>
5:13 pm - Thursday April 19, 7601

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ቅሬታ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበና  ከግምት ያላስገባ ነው!!! (የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት....)

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ቅሬታ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበና  ከግምት ያላስገባ ነው!!!
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ጌታቸው ባልቻ
ሀብታሙ ምናለ
 
* የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምላሽ የሀገር ባለውለታ ለሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አይመጥንም !!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው እለት በመንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ አማካይነት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ እንዲሁም ብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ለሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ወቅታዊ የሀገራችንን ጉዳይ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቷ ይታወሳል።
በመግለጫውም በኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት አውግዞ መንግስትም እየተደረገ ያለውን ሀይማኖት ተኮር ጥቃት በአስቸኳይ ሊያስቆም እንደሚገባ ገልፆ ችግሮች ያላቸውን በርካታ ሁኔታዎች በማብራሪያ አስቀምጧል።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ጌታቸው ባልቻ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችው እና የሰጠችውን መግለጫ ተቀብሎ መንግስታዊ የእርምት ተግባር ከመስጠት እንዲሁም በመዋቅሮቻቸው ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ ሆድ አደር ባለሥልጣኖቻቸው ላይ ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ቅሬታ ክልሉ ያለበትን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበና እየተደረገ ያለውን ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው ሲሉ መተቸታቸው ለኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማንመጥን እና የክልሉ መንግስት በምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት በቸልታ እየተመለከተው መሆኑን ማሳያ ነው።
ከዚህ ቀደም እኚሁ የኦሮሚያ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ጥቃቱን የሃይማኖት ነው አትበሉ በማለት በቁስላችን ላይ እንጨት በመስደድ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን በተደጋጋሚ በክልሉ መንግስት የሚወጡ መግለጫዎች ቁስሎቻችንን እንድናክም ሳይሆን ቁስሎቻችን እንዲመረቅዙ የሚያደርጉ ናቸው።
አንተ ክርስቲያን ነህ እየተባለ ሲገደል ለቆየ ህዝብ በክርስትናው ሳይሆን የክልላች ነዋሪ እና ሰው ስለሆነ ነው ድጋፍ የምናደርግለት ማለት ከመሣለቅ አይተናነስም።
ተወደደም ተጠላም በኦሮሚያ የሚገኙ ምዕመናን የተገደሉትም እየተገደሉ ያሉትም ኦርቶዶክሳውያን ስለሆኑ ብቻ ነው ! ይህንንም ከመቀበል ይልቅ አላግባብ የሚደረጉ ጨፍን እና ላሞኝህ አይነት አካሄድ ለሀገር ግንባታም ሆነ በመተሳሰብ እና በመፈቃቀር ላይ ለምንገነባትና ለምንኖርባት ሀገራችን ቅንጣት ያህል የሚፈይደው ነገር አለመኖሩን ከግምት በማስገባት መንግስትም እንዳለበት ትልቅ ኃላፊነት የኦርቶዶክሳውያንን የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊያስጠብቅ ይገባል !!
የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
Filed in: Amharic