>

ሞጋሳ የዘር ፍጅት ማስፈጸምያ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ? (ርዕዮት ሚዲያ)

ሞጋሳ የዘር ፍጅት ማስፈጸምያ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?

ርዕዮት ሚዲያ

አብይ አህመድ አዲስ አበቤን ምን ሊግት እንደወሰነ ለመረዳት እና በቄሮ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ የታሪክ ስር ለመረዳት ይህንን ጥንቅር ይመልከቱ — የገዳ ድርጅት የዘር ጭፍጨፋ ማስፈጸምያ ስርአት የሆነው ሞጋሳ እነሆ በዘመናዊ መልክ በአዲስአበባችንም ሆነ በኢትዮጵያችን ላይ የመስፈኑ ተጨባጭ ማረጋገጫዎች በየእለቱ እየበረከቱ ነው፡፡

ይኸውና የኦሮሙማ አጀንዳ ፊታውራሪ አብይ አህመድ አዲስ አበቤ ገዳን በትምህርት ስርአት ደረጃ እንዲጋት ወስኗል፡፡ ይህ በአለም ተወዳዳሪ የሌለው የነባር ኢትዮጵያውያን ነገዶችን ዘር ያጠፋ እና ያሳሳ፣ ባህል የለወጠ፣ ሀይማኖት የቀየረ እና ታሪክ ያወደመ ስርአት መነወር፣ መወገዝ እና መታገድ ሲገባው፣ በጎ እሴት ይመስል በእነኚህ ከቻሉ የኢትዮጵያን ያህል የምትሰፋ “ኦሮሚያ” ለመፍጠር፣ ካልሆነላቸው ደግሞ የኢትዮጵያን መሬት ቆርሰው ኩርማን አገር ለመመስረት ቆርጠው በተነሱ የኦሮሙማ ወታደሮች አስገዳጅነት በትምህርት ስርአት ውስጥ ተካትቶ ሊሰጥ ነው፡፡

ይቅርታ ሊጠየቅበት እና ካሳ ሊከፈልበት የሚገባ በሞጋሳ የተፈጸመ ይርጋ የሌለው ዘር የማጥፋት ወንጀል በኩራት የሚወደስ እና የሚሸለልበት ሆኗል፡፡ ይህ ተግባር አንድም አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስጢራዊ ንግግራቸው በሚገባ ያብራሩት እቅድ በፍጥነት እና በጉልበት መፈጸሙ እንደቀጠለ ሲያረጋግጥ፣ አንድም ደግሞ የአብይ አህመድ አገዛዝ ለአዲስ አበቤዎች እና ለኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ ደጋፊ ዜጎች ያለውን ለከት ያጣ ንቀት ያመለክታል፡፡ ሆኖም የገዳ ድርጅትም ሆነ የሞጋሳ ስርአት እንድንማረው ሳይሆን እንድንዋጋው ግድ የሚሉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነኚህ ምክንያቶች በተጨባጭ ታሪካዊ ማስረጃ ተደግፈው፣ በጥልቅ ትንተና ታጅበው ቀርበውላችኋል፡፡ እውቀት ከባርነት ያወጣልና፣ ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ ሁሌ ተገዥ፣ ሁሌ ጨቅላ ሆኖ ለመኖር በእራሱ ላይ የፈረደ ነውና፣ ይህንን ዝግጅት በመከታተል ትላንት በኢትዮጵያውያን ላይ በገዳ ድርጅት እና በሞጋሳ ስርአት የተፈጸመውን ዳር አልባ ወንጀል እንዲሁም ዛሬ ላይ ያንዣበበውን የኦሮሙማ ሰልቃጭ ጭቆና ጠንቅቀው ይረዱ፡፡

Filed in: Amharic