>

እሱ_Think tank ሳይሆን Sink tank ነው! (እንግዳ ታደሰ)

እሱ Think tank ሳይሆን Sink tank… ነው!

እንግዳ ታደሰ

ከጦቢያ መጽሄት ቋሚ አምደኛ ከነበረው ሀሰን ዑመር አብደላ ጋር ቁጭ ብሎ ማውራት፣ የዚያን ትውልድ ፖለቲካ ውጣ ውረድ ከማወቅ አንስቶ፣በቀልድ እያዋዛ የሚያነሳሳቸው ፖለቲካዊ ቀልዶችና ፥ ምጸቶች በራሳቸው ሳቅ የሚያጭሩ ናቸው። በአንድ ወቅት ጥቁር ቡና ይዘን ስናወጋ ይህን ወግ አወጋኝ።
በግራ ዘመሙ ፖለቲካ ስትታመስ በነበረችው ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው በሚከፈቱት የፖለቲካ ኪዮስኮች ውስጥ፣ ኮፍያ እየለዋወጠ ፖለቲካ ውስጥ የሚዘፈቅ አንድ ሰው ነበር።አንድ ቀን የዚህ ተዘፋቂ ሰው ስም “በቲንክ ታንክ” ግሩፖች ውስጥ ስሙ መካተቱን የሰማው የራሱ ወንድም፣ ተገርሞ! እንዲህ አለው አሉ። እሱ! ወንድሜ “ቲንክ – ታንክ” ሳይሆን ሲንክ-ታንክ ነው። ባህር የሰመጠ ታንክ።
በዚህ Thinktank ርዕስ ዙርያ በፈረንጆች አቆጣጠር 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያንሪቪው ላይ ከጻፍኩት ጽሁፍ የተወሰደ ነው ምጸታዊ ቀልዱ። ትላንት ፕሮፌሰር መረራ ዘባረቁት በተባለው ተረታ-ተረት ፌስቡኩ ሁሉ ዛሬ እየወረደባቸው ነው።
ችግሩ እንዲህ ያሉ የቅዠት ተረታ ተረቶች ካላመነጩ undp የተባለው የተባበሩት መንግስታት አካል ፈሰስ አይሰጥም። ብዙው የስድሳዎቹ ፖለቲኸኞች ይህን  የዩኤንዲፒ አሞሌ ጨው ለምደዋል ።
ኢትዮጵያን ለመከራ የዳረጓት እነኚህ የስድሳዎቹ ጎምቱ ፖለቲከኞች ፣በተለይ የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ መንግስት አገር ውስጥ እንዲገቡ ሲፈቅድላቸው ትልቁ ጃክፖት ሎተሪ ስለወጣላቸው ሰብሰብ ይሉና፣ የቲንክ-ታንክ ምክክር ጉባኤ ፕሮጀክት ይቀርጹና ለፈረደበት undp ያቀርባሉ። ፈሰሱ ይመጣል ! የፈረንጅ አገሯም ጡረታ ወይ በዩሮ’ ወይ በዶላር ስትመጣላቸው በጥቁር ገበያ እየሸረፉ ያባዟትና ከ-undpው ጋር አዳምረው! ከበረዶ ያላቀቃቸውን የአብይ መንግስት እያመሰገኑ ዳዲ’/ ጠጅ በሹርቤ ፣ ጥሬ ስጋ ከሻኛ እያማረጡ ነገር ይጎነጉናሉ።
እነ ለታ ሌንጮ በኦስሎ ይህን ተረታ ተረት እየጻፉ ብዙ ክሮነር ይውስዱ እንደነበር አውቃለሁ።አሁን ደግሞ ከ-undp. ይህ የትላንቱ  የጋራ መድረክ ጉባኤ #ከቲንክታንክነቱ ይልቅ- #ሲንክታንክ ነበር። የችግሩ ፈጣሪዎች የችግሩ መፍትሄዎች በጭራሽ አይሆኑም። የ-undp አሞሌ ጨው ላሾች ናቸው ባብዛኛው።
Filed in: Amharic