>

በአፍራሾችህ ዶማ ላይ የተኛህው አዲስ አበቤ ንቃ...! ንቃ...!  ተደራጅ...! ተደራጅ...!!! (አለማየሁ ስነጊዮርጊስ)

በአፍራሾችህ ዶማ ላይ የተኛህው አዲስ አበቤ ንቃ…! ንቃ…!  ተደራጅ…! ተደራጅ...!!!

አለማየሁ ስነጊዮርጊስ
* የአዲስ አበባ ራስ ገዝነት እንቅስቃሴ እና ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል…!
 
*****
የመረጥነው ያስተዳድረን፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ይዘን ሰልፍ እንውጣ፣ …ወዘተ…ዛሬ ቅንጦት ናቸው። ወዳጄ በሃገራችን ሌሎች አካባቢዎች እየጠፋ ያለው ህይወትና ንብረት እኔን አይመለከተኝም የምትል ከሆነ ህልመኛ ነህ፤ እናትና ልጅ አንድ ላይ የሚገሉ፣ ቤተክርስቲያን እያቃጠሉ አባቶችን የሚያርዱ ላንተ ይመለሱ ይመስልሃል? ይልቅስ ተጠንቀቅ ወዳጄ የልጅህና ሚስትህ ሬሳ ላይ ቆመው ሊጨፍሩብህ የቋመጡ ብዙ ናቸው፤ ፖለቲካውን ተውና ህይወትን አትርፍ፤ ለፖለቲካ ያንተ ነፍስ ከቁጥር የዘለለ ፋይዳ የላትም።
ለምሳሌ
ለብዙዎቹ ፖለቲከኞች አንተ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሳትሆን ብሄር አሊያም ቁጥር ነህ፤ ስለዚህ ዜና ማድመቂያ ከመሆንህ በፊት ለመግደል ሳይሆን ላለመገደል ፤ እናትህንና ልጅህን ለማስገደልተዘጋጅ።
ፊሽካ የሚነፋው ሰውዬ ዛሬም መሃል አዲሳባ ተቀምጦ (ሽመልስ) ለተጨማሪ ጭፍጨፋ ማካሄጃ ሀይል እያደራጀ ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮሙማ አባገዳ ምናምን እያለ የሟቾችን የብሄር ስብጥር ይደለድላል፤ ድሃ ደመ ከልብ ሆኖ ይቀራል፤ ስለዚህ ወዳጄ ነግ በኔ ብለህ ጉራጌ ሆነ ወላይታ፣ ትግሬ ሆነ አፋር፣ ጉሙዝ ሆነ አኝዋክ፣ ለጎረቤትህ ሮጠህ ድረስለት፤ የነሱን ቁሻሻ ፖለቲካ ትተህ መጀመሪያ ነፍስህን አቆይ።
ነጥቦቹን ሳታያይዛቸውና ማን ምን እያረገ፣ ማን ምን እየተደረገ እንደሆነ በየዋህ አስተሰሰብ ካየኸው፣ የሚመጣው ካለፈው ይብሳል፤ ወደ አዲሳባ የሚመጣ ጦስ ደግሞ በድንጋይና ሜንጫ የሚያልቅ አይደለም፤ ባስቸኳይ ከተማዋን ለቆ መውጣት ያለበት የኦሮሚያ ፖሊስ በፌደራል ከተማ ውስጥ ለምን እንደተቀመጠ ይግባህ።
ከተገደለ በኋላ ብሄር የሚፈለግለት ሰው ሲገደል ቆሞ የሚያይ፣ እስካፍንጫው የታጠቀ ጦር እዚህ ከተማ ከህግ ውጪ ተቀምጦ የአዲስ አበባን ህዝብ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀ ነው፤ የዚህ ጦር መሪ ደግሞ “ጃዋር ወንድማችን ነው፤ ሽመልስ አሳራጃችን ነው፤  እሱን የነካ ባይናችን መጣ” እያለ ሲቀባጥር የነበረው የለየለት ዘረኛ ሰውዬ ነው፤ ኮሽ ቢል ይህ ሰው ምን እርምጃ እንደሚወስድ አለማሰብ ነው፤ እያስፈራራሁህ አይደለም፤ ግን አንተ እየሞተ ካለው ከማንም በምንም አትለይም፤ እንደቅጠል እየረገፈ ያለው ሁሉ እንዳንተው የሚያመልከው አምላክ ፣ የሚወደው ቤተሰብና ጓደኛ፣ ዘመድ ወዘት …የነበረው ነው፤ ስለዚህ ነው ለመግደል ሳይሆን ላለመገደል ዝግጁ መሆን ያለብህ፤ በየቀኑ ጩህ፤ በየእለቱ ተድራጅ፤ ገፍቶ ለሚመጣው ተዘጋጅ።
የኦሮምያ ፖሊስ ግን ከአዲስ አበባ ምን ያደርጋል????የአዲስ አበባ ፖሊስ ደብረ ብርሃን ወይም የአፋር ፖሊስ አዲስ አበባ ላይ ሲሰራ አይተህ ታውቃለህ? እናም እኔ የምልህ – ተደራጅ ተደራጅ ተደራጅ ለመግደል ሳይሆን ላለመሞት ተዘጋጅ!!!
Filed in: Amharic