁቤዬን በግድ ካላራግፍኩብህ ሲልህ ታየዋለህ፡፡ ዋቄ ፈታዬን በአናትህ ካልተከልኩብህ ብሎ ሲገግምብህ ታየዋለህ፡፡ ገዳ-ዬን ተሸክመህልኝ ዙር ይልሃል፡፡ ነዋሪዉ በስንት መዓት ሺህ ዓይነት ችግሮች በተወጠረባት በአዲሳባ መሐል ምን ዓይነት መፍትሄ እያመጡልኝ ይሆን ብለህ ስትጠብቅ በጠራራ ጸሐይ የኢሬቻ ሃይቅ ሲያስቆፍርና ውሃ ሲሞላ ታየዋለህ፡፡ የኦሮሚያ ባንዲራ ላይ ባለው የዛፍ ቅርፅና የውሃ ዋና ያጌጠ የሽርሽር መናፈሻ ሲገነባ ታየዋለህ፡፡ ጦርሠራዊቱን፣ ባንኩን፣ ፍርድቤቱን፣ አቃቤህጉን፣ ፖሊሱን፣ ጉምሩኩን፣ ነዳጁን፣ ኢንዱስትሪውን፣ ፖለቲካውን፣ ቀበሌውን፣ ክፍለከተማውን፣ እያንዳንዱን መሥሪያ ቤት ሁሉ፣ እያንዳንዷን ጥቅም የሚገኝባትን ቦታ ሁሉ… አንዲትም ሳይቀር እያነፈነፉ… እኛና-እኛ-ብቻ ካልሠፈርንበት፣ የኛ ካድሬ… የኛ ቶሎሳና ኡማዎች፣ የእኛ ነገራና ጉዲናዎች ካልተቆጣጠሩት፣ ኬኛ ካልበላው ሞተን እንገኛለን ሲሉ ታያቸዋለህ፡፡
ነገረ ሥራቸውን ሁሉ ስታየው በቃ ሁሉም ነገራቸው ጭፍን ያለ ‹‹ዛሬን ካልበላህ ነገ ትሞታለህ›› የተባለ፣ ወይ ‹‹ችጋር ነገ ይገልሃል›› የተባለ ጠኔያም ወራሪ ሠራዊት በሁሉ ነገርህ ላይ የሠፈረብህ የሚመስል ግግም ፍጥጥ ያለ ይሉኝታ የሌለው ነገራቸው ሁሉ – ቆሽትህን አሳርሮ ብቻ አይተውህም እኮ! በቃ የቀረችህን እንጥፍጣፊ ቅንነት ሁሉ አንድ በአንድ አሟጦ ያለ አመልህ ‹‹ፎቢክ›› አድርጎ ነው የሚያስቀርህ፡፡ የምሬን ነው የምልህ – ኡማዎቹን በዓይንህ ማየት ትጠላለህ፡፡ ምን እየሰሩ እንደሆነ በግላጭ እያየሃቸው – ሀገሬ፣ ክብሬ፣ ማዕረጌ… እያሉ ሲለፋደዱ መስማት ትጠላለህ፡፡ በትክክል አይ ኪዋችንን 63 ነው ብለው የደመደሙ ነው የሚመስልህ፡፡ ወይም እነሱ እንደዚያ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ እንጂ በጤናቸው – እንደዚህ – የጅል ብልጦች ለመሆን አይሟሟቱም እያየሃቸው፡፡
በዚያ ላይ መንግሥት-ነክ በሆነ ስብሰባማ ላይ ድንገት ተሳስተህ ተገኝ እስቲ? መፈጠርህን ትጠላለህ፡፡ አንዴ ይሄ ለውጥ ተብዬ ያመጣው ከአብይ ተሿሚ ቶሎሳዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ በሚመራው ስብሰባ ላይ በግድ ተገኘሁ፡፡ እንዴ?! ‹‹ነፍጠኛ፣ ነፍጠኛ›› እንዳለ ወረደ! በተለይ አሁን ጊዜው የኛ ነው የሚል ትምክህት ትህትናቸውን ጨርሶ ስላጠፋባቸው ከወያኔም ጊዜ በባሰ በእጥፍ ጥላቻቸውና ገገማነታቸው አይሏል፡፡ ንግድና ነፍጠኛን ምን አገናኛቸው? ይሄ የነፍጠኛ ቡዳ የበላው ሚኒስትር ዴኤታስ ነው ኢትዮጵያን ከዓለም ዘመናዊ ንግድ ጋር ለማስተሳሰር የሚመራት? ቀልድ ነው ለውጡ!
ዴኤታው የዓመቱን አንዲት ስብሰባውን በነፍጠኛ ጀምሮ፣ በነፍጠኛ ጨረሰ፡፡ በሌላውም ቦታ ያው ነው፡፡ የመንግሥት ነክ ቦታ ላይ አትሰብሰብ፡፡ ሲያቅለሸልሹህ ነው የሚውሉት፡፡ በቃ ሁለ-ነገራቸውን ትጠላለህ፡፡ በመካከላቸው መገኘትህን ትጠላለህ፡፡ በዚህ ዘመን በእነዚህ ውዳቂ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች መካከል መፈጠርህን ትጠላለህ፡፡ ዕድልህን ትረግማለህ፡፡ እኔ እንደዚያ ነው የሚሰማኝ፡፡ ሌላውም ከኔ አይለይም፡፡ ከኔም ይብሳል፡፡ ብዙው ሰው ለጨዋታ ሳነሳለት እንኳ ለማንሳት ራሱ አይፈልግም፡፡ እንዲህ የምትንገፈገፈው ወደህ አይደለም፡፡ ለመጥላት ፈልገህ አይደለም፡፡ ለመማረር ፈልገህ አይደለም፡፡ በቃ ግግም ያሉ፣ ድርቅ ያሉ፣ ሼም የሚባል ነገር ጨርሶ የማይጎበኛቸው – ደረቅ ተረኞች ለመሆን የሚሞክሩት ነገር ነው ነገራቸውን ሁሉ አስፀይፎህ እንድትንገፈገፍ የሚያደርግህ፡፡
ሳያቸው፣ እና ስታዘባቸው – ከሞላ ጎደል – ሲበዛ ይሉኝታ የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው እልም ያሉ ዓይነደረቅ ነውረኞች ናቸው፡፡ ልክ ያቺ ቤቲ ተብዬዋን የኤል ቲቪ ጋዜጠኛ ተመልከታት፡፡ የቡና ቤት ሴተኛ አዳሪ ነው የምትመስለው፡፡ ከነንግግሯ፣ ዘለፋዋ፣ ሌንጬጯ፣ የስድብና የማንጓጠጥ ድፍረቷ፣ ዘረኝነቷ፣ ባለጊዜ ነኝ ብላ የምታስበውና… ያ ደሞ ማንንም እንዳሰኛት ለመዘርጠጥ መብት ሰጥቶኛል ብላ የምታስብበት ሁሉነገሯ፡፡ ትጠላለህ ቶክሾው፡፡
ስነምግባር የሚባልና ይሉኝታ የሚባል ለሰው ልጅ በተለይ ለኢትዮጵያዊ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር አያውቁትም፡፡ ሁሉም የለውጥ አጋፋሪ ተብለው ተመራርጠውም፣ ተመልምለውም የምናያቸው የቄሮው ሰዎች እንደሧው ናቸው፡፡ ከዋናው ሰውዬ እስከ መጨረሻው የወረደ ተላላኪ ካድሬ ድረስ – ሁሉም ከሆነ የዐይነደረቅነት ፋብሪካ ተመርተው የወጡ እስኪመስሉህ ድረስ አንድ ዓይነት ድርቅናና ይሉኝታ-ቢስነት የተላበሱ ኡማዎች ናቸው፡፡ በፍፁም ከተማ ውስጥ አድገህ፣ የከተማ ልጅ ሰብዕና ይዘህ፣ በተለይ የተማረ ሰው ሆነህ – ከእነርሱ ጋር ችለህ መዝለቅ አትችልም!
እንዴ? ወያኔዎቹ እኮ ሀገርንም ሲወሩ – እንዲህ ዓይናቸውን አድርቀው በግግምና አልነበረም እኮ! ቢያንስ ሌብነትን እስኪለምዱ እኮ የለየላቸው ‹‹አላስ›› ነበሩ እኮ፡፡ ‹‹አላስበላ›› ‹‹አላስጠጣ›› ‹‹አላስቀምስ›› ባዮች፡፡ የሚፈልጉትን እስኪያልቡ ድረስ እኮ ትህትናና ፈገግታ እኮ አይለያቸውም፡፡ አክብረው ነው የሚመዘምዙህ፡፡ ወያኔዎቹ ቢያንስ የሚፈልጉት ነገር ምን እንደሆነ በትክክል ለይተው ያውቃሉ – እንጂ ሁሉን ነገር እንደ ፋንዲያ እላይህ ላይ እንጫንብህ እኮ አይሉህም!
ወያኔ በሥልጣን ዘመኗ አንድም ጊዜ ጊዜው የትግሬ ስለሆነ ትግርኛዬን በግድ ተማርልኝ የሚል ቃል ወጥቷት አያውቅም! ወያኔ በግድ ጥህሎዬን ካልበላህ፣ ህልበቴን ካልወጠወጥክ ብላ ገበታህ ላይ ሠፍራ አታውቅም! ወያኔ አዲሳባ መንገዶች ላይ ቀሚሳቸው ላይ ቄጠማ እየነሰነሰች በዓመት አንዴ የምትለቅብንን ልጃገረዶች እንኳ ሲያይ ብዙ ሰዉ እንዴት ነበር ያረገው የነበረው? አስበው እስቲ ካሁኑ ጋር! ሁሉም የሚያውቀው ነው! ምንም የተደባበቀ ነገር የለውም! ወያኔ ኮንዶሚኒየምን የገብረእግዚአብሔሮች መናኸሪያ አስመስላዋለች! ብታስመስለውም ግን፣ እነ 22ን እና ጎፋን፣ ላፍቶን የመሳሰሉ ሰፈሮችንም መቀሌ የገባህ እስኪመስልህ የትግራይ ቀበሌዎች ብታደርጋቸውም ግን፣ ነገር ግን፣ ወያኔ ይህን ሁሉ ስታደርግ ዓይን እኮ አለው!
ወያኔ በስርቆቷ ሁሌም ከሌላው ጋር እየቀላቀለችና እየተቀላቀለች ነው፡፡ በዕጣ እያወጣችኮ ነበር ቀዩዋን ያየ ጨዋታዋን የምትጫወተው፡፡ እንጂ እንዲህ እንደ ቄሮዎቹ ገና መንበሯ ሳታረጋ እንዲህ መሐል አዲሳባ ላይ አራግፋ ዓይን አውጥታ 20 ሺኅ የትግራይ ታጋዮችን፣ ወይ 20ሺህ የትግራይ ተፈናቃዮችን አሰፈርኩበት የሚል የጅል ገገማ ዝርፊያ አሰምታ አታውቅም! እንዴ ወያኔ በ20 ምናምን ዓመት ቆይታዋ መቼ ነው የተበሳጩ ትግራዋዮች ሌላውን በገጀራ ጨፈጨፉ አስብላ፣ ሰው አሰቅላ፣ ከተማ አስወርራ እያነደደች አሳድራ የምትታወቀው?
በእርግጥ በሥልጣንና በጥቅም ጅብ የሚያደርጋቸው የወያኔዎቹ ፋሺስታዊ ነገራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ – ግን ሁሉንም እኛ ብቻ፣ ዛሬውኑ እና ዛሬውኑ በልተነው እንሙት – ሁሉ ነገራችንን እናራግፍባችሁ – በመደብ ቋንቋዕ ትግርኛ ካላነገራችሁን ከናንተ ጋር አንገበያይም – ደማችሁን ካላጣራን እኛ ክልል አትኖሩም – የሚል ግን የወረደ የመጨረሻውን ዓይን ያወጣ ዘረኛ ፈጣጣነት ውስጥ በፍፁም አልገቡም ወያኔዎቹ! ቢያንስ ለይምሰል እንኳ የሆነ ሼም የሚባል ነገር እኮ ይጨልፋቸው ነበር! እነዚህ እኮ በቃ በአንዴ እኔ ነኝ ያለ አተት እኮ ነው የሆኑብን! እንዴ? ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ? በ2 ዓመት ስንቱን ጉድ እኮ ነው ያሳዩን!
ያውም እኮ የረባ መሣሪያና ምናምን እኮ እያሳዩ እኮ አይደለም! እንደ ድንጋይ ዘመን ሰው – ድንጋይና ዱላ፣ ገጀራና ሜንጫ እያፋጩ እኮ ነው – ቀጥቅጠን እንገዛሃለን ምንም አባክ አታመጣም እያሉን ያሉት! እንደነዚህማ አተት የሆነ ገገማ ገዢ በኢትዮጵያ ምድር ተፈጥሮም አጋጥሞም አያውቅም! እንዴ! በስብስቴ ዘመንም፣ በጣሊያን ዘመንም፣ በወያኔ ዘመንም እንደነዚህ ያለ ጉድ አይተንም ሰምተንም አናውቅም! ጣልያን እኮ ሊገዛን ሲመጣ – ሀገሩን እየወረረም መንገድ፣ ፎቅ፣ ህንጻ፣ መኪና፣ ኬክ፣ ፓስታ፣ ቺክ፣ ዘመናዊ ትምህርት፣ ዘመናዊ ነገሮችን ምናምን ሁሉ እኮ እያግተለተለ እያስከየፈን እኮ ነበር የመጣው፡፡ እንጂ እንዲህ ግግም ብሎ ኢሬቻና ሜንጫውን እያግተለተለ፣ የእርድ ነጋሪት እያስመታ እኮ አይደለም የመጣው! እነዚህ የምን ጉዶች ናቸው ግን? እውነት በኢትዮጵያዊ ማንነት ውስጥ እንዲህ ዓይኑን ያወጣ ኋላቀር የፋሺስትነት መንፈስ ነበረ ማለት ነው እኛ ሳናውቀው? ወይስ ወያኔዎቹ ምን አስነክተዋቸው ነው ሥልጣኑን ያስረከቧቸው?
ገና ሥልጣኑ ሳይደላደል፣ ገና ገዢነታቸው ሳይረጋ ካሁኑ እንዲህ የሆኑ.. ትንሽ ቢቆዩማ ምን ሊያደርጉን እንደሚከጅሉና እንደሚያደርጉማ መገመት አይከብድም! ያን ስለምናይ ነው ዛሬ ላይ አምርረን የምንጮኸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ውለው ካደሩ፣ ውስጣችን ያለውን ቅንነት አንጠፍጥፈው ማስጨረስ ብቻ አይደለም፡፡ ያን ማድረጉን አሁን ባጭሩ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ራሳችንም ሁላችንም ልንቆጣጠረው ወደማንችለው ሀገራዊ ህዝባዊ ብስጭትና ቁጣ ውስጥ ነው የሚጨምሩን፡፡ የመጨረሻዋን ኢትዮጵያዊ ትዕግሥታችንን ነው የሚያስጨርሱን፡፡ እነዚህ ሰዎች በዚሁ ከቀጠሉ የምንደርስበት የጥፋትና የመጨራረስ ሰቆቃ እንዲህ በቀላሉ የሚያባራ አይነት አይሆንም፡፡ እነዚህ ሰዎች ይዘውን ይጠፋሉ፡፡ ያጠፋፉናል፡፡ ለዚያ ነው የምንጮኸው፡፡ ለዚያ ነው ካሁኑ ወጊዱ! እዛው የለመዳችሁበት! ብለን ቆርጠን መነሳት ያለብን!
እውነቱን ለመናገር – በእኔ አስተሳሰብ – እና በብዙዎችም የተገራ ማንነትና ሰብዕናን ለዘመናት አዳብረው በኖሩ ማናቸውም ኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ – በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያወረዱብንን ሰቆቃና አፈና፣ ሽብርና ዘረፋ፣ እና ፋሺስታዊ የዘረኝነት ልክፍት አይቶና ተመልክቶ – ከእንግዲህ ወዲያ – በእነዚህ በለውጥ ስም በማይመጥናቸው የሀገር መሪነት መንበር ላይ ፊጥ ብለው በተገኙ ኋላቀርና ስግብግብ የቄሮ ዘራፊዎች ለመገዛት ፈቃደኛ የሚሆን ኢትዮጵያዊ – በእውነት ኢትዮጵያዊነቱን ከውስጡ አውጥቶ ሽጦታል! እንዴ?! ለውጥ እኮ ዓይነት አለው፡፡ ይሄ ለውጥ አይደለም፡፡ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ በመካከሉ ባለችው ክፍተት ዓይናችን እያየ የመጣብን መዓት ነው ይሄ፡፡
ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ‹‹ለውጥ!›› እያልን የጮህነው፣ ስንቶች – ብዙ ሺህ የኦሮሞ ልጆችን ጨምሮ – የምንናፍቀውን ለውጥ ለማምጣት ስንት መከራ የተቀበሉት፣ በግፈኞች ነፍሳቸውን እየተነጠቁ በየፈፋው በየመንገዱ ወድቀው የቀሩት እኮ – ትሻልን ፈትተን ትብስን ለማግባት አልነበረም! የዛገና የተሰለቸን ዘረኝነት፣ በአዲስ ጉልበቱ በሚንቀሳቀስ አስቀያሚና አስነዋሪ ዘረኝነት ለመተካት እኮ አልነበረም፡፡ ከዘረኝነት ጦስ ተላቀን፣ የተሻለች፣ የሠለጠነች፣ ዘመናዊ፣ ሁሉንም በእኩል ዓይን የምታይ… እኩል ፍትህን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ መድልዎ የምታዳርስ… የሁላችንም የሆነች፣ ለሁላችንም የቆመች፣ ከዓለም ጋር እኩል ለመራመድ የምትችል ዘመናዊት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን ተብሎ እኮ ነበር ‹‹ለውጥ! ለውጥ! ለውጥ! ለውጥ!›› ተብሎ ሲጮህ፣ ለለውጡ የሰው ደምና ህይወት ሲገበርለት የነበረው፡፡ እንጂ መች ከኋላቀርም የባሱ ኋላቀር ዘረኞችን በላያችን ላይ ገዢ አድርገን ለመሾም ሆኖ? የለውጡ መንፈስ – በጅቦች ኮቴ ተተክቶ የሰው ነፍስና የሀገር ሀብት የሚበላ ከጅብም የባሰ ክፉ የተራበ የቀን ጅብ ለማምጣት እኮ ፈጽሞ አልነበረም!
ዛሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል፣ የተሻለችን ኢትዮጵያ ለማየት እውን ለማድረግ የምትፈልግ፣ ሀገርህ ዛሬ በአንተ እጅ ላይ እንዳለች – ካንተ ሌላ ማንም የሚነሳላት ልጅ እንደሌላት እወቅ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነን የምንል፣ በኢትዮጵያ ታላቅ ተስፋ ያለንና ሀገራችንንና ህዝባችንን ከዓለም ዘመናዊ ሀገሮች ተርታ ተሰልፋ ለማየት ከልባችን ለምንቃትት የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ – ዛሬ ኢትዮጵያ ከእኛ ከራሳችን ከእያንዳንዳችን – ከእኔና ከአንተ ከአንቺ ሌላ – የመነሳት ህልሟን ይዞ የሚነሳላት ማንም ሰው የላትምና – ለምታስባት የተሻለች ሀገር ሆ ብለህ ተነስተህ የሞት ሽረት ትግልህን መጀመር ያለብህ ጊዜው አሁን ነው! ከራሴ ይጀምራል! ከአንተ ይጀምራል! ከአንቺ ይጀምራል! ከዚህም አሁን ከምናየው በእጅጉ ገዝፎና ብሶ ሊመጣ ካለው አሰቃቂ ጊዜ ሊሰውረን የሚችለው ብቸኛው መፍትሄ ልባም ሆነን በልበ ሙሉነት ከዚህ ከምናያት የተሻለችን ሀገር የምንፈጥረው እኛው እራሳችን መሆናችንን አውቀን ዛሬውኑ በቁርጠኝነት መነሳት ብቻ ነው፡፡ መፍትሄው እንደ ልባሙ እስክንድር ልባም ሆነን መገኘት ብቻ ነው!
አንድን እውነት ዛሬ ላይ ሆኜ በእርግጠኝነት እናገራለሁ፡፡ ትናንት ገጀራና ሜንጫ እየሞረዱ ሀገራችንን ከጣሊያን ወራሪ የታደጉንን የራስ መኮንንን ሐውልቶች በሐረር አደባባይ፣ በሐረር ጀጉላ ሆስፒታል፣ እና በለንደን ያፈራረሱት ኋላቀርና ፀረ-ኢትዮጵያ ቄሮዎች – ይሄ የቄሮ መንግሥት በሥልጣን ላይ እስካለላቸው ድረስ – ነገ ደግሞ ገጀራና ሜንጫቸውን እየሣሉ – በቄሮው መንግሥት ጦር ታጅበው – የአዲሳባውን የጊዮርጊስን የእምዬ ምኒልክን ኃውልትና የሰማዕቱን የአቡነ ጴጥሮስን ኃውልት አይንህ እያየ ሲያፈራርሱት በዓይኖችህ በብረቱ ታየዋለህ፡፡
ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከመኪና ላይ እያወረዱ፣ ከለቀስተኛና ከስለተኛ ላይ እየቀሙ፣ ከትምህርትቤትና ከመሥሪያቤቶች ላይ እያወረዱ የሚያቃጥሉና የሚረጋግጡ ቄሮዎች፣ ዛሬ ላይ ለጥምቀት፣ ለደመራና ለድጋፍ ሠልፍ ከሚወጣ ኢትዮጵያዊ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ እየነጠቁ፣ ሰውን እያሰሩ እየደበደቡ፣ መሬት ላይ የሚረጋግጡ የቄሮው መንግሥት የማለዳ ወታደሮች፣ ዛሬ ላይ በኤምባሲዎችና በዓለማቀፍ የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ ሰገነቶች ላይ የተሰቀሉ የኢትዮጵያን ባንዲራ አውርደው የኦነግን ባንዲራ የሚያውለበልቡት ቄሮዎች – ነገ በየቤትህ፣ እና በየመሥሪያ ቤትህ፣ እና በገዛ ሀገር ምድርህ ላይ – አባቶቻችን የተጋደሉላትን ባንዲራ ከልክለው ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ዜጋ፣ ፀረ-ዘመናዊነት፣ ፀረ-ሐይማኖት ባንዲራቸውን በግላጭ የሚያውለበልቡበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡ አሁንም በኦሮሚያ ክልል ከሞላ ጎደል ይሄ እውነ ሆኗል፡፡
ዛሬ ወለጋ ላይ ሄደህ የኢትዮጵያን ባንዲራ አታውለበልብም፡፡ ባሌ ላይ የቤተክርስትያን ቅዳሴን በኦነግ ባንዲራ በተሸፈነ ከበሮ እንዲቀደስ አድርገዋል፡፡ ዛሬ ላይ ባሌ ገብተህ የኢትዮጵያን ባንዲራ አውጥተህ አትገኝም፡፡ ዛሬ ሻሸመኔ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ ማውለብለብ የሞት ትኬትን መቁረጥ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ቁልቢ ገብርዔል የሚጓዝ የምዕመናን መኪና የኢትዮጵያን ባንዲራ አውለብልቦ አይደለም በትንሽዬ ቀለም ቀብቶ ማለፍ አይችልም፡፡ ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ነው፡፡ የዛሬ ቄሮዎች ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘናግቶ አሜን ብሎ ቁጭ ባለበት በዚህች አጭር ጊዜ ያሳኩትን ፀረ-ሀገርና ፀረ-ባንዲራ ተግባር ፋሺስት ጣሊያን እንኳ 5ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ የዚህን ያህል ደረጃ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ፀረ-ባንዲራ፣ ፀረ-ሀገር ውድመት ለማድረስ አልተሳካላትም፡፡
ዛሬ በቡራዩ፣ በሻሸመኔና በአርሲ፣ በሀረርጌና በባሌ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን በቀን አደባባይ ከተሞችን ለቀናት በቁጥጥራቸው ሥር እያዋሉ ያረዱት፣ የጨፈጨፉት፣ ያቃጠሉት፣ የበለቱት – እና ኢትዮጵያውያን በግፍ ሲጨፈጨፉ (እንዲጨፈጨፉም) እጃቸውን አጣጥፈው መሣሪያቸውን ደግነው ያጀቡት፣ የጄኖሳይድ አስፈጻሚ ሆነው ደጀንም የፊት አርበኛም ሆነው ራሱን መከላከል የማይችለውን ያልታጠቀ ንጹህ ኢትዮጵያ በቀን ፀሀይ ያስጨፈጨፉት የቄሮው መንግሥት ወታደሮች፣ እና ኋላቀር ገዢዎች – ነገ ከነገወዲያ ከአሁኑም በበለጠ ኃይልና ጉልበት ሲደረጁ ደግሞ – ምን መቅሰፍት፣ ምን ጭፍጨፋ፣ ምን አይነት አይን ያወጣ ኋላቀር ፋሺስታዊ የዘረኛ ጭፍጨፋና አገዛዝ ሊያነግሡብን እንደተዘጋጁ ከአሁኑ የሚሆነውን አይቶ ማወቅ፣ መገመት፣ መሥጋት የማይችል ኢትዮጵያዊ ካለ – በእውነት ማሰብን እንደ ነውር የቆጠረ፣ ስለነገ ማሰብን የማይፈልግ፣ አሊያም ከናካቴው ማሰብ የተሳነው ብቻ ነው!
እነዚህን ይሉኝታ የሌላቸው ኋላቀር ገዳዮችና ዘራፊዎች ሀሞትን ኮስተር ታግሎ፣ ተገቢውን ማንኛውንም ኢትዮጵያዊነት የሚጠይቀውን ዋጋ ከፍሎ፣ ጥፋታቸው ሀገር ምድሩን አዳርሶ ሀገሪቱን የደም ምድር ከማድረጉ በፊት፣ በጊዜ በወጉ መሸኘት ዛሬ ላይ ባለ በእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ እጅ ላይ የወደቀ የዜግነት ግዴታ ነው! ዛሬ ለትግል የታጠፈ ኢትዮጵያዊ ክንድ – ነገ በግልጽ አደባባይ – ከዛሬውም በባሰ አሰቃቂ መልኩ – በቄሮው ገጀራ እንደሚታጠፍ – በበኩሌ አንዲትም ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም! በብዙ ኢትዮጵያውያን አዕምሮ ውስጥ የሚመላለሰውና 2 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተግባር የመሰከረው ሀቅ ይሄው ነው፡፡
ዓይን-አውጣውን ዘረኛ የቄሮ ፋሺስት መንግሥትና ከጀርባው ያሰለፋቸውንና በኃይልና በትጥቅ እያደረጃቸው ያሉትን ባለሜንጫ አራጅ ሰልፈኞቹን በተባበረ ክንድ አምርሮ የመታገያ ጊዜው አሁን ነው! ጌዜው አሁን! አሁን ነው ወይም መቼም አይደለም! ጊዜ ነገ ነፍሳችንን የሚቀማ ባላንጣችን ነው! ለነገ ጊዜ የለም! ወደድንም ጠላን ኢትዮጵያውያን ጊዜ የመስጠት ቅንጦቱ ከእጃችን ላይ ወጥቷል! ምንም የምናባክነው ጊዜ የለንም! ለለውጥ የምንነሳበት ጊዜው አሁንና አሁን ነው!
“ሀገሬ ኢትዮጵያ – መመኪያዬ
በክፉ የሚያይሽ – ደመኛዬ
እሞትልሻለሁ – ተጋድዬ
ክብርና ኩራቴ – ኢትዮጵያዬ
አለኝ ጀግንነት – አልፈራም ሞት
ከዘር ማንዘሬ – የወረስኩት
ቃል ገብቻለሁ – ሀገሬ እናቴ
ማንም አይደፍርሽ – ሳለሁ በህይወቴ”!!
አንድ ሺህ ነፍስ ቢኖረኝ ለሀገሬ ስል አንድ ሺህ ጊዜ ለመሞት ፍቃደኛ ነኝ፡፡ ፈጣሪ ለሀገሬ ለመኖርም፣ ለሀገሬ ለመሞትም ያብቃኝ፡፡
የአናብስት ምድር ኢትዮጵያ በልጆቿ ተከብራ ለዘላለም ትኑር፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ!
Filed in: Amharic