>

እግዚአብሔር ይማርህ !!  ከኑመጋ ዱቢን፤ እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ… … ••• ( ዘመድኩን በቀለ)

እግዚአብሔር ይማርህ !!

 ከኑመጋ ዱቢን፤ እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ… …
••• ዘመድኩን በቀለ 
 
* የምመክርህ ብትሞት የፈለገ ብትታመም እንዲህች ብለህ ሚኒልክ ሆስፒታል ሄደህ እንዳትታከም!
* ኮሮና ይዞህ ቢገድልህ እንኳ ሬሳህ ሚኒልክ ሆስፒታል ሄዶ እንዳይመረመር። እንዳታደርገው።
* በጠላትህ ስም በተሰየመ ሆስፒታል እንዳትታከም። የካቲት 12 ብትል፣ ራስደስታ ብትል፣ ዘውዲቱ ብትል፣ ጳውሎስ ብትል። እንዲህች ብለህ በአጼዎቹ ሆስፒታል እንዳትታከም…
 
ጃዌ አትፍራ። አትንቀጥቀጥ። ወንድ ልጅ አይደለህም እንዴ? ያውም የነፃ አውጪ ሠራዊት አለቃ ሆነህ፣ ደግሞ ቀበቶ የታጠቀ ወንድ እንደዚህ አይሆንም። መድኃኔዓለምን እውነቴን እኮ ነው። ምንድነው በአንድ ጊዜ እንዲህ መንበጫበጭ?
•••
ኦቦሌሶ ኢትዮጵያዊ ሆነህ፣ በዚያላይ አፍሪካዊ ሆነህ ይቅርታ ኦሮሚያዊ ሆነህ፣ በዚያ ላይ መንግሥትን ያህል ነገር ተቃዋሚ ሆነህ ካልታሰርክማ ምኑን ወንድ ሆንከው? ደግሞም በአንድ ጊዜ እንዲህ መክሳት አልነበረብህም። አዜኝን።
•••
ኦቦሌሳ ከሚኒሶታ ሆነህ ስንቱን ቁጭ ብድግ ስታደርግ የኖርክ ሰውዬ ሱልልታ ስትደርስማ እንዲህ ራስህን በአንድጊዜ በተቅማጥም በሻታም ማሰቃየት የለብህም። ቆፍጠን በል። የዋቆ ጉቱ ልጅ አይደለህም እንዴ?
•••
ይኸውልህ ዓለም እንዲህ ናት። አንተ ያኔ እነሱ ሲታሰሩ የጮህክላቸው እነ አህመዲን ጀበል ዛሬ አንተ ስትታሰር ሥራው ያውጣው ብለውህ ዝም አሉህ። አንተ የአሩሲ እስላም ነህ። እነ አህመዲን ጀበል የጅማ እስላሞች ናቸው። በዚህ ላይ የጠቅላያችን የሰፈር ልጅ ነው። ሺ ዓመት ትበሰብሳታለህ እንጂ ጀበሎ ስለአንተ መፈታት ትንፍሽ አይላትም። ሸወዱህ።
•••
አንተ ስትታሰር ሰማይ ምድሩ የሚደበላለቅ መስሎህ ነበር። ወፍ የለም። ራስህን ቆለልከው። ሌሎች ደግሞ የበለጠ ቆለሉህ። ለመውረድ ስትቸገር ይኸው ጊዜ ደጉ ፈጥፍጦ ጣለህ። ምህረቱን ይላክልህ። ሽንትቤት አታብዛ። ምግብም አታብዛ። ተረጋጋ። ውጪው ሰላም ነው። ቄሮም ጫ ብሏል። መንግሥትም አምርሯል። በሐረርጌ ከወታደር ጋር የተሳፈጡ ትንሽ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እናም ተረጋጋ።
•••
እነ እስክንድርን እያየህ ተጽናና፣ ወኅኒ ቤት ቤታቸው የሆኑትን እነ እነ ስንታየሁን እያየህ ተጽናና። ትንፋሽህን ሰብስበህ ወደራስህ ተመለስ። የጥሞና ጊዜ ውሰድ። በቀለ ገርባን አትስማው። እሱ ከአንተ የባሰ ቱቀማ መራታ ቀዌ ነው። እናም ራስህን አዳምጥ።
•••
የምመክርህ ብትሞት የፈለገ ብትታመም እንዲህች ብለህ ሚኒልክ ሆስፒታል ሄደህ እንዳትታከም። ኮሮና ይዞህ ቢገድልህ እንኳ ሬሳህ ሚኒልክ ሆስፒታል ሄዶ እንዳይመረመር። እንዳታደርገው። በጠላትህ ስም በተሰየመ ሆስፒታል እንዳትታከም። የካቲት 12 ብትል፣ ራስደስታ ብትል፣ ዘውዲቱ ብትል፣ ጳውሎስ ብትል። እንዲህች ብለህ በአጼዎቹ ሆስፒታል እንዳትታከም። ቢቻልህ ከተቻለ ዳማከሴ ብትቀባ፣ ቀበርቾ ብትታጠን ይሻልሃል። ሞተሃላ ጃዌ።
•••
ልጅህ ደህና ነው። ባለቤትህም ሰላም ናት። እኛም ሰላም ነን። ቄሮም ሰላም ነው። አይዞህ ሰማይ ሂዊም ሰላም ናት። እናም አታስብ። አትጨነቅ። ፍርዱ ከእግዚአብሔር ከሆነ ዋጋህን ታገኛለህ። ፍርዱ ከሰው ከሆነ ዘመኑ የኦሮሞ ስለሆነ ብዙም አትቆይም። ለሥልጣኑ ካላሰጋህ፣ አርፈህ ፀባይ ካሳመርክ። ልክ እንደ አንዷለም አራጌ ፀባየኛ ከሆንክ ትፈታለህ። ተንፍሰህ ትወጣለህ። ተምረህ ታርመህ ትወጣለህ።
•••
ፀጋዬ አራርሳ መሳቂያ ሆኖልሃል። ብርሃነመስቀልማ ሙድ እየተያዘበት ነው። ሁሉም ለኦሮሞ ወጣት በአማርኛ ቋንቋ ነው የዐመጽ ጥሪያቸውን የሚያስተላልፉት። ወጣቱ ቄሮ የቁቤ ጄኔሬሽን ነው። አማርኛ አይሰማ፣ አይናገር፣ እንዴት ይስማቸው? አልተግባቡም። አልጋ ወራሽ ነው ያጣኸው። የመለስም፣ የአንተም ችግር እርሱ ነው እናም አይዞኝ።
•••
እንዲያውም አንተ እኮ ጥሩ ጊዜ ነው የታሠረከው። ሱሪህን አውልቆ የሚደፍርህ የለ፣ ብልትህ ላይ ( ካለህ ነው) ሃይላንድ የሚያንጠለጥል የለ። በዘርህ የሚሰድብህ የለ። ( ዐማራና ኦሮሞ) ስለሆንክ እድለኛ ነህ። በካቴና አትታሰር። ዳኛ ፈገግ ነው እንጂ ያለብህ “ ዝጋ ምንአባቱ ነው አፉን የሚከፍተው? ” አላለህ። እናም ከምር ዕድለኛ ነህ። ራሴ በምፈልገው ሃኪም ነው የምታከመው ብለህ እየታከምክ። ኧረ አትቀልድ አባቴ።
•••
ለማንኛውም እስር ጥሩ አይደለም። ከማንም አልመኝም። ተምረህ ለመውጣት ያብቃህ። በእነ አህመዲን ጀበል፣ በእነ ካሚል ሸምሱ፣ በእነ አቡበከር ግን ተስፋ ቁረጥ። ወፍ የለም። አባቴይሙት ወፍ የለም። ጋዜጠኞች እነ ኦኤምኤን እንኳ ኢንተርቪው ሊያደርጉላቸው ቢፈልጉም ስልክም አያነሱላቸውም። እናም እርሳቸው። አየህ የሰው ነገር እንዲህ ነው። በል ምህረቱን ይላክልህ። በላይም በታችም የሚያጣድፍህን ያስታግስልህ። አሜን።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ነሐሴ 15/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic