>

አህመዲን ጀበል በሞጣ ላይ አቀነባብሮ የሰራዉ ድራማ ሰሞኑን ያስቃዠዉ ጀምሯል...!!! (አህመዲን ሱሌይማን)

አህመዲን ጀበል በሞጣ ላይ አቀነባብሮ የሰራዉ ድራማ ሰሞኑን ያስቃዠዉ ጀምሯል…!!!

አህመዲን ሱሌይማን

 

” በአማራ ክልል መስኪድ አልተቃጠለም ለማለት አይደለም። በእስቴ የተቃጠሉት ይጠቀሳሉ። የሞጣዉ ግን የተለየ ኬዝ። አንዳጁ እራሱ አልቃሹ አካል ነበር። የእስቴዉን እንደ ሞጣዉ ያላጮሁት ከኦሮሚያ መስኪድ ቃጠሎዎች በፊት የተፈፀመ ስለነበር ነዉ!!!
 
በአብዛኛዉ የሞጣ ከተማ ሙስሊሞች ተከራይተዉ ንግድ የሚሰሩበትን ህንፃ አገር ለመበጥበጥና ህዝብን ለማባላት ሆን ብሎ ከዛዉ አካባቢ ከሆነዉ አዱኛ ሙጬ ከሚባል ጉማጅ በርሚል ፊት ጋር በቅንጅት እንዲቃጠል ካስደረገና የአዞ እንባ በማንባት አማራ ክልልን ለማመስ መሞከሩ ከታወቀበት በኋላ ወንጀሉና ስራዉ እንቅልፍ ስለነሳዉ በእኔ ላይ ማስረጃ ካላችሁ አምጡና በህግ ልጠየቅበት በማለት ላይ ነዉ።
የሞጣን መስኪድ አህመዲን ጀበልና በፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲካ የተጠመቁት ተከታዮቹ ለማቃጠላቸዉ ጥቂት የማይባሉ ምክኒያቶች ነበሯቸዉ። አንደኛዉ፣ ከዚህ ክስተት በፊት በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ በርካታ መስኪዶች ተቃጥለዉና ፈርሰዉ ነበር። በኦሮሚያ የተቃጠሉት አቃጣዮቻቸዉ ማን እንደሆነ ባይታወቅም የአዲስ አበባዎቹ በአስተዳደሩ ስህተቶች ፈርሰዉ የነበሩ ነበሩ። የሚገርመዉ በተለይ በኦሮሚያ ላይ ተቃጥለዉ የነበሩት መስኪዶችን በተመለከተ እሱና ሌሎቹ አክራሪ ኡስታዞች በጊዜዉ አንዲትም ነገር ሲተነፍሱ አልተሰማም። እንዲያዉም ስለ ኦሮሚያ ክልል አቃፊነትና ብዝሀነት ሊደሰኩረን በመሞከር የክልሉን ግፅታ ለመገንባት ቢዚ ሆነዉ ነበር። በክልሉ በመስጂዶች ላይ የደረሰዉን ዉድመት በማድበስበስ ለማሳለፍም ተሞክሮ ነበር። ሙስሊሞች አማራ ናችሁ ተብለዉ በብሄርና በማንነታቸዉ ከክልሉ ቤትና ማሳቸዉ ተቃጥሎና ከሞት የተረፉት ተሰደዉ (በወሎ ያሉት ከኦሮሚያ የተፈናቀሉት ሙስሊሞች)  ባሉበትም፣ አህመዲን ጀበልም ሆነ ሌሎች “ኡስታዞች” forcefully ወጥተዉ ለማዉገዝ ፈቃደኛ አልነበሩም። ነገር ግን እርሱና ግብርአበሮቹ ለመደበቅ የሞከሩት በክልሉ የደረሰዉ ይህ አሳፋሪ ተግባር ከህዝብ ሊደበቅ ስላልቻለ ክልሉ ክፉኛ ተወቃሽ ሆኖባቸዉ ነበር። አህመዲን ጀበል ደግሞ ይህ ጉዳይ ከነጃዋር ጋር በቅንጅት መሬት ማዉረድ ለጀመረዉ ኦሮሚያዊ ለሆነዉ ፅንፈኛ የፖለቲካ ስራዉ እንቅፋት የሚሆንበት ስለመሰለዉ፣ ችግሩን አጠቃላይ አገራዊ ችግር ለማስመሰልና እኛ ጋር ብቻ አይደለም ለማስባል፣ ሽብሩን የሚተገብርበት ሌላ ክልል ፍለጋ ላይ ነበር። በኦሮሚያ የተፈጠረዉን አገራዊ በማስመሰል ለማመጣጠን ደግሞ ከአማራ ክልል በላይ ተመራጭ ክልል አልነበረም። በመሆኑም እሱና ቡድኑ አማራ ክልል ዉስጥ አንድ ነገር አስደርጎ በማስጮህ ጩኸቱን ማመጣጠን ነበረባቸዉ (እራሱ ለኩሶ፣ እራሱ አቃጥሎ፣ እራሱ መጮህ)። ስለዚህ በሞጣ የሆነዉን በቅንብር ያስደረገዉ እርሱ እራሱ ለመሆኑ በጊዜዉ ጥርጥር አልነበረኝም።
ሁለተኛዉ ምክኒያታቸዉ፣ አህመዲን ጀበል በአማራ ክልል በባቲ አካባቢ ህዝብና በአፋር መካከል ምንም ባልተጣሉበት አስታርቃለሁ ብሎ መግባቱን ተከትሎ የሆነዉ ጉዳይ ነዉ። እሱና ለዚህ ሚሽን ይዟቸዉ የሄዱት ሌሎች ኡስታዞች (ካሚል ሸምሱ፣ መሀመድ ፈረጃ…) ማስታረቁን እንደ ሽፋን ተጠቅመዉ ፅንፈኛ ሴሎችን በአካባቢዉ በመትከል ክልሉን ለማመስ ሙከራ ማድረጋቸዉ በክልሉ ፅጥታና ደህንነት ኋይል ከተነቃበት በኋላና ያንን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የአንድነትና የሰደቃ ሙሀደራዎች በሚሉ ምክኒያቶች ሊያደርጉ የነበረዉን ስብሰባዎች ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ እኛ ሰላም ስለምንፈልግ አስሬ እየመጣችሁ አትበጥብጡን ወይም አገር ከተረጋጋ በኋላ ተመልሳችሁ መምጣት ትችላላችሁ፣ አሁን ግን እንረፍበት (ቃል በቃል) ብሏቸዉ ስብሰባዎቻቸዉን ሁሉ ሰርዞ ካባረራቸዉ በኋላ (ደሴ ወሎ አምባ የተከለከለዉ ስብሰባቸዉ ዋነኛዉ ነበር) በክልሉና በአማራ ህዝብ ላይ ይህ ነዉ የማይባል ጥላቻ የወለደዉ ቂም ይዘዉ ነበር የተመለሱት። ኦሮሚያ መስኪድ ተቃጥሎ አዲስ አበባ ላይ መስኪድ ፈርሶ አማራ ክልልማ ምንም ነገር ሳይሆን አይቀራትም ሳይፈርስና ብለዉ በክልሉ ላይ በተለይ መስጂድን ማቃጠል ላይ ትልቅ ሴራ ጀምረዉ ነበር። የክልሉ የፀጥታዉ ስርአት ተዘናግቷል ወይም ይከሰታል ብሎ አይጠረጥርም ያሉበትን ሞጣን በዚህ ምክኒያት ሊመርጡ ችለዋል።
ሌላዉ ምክኒያታቸዉ ደግሞ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እና የአማራ ክልል መጅሊስ ከክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር የፈጠሩት ቅንጅትና የአብሮ መስራት ትብብር አብግኗቸዉ ነበር። የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤትና የክልሉ መጅሊስ ለፀጥታዉ አካላት እነዚህን አክራሪዎች ከክልላችን አግዱልን፣ ሰላምና አብሮነታችንን ሊያደፈርሱ በመሯሯጥ ላይ ስላሉ በክልላችን እንዳይመጡ ከልክሉልን፣ ወሎ መጅሊስ ብለዉ ያቋቋሙትንም ስብስብ ከህግ አግባብ ዉጭ በመሆኑ ክልሉ እንዲበትንልንና ሌሎችን ጥያቄዎችን የያዙ ብዙ ደብዳቤዎችን በመፃፍና ለፀጥታዉ አካላት በማሳወቅ የተናበበ ስራ እየሰሩ ነበር። በኦሮሚያ የነበረዉ ብጥብጥ በእነዚህ ሰዎች በኩል ወደ አማራ ክልልም ኢምፖርት እንደሚደረግ የፀጥታዉ ኋይል ያዉቅ ነበር። እንዲያዉም ጄኔራል አሳምነዉ ከአባቶች የሚመጡልኝን ጥያቄዎች በክብር በማስተናገድ ሳይሸራረፍ ክልሉ በፅንፈኞችና ህገወጦች ላይ እርምጃ ይወስዳል በማለት ተናግሮ ነበር። በእነዚህ ምክኒያቶች የተነሳ ነዉ የአማራን ክልል እነሱ በሚጨመላለቁበት ጭቃ ዉስጥ ጎትተዉ ለማስገባት የጣሩት። በተወሰነ መልኩ በጊዜዉ ተሳክቶላቸዋል። ከአገር ማበጣበጥ በመዋጮ ሰበብ የህዝብ ገንዘብ እስከመመዝበር ድረስ።
አሁንስ? የኦሮሚያ ክልል ትርምስ ዉስጥ በገባበትና ወዳጆቻችንና ወንድሞቻችን የሚሏቸዉ እነ ጃዋርና ፅንፈኞች በሀጫሉ ግድያ ተለቅመዉ እስር በገቡበት እንዲሁም በአንድ ወቅት ሲመኩበት የነበረዉ በክልሉ የተዘረጋዉ የሽብር ሰንሰለትና የማበጣበጫ ጣቢያቸዉ የሆነዉ omn ከአየር ተመትቶ በወደቀበት ምን እያሰቡ ይሆን? ከኦሮሞ አክራሪ የፖለቲካ ፅንፈኞች ጋር እስልምናችንን በማቆራኘት በንፁሀን ደም እየቆመሩ ፖለቲካዊ ስልጣን ለመያዝ ሲተበትቡት የነበረዉ ትብታቦ በትንሹ ብቻ ላላ እያለ መምጣቱን ሲያዉቁ፣ እንዲህ መንቀል የጀመሩ ሙሉ በሙሉ ተበጣጥሶ ህዝብ ራቁታቸዉን ሲያያቸዉ ምን ሊሆኑ ነዉ? አህመዲን ጀበልና ተባባሪዎቹ በሞጣ መስኪድ ቃጠሎ በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ከሁሉም ጥፋትና ለቅሶ ጀርባ፣ የወሀቢያ እጅ አለበት የሚለዉ ዕይታዬ መቼም አይለወጥም። በኢትዮጲያ ባለፉት ጥቂት አመታት በደረሱ ጥፋቶች በሙሉ የእነሱ ተሳትፎ ያልነበረበት አልነበረም። ሀይማኖታዊም ፖለቲካዊም ይዘት ባለዉ ጥፋት ዉስጥ ሁሉ ተሳትፈዋል።
*****
Filed in: Amharic