>

"ገዳ" ወደትምህርት ስርአቱ ከመግባቱ በፊት.... 214 ሚሊየን ብሩ ለምን ዋለ? (ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

“ገዳ” ወደትምህርት ስርአቱ ከመግባቱ በፊት…. 214 ሚሊየን ብሩ ለምን ዋለ?

ብርሀኑ ተክለአረጋይ

የሀይል ሚዛን እየጠበቀ ሲከረባበት የኖረውና የሄደውም የመጣውም አገዛዝ ቀይ ምንጣፍ ሆነውለት መሬት ሲሰበስብና ዜጎችን ሲያስለቅስ የነበረው ድንቁ ደያስ (አባዱላ?) ሚዛን ከድቶት ከብልፅግና ጋር ከተጣላና ከሀገር ከወጣ በኋላ (ውጣ ተብሎ እንዳልወጣ ሁሉ) እርሱ የሰራቸው ግፎችና ያስለቀሳቸው ዜጎች በዋልታ ቴሌቪዥንና በተለያዩ ሚዲያዎች ሲለቀቁ ከርመዋል።
ግለሰቡ ከሀገር ከወጣ በኋላ  እርሱን የሚያሞካሹ፣ መንግስትን የሚዘልፉና የሚያስፈራሩ አባገዳዎችን ቃለመጠይቅ የያዘ አሳታሚው ያልታወቀ መፅሔትን ከማሳተም ጀምሮ በomn ቴሌቪዥን ቀርቦ “ድንገት ብገደል እንኳን የኦሮሞ ህዝብ ሀብቴን እንዲጠቀም ብዬ 214 ሚሊየን ብር በአባገዳዎች ስም፣ በአባቦኩዎች ስም ባንክ አስገብቼ ነው ከሀገር የወጣሁት”በማለት ተናግረዋል።
ታዲያ ድንቁ ደያስ ላይ ዶክመንታሪ እያሰራ አፋልጉኝ ሲል የከረመው መንግስት በራሳቸው በኦቦ ድንቁ ስለተገለፀው ስለዚህ ገንዘብ አልሰማም ይሆን? “የኦሮሞ ህዝብ እንዲጠቀምበት” የተባለው ገንዘብስ ለምን አገልግሎት እየዋለ ይሆን? አደራ ተቀባዮቹ ገንዘቡን “የገዳ እሴቶች”  ከሚባሉት መካከል ለእርቅ፣ለልማት … አዋሉት ወይስ……..? በወንጀል እንፈልገዋለን የተባለ ግለሰብ ገንዘብስ በአደራ መቀበል ከገዳ “እሴት” ጋር አይቃረንም?
ከሁሉም በፊት ህግ ይከበር
Filed in: Amharic