>
5:13 pm - Wednesday April 20, 4327

የክብር ዘበኛው የሙዚቃ ሰው ጌታቸው ተካ አረፈ!

የክብር ዘበኛው የሙዚቃ ሰው ጌታቸው ተካ አረፈ!

በዝችው ቁመቴ፣ ውበቴ እንዳንቺ ነው፣ ማርዬ ማር ወለላ (ከውብሸት ፍስሃ ቀጥሎ) የሚሉና ሌሎች የፍቅርና አብዮታዊ የእናት ሃገር ዜማዎችን ተጫውቷል…
ጌቾ በተለይ የእናት ሃገር ፍቅርንና አበዮታዊ ዜማዎችን በመጫወት በኩል  በማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ ዕውቅናን ያተረፈ ነበር…
ድምፃዊ ጌታቸው ተካ። የሦስት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነው…
ከልብ አዝኛለሁ  –  ስለ ጌታቸው ተካ ዕረፍት
ከሁለት ቀናት በፊት ጋሽ አየለ ማሞ የጌታቸው ተካ ጤንነት ጥሩ መሆኑን፣  ደህና የሕክምና ዕርዳታ ስለማግኘቱ አጫውቶኝ ነበር።  ትላንት ነሐሴ 21 ቀን ወደ ማምሻው ላይ ጋሽ አየለ ለጌታቸው ተካ ደውሎለት በጣም ደስተኛ በሆነ ስሜት ያናገረው መሆኑን፣  የሕክምና ዕርዳታ እያገኘ
 በነበረበት ጊዜ ሐኪሞቹ በጌታቸው ጥርስ የማያስከድን ጨዋታ በእጅጉ የተደሰቱትን ያህል በጌታቸው ተካ ዕረፍት ከልብ  ያዘኑ መሆናቸውን እንደገለጹለት  … ጥልቅ በሆነ የኀዘን ስሜት ውስጥ  እንዳለ ነግሮኝ ነበር።  ይኸው ፍልቅልቁና ትልቅ ትንሽ  የሚባለውን ሰው ሁሉ አክባሪው ጌታቸው… ኖረ ኖረና ከፈገግታውና ከትኅትናው ጋር አረፈ።…
 ድምፀ-መረዋው፣ ፍልቅልቁ፣ ሰው አክባሪውና ለእግዚአብሔር ሰላምታ ንፉግ ያልነበረው ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያና ቆፍጣናው ወታደር ጌታቸው ተካ አረፈ። ከልብ አዝኛለሁ።  ሞት የሕይወት ጥላ ነው… የሰው ሁሉ መጨረሻ ሞት ነው። ለጌቾ ቤተሰቦች፣  ለወዳጆቹና ለአክባሪዎቹ ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁ።
 የጌታቸው ተካ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 23  ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4-5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዲስ አበባ 12  ቁጥር አውቶብስ ማዞሪያ በተለምዶ “ብረት ድልድይ” ተብሎ በሚታወቀው ሠፈር  በሚገኘው በመንበረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
Filed in: Amharic