>
5:13 pm - Tuesday April 18, 2051

ደርግ "ጋላ" የሚለውን ቃል በህግ እንዳገደው ሁሉ፣ ብልፅግናም "ነፍጠኛ" የሚለውን ቃል  ህገ-ወጥ ማድረግ አለበት!!! (ያሬድ ጥበቡ)

ደርግ “ጋላ” የሚለውን ቃል በህግ እንዳገደው ሁሉ፣ ብልፅግናም “ነፍጠኛ” የሚለውን ቃል  ህገ-ወጥ ማድረግ አለበት!!!

ያሬድ ጥበቡ

የጥንት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የክፍል ባልደረባዬ የነበረው ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለነፍጠኝነት ሲያወራ ሰማሁት። እናም አሰብኩ። ልክ ደርግ ጋላ የሚለውን ቃል መጠቀም በህግ እንዳገደው ሁሉ፣ የኦሮሚያ ክልሉም ብልፅግና ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ነፍጠኛ የሚለውን ቃል መጠቀም ህገወጥ ማድረግ አለባቸው። ምክንያቱም ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚገደሉት ነፍጠኛ እየተባሉ በመሆኑ ቃሉን መጠቀም ነውርና በህግ የሚያስጠይቅ ካልተደረገ፣ በዚህች ሃገር ላይ ገና የብዙ ንፁሀን ደም ይፈሳል።
ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የሃገሪቱ ጥግ የመኖር መብት ስላላቸው፣ ነፍጠኛ እየተባሉ መገደሉ እንዲቆም ከተፈለገ መንግስት ይህን ቃል መጠቀም ወንጀል ነው ብሎ ማወጅ አለበት። ያን ሳያደርግ ቀርቶ እነሺመልስ እብዲሳ በድብቅም ሆነ በህዝብ አደባባይ ሲጠቀሙበት ካየን፣ መንግስትን የግድያዎቹ ተባባሪ አድርገን መመልከት ግዴታችን ይሆናል። ከመመልከትም በላይ ለህልውናችን እንድንተጋ እንገደዳለን። ይሄው ነው!
Filed in: Amharic