>
5:13 pm - Monday April 20, 8989

"700 ካሬ ሜትር ውሰድ ተብዬ ነበር።…… ከመኪና  እና ቤት ሌላም ማግኘት አይቸግረኝም  ነበር"  ዮናታን ተስፋዬ

“700 ካሬ ሜትር ውሰድ ተብዬ ነበር።…… ከመኪና  እና ቤት ሌላም ማግኘት አይቸግረኝም  ነበር”

 ዮናታን ተስፋዬ
ለራሱ ያለውን ለህሊናው ትተነው ስለታከለ አንድ ምስክር አግኝተናል –  ዮናታን ተስፋዬን!!!
ህብር ራድዮ
~”ቡራዬ ላይ 700 ካሬ ሜትር ውሰድ ተብዬ አልፈልግም ብያለሁ።” ብሏል። የጓደኛዬን ዮናታንን መረጃ እንዳለ ብንወስደው ባለጊዜዎቹ “የእኔ ነው” ለሚሉት ሳይፈልጉ መሬት ዘግነው “እንካ ውሰድ” እንደሚሉ ነው። ስጡኝ ብለው ለሚጠይቁማ በሄክታር ሰጥተዋቸዋል ማለት ነው!
~”ብፈልግ ቤትና መኪና ብቻ ሳይሆን ሌላም ማግኘት እችል ነበር።” ብሏል ዮኒ።  ቤትና መኪና የፈለገ ወስዷል። ሌላም የፈለገ ወስዷል ማለት ነው።
ሌላው ግን እነ ዮናታንም ውሰዱ ሲባሉ ብቻ ሳይሆን ባለጊዜዎቹ የእኛ ነው ለሚሉት ሁሉ ጠየቀም አልጠየቀም መሬት፣ መኪና ሌላም ሌላም እያነሱ ሲሰጡ እንደነበር ያውቁ ነበር። ለዚህም ምስክር ናቸው!
ሌላውን ሀቅ ለህሊናው ትተን ይችንም መተርጎሟን አውቆም ይሁን ሳያውቅ መተንፈሱ መልካም ነው። ዮኒ እንደነገረን ከሆነ የገዥዎቹን ስም ያሞካሹ በትንሹ ከ700 ካሬ ጀምሮ “ውሰዱት” ተብለዋል።  እዚህ ፌስቡክ ላይ ሲገፋን የሚውለው በትንሹ 700 ካሬ ሜትር የተገፈተረለት  ነው። ሌላም ሌላም አለ!
በእርግጥ የምናውቀው የድሮው ዮናታን እነዚህን ዘራፊዎች መታገል ሞራል የነበረው ነው።  አሁን እየዘረፉም እያሞካሻቸው ከርሟል። ቢያንስ ግን ለደንበኛ ትርጉም የተጋለጠችውን ምስክርነት ስለሰጠ ምስጋና ይገባዋል። በመስቀለኛ ጥያቄ ደግሞ ፍንትው ማለት  የምትችል ነበረ።
Filed in: Amharic