>

ከሚያጨበጭብላቸው ከሆንክ ብትገድልም ያጨበጭብልሀል፤ ከሚረግማቸው ከሆንክ ብታድንም ይረግምሀል!  (ዶ/ ር በድሉ ዋቅጅራ)

ከሚያጨበጭብላቸው ከሆንክ ብትገድልም ያጨበጭብልሀል፤ ከሚረግማቸው ከሆንክ ብታድንም ይረግምሀል!

 ዶ ር በድሉ ዋቅጅራ
.
.
እንደኛ ኢትዮጵያውያን በሰብአዊነት ሚዛን የቀለለ ማህበረሰብ አንዱ መገለጫ ግለሰቦችን፣ ጎሳን/ብሄርን እና ቡድንን ከሰብአዊነት እሴቶች በላይ ማድረጉ ነው፡፡ መግደልን የሚያወግዘው፣ ጥቃትን የማይቀበለው አድራጊውን ከግምት አስገብቶ ነው፡፡ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ማንም ያድርገው ማንም፣ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ማውገዝ የማይችል ማህበረሰብ፣ ደመነፍስ ከሰለጠነባቸው እንሰሳት ብዙ አይለይም፡፡
.
እያንዳንዱ ግለሰብ፣ እያንዳንዱ ብሄር፣ እያንዳንዱ ፓርቲ፣ እያንዳንዱ ሰፈር፣ ወዘተ… ይግደሉም ያድኑ፣ ይንጠቁም ይለግሱም፣ ያቃጥሉም – ይገንቡም፣ ወዘተ… የሚያጨበጭብላቸውና የሚረግማቸው ግለሰቦች፣ ብሄሮች፣ ፓርቲዎች፣ ቡድኖች አሉት፡፡ ከሚያጨበጭብላቸው ከሆንክ ብትገድልም ያጨበጭብልሀል፤ ከሚረግማቸው ከሆንክ ብታድንም ይረግምሀል፡፡
.
ሃያ ስምንት ዜጎቻችንን አልቃይዳ ሲቀላ የተንገበገብነው፣ የሀገሪቱን አደባባይ በሰልፍ ያናወጥነው ስለድርጊቱ ነው አድራጊው? ስለድርጊቱ ከሆነ፣ አልቃኢዳ ያደረገው በቁጥርም በአሰቃቂነትም በሀጫሉ ሞት ምክንያት የተደረገውን  ሩብ አይሆንም፡፡
.
ታዲያ ያንን ሰልፍ ያስተባበሩት፣ እነዚያ ለዜጎች ተቆርቋሪ፣ የሰብአዊነት ጠበቆች ዛሬ የታሉ??? የወረዳ፣ የዞን አስተዳዳሪዎችም ሆኑ የክልል መንግስታት፣ የሀገር መሪ ባለስልጣናት የት አሉ????  የተሰለፍነውስ ዜጎች የት አለን??
Filed in: Amharic