>
5:13 pm - Tuesday April 20, 7126

ኦ ምኒልክ....!!! (ጴጥሮስ አሸናፊ)

ኦ ምኒልክ….!!!

ጴጥሮስ አሸናፊ

ይህ ጋዜጣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎች ከ1906 ጀምሮ በብራዚል በአፍሮ ብራዚላውያን ይታተም የነበረ ነው።
O Menelik የጋዜጣው ስም ሲሆን ዐላማው የነጭ የበላይነትን በጽሑፉ መዋጋት ነበር። ጋዜጣው ስሙን የወሰደው ከታላቁ የጥቁር ንጉሥ ዳግማዊ አጤ ምንሊክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነበር። አጤው የነጻነት ጮራ ስለነበሩ የዐለም ሕዝብ እንደ ተዐምር ነበር የሚመለከታቸው። በአሜሪካን ሐገር ነጭና ጥቁር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቤተ ክርስቲያን እንኳ አብሮ አይጸልይም ነበር። ጥቁሩ የተገለለና “ትንሽ” ነበር። በጥቅሉ ጥቁሩ ነጩን ጌታውን ተሸክሞ ከመዞር ያለፈ ተግባር የለውም ነበር ።
በአውሮፓ እስከ 1960ዎቹ ብዙ ሐገሮች Human zoo ነበራቸው። ጥቁር እንደ ብርቅየ እንስሳ በፓርክ ውስጥ ተቀምጦ ሙዝና ባኒ እየተጣለለት በአያሌ ሰዎች ይጎበኝ ነበር።
በአፍሪቃና በአውስትራሊያ እንደ እንሰሳ አስተሳስረው ያሰማሯቸውና ይጠብቋቸው ነበር። ለአይን የሚዘገንንና ለጆሮ የሚከብድ የቅኝ  ገዢዎችን ከልክ ያለፈ አውሬያዊ ተግባራትን ጨምሮ  ተዘርዝሮ የማያልቅ ብዙ… ብዙ ግፍ በሰው ልጆች ላይ ተፈፅሟል።
የእኛ ሐገር ሰው ይህን ነገር ሲሰማ ግርርርር ይለዋል።
ለፖለቲካ ጥቅም ተብሎ የሚወራም ይመስለዋል።
ግን አይፈረድበትም!  ምክንያቱም አጤ ምንሊክ እንደዚህ አይነት ባርነትን ወደ ሃገራቸው አስገብተው  አላስተዋወቁትማ ! ሥልጣኔን እንጂ ቅኝ ተገዥነትን አልተቀበሉማ!

ኦ ምንሊክ!

ንጉሥ ሆይ ልደትዎን በኩራት እናከብራለን! 
ክብር ለአጤ ምንሊክ !
መልካም 176ኛ አመት ልደት!
Filed in: Amharic