>
5:13 pm - Monday April 18, 9329

ንጹሃን ሲታረዱ እየፎከርክ ስለ ግድያ ስታወራ የሚሰማህ ጆሮ ማግኘት አይከብድም...??? (ህብር ራድዮ)

ንጹሃን ሲታረዱ እየፎከርክ ስለ ግድያ ስታወራ የሚሰማህ ጆሮ ማግኘት አይከብድም…???

ህብር ራድዮ

ደምህ ደሜ ነው ያለህን ወገንህ ላይ ዛሬ ሥልጣን አስክሮህ ከውስጥ እና ከውጭ ተመሳጥረህ እንደ ጠላት በገዛ አገሩ “ግድለው” ስትል እየሰማ ለሌላ እልቂት የምትጠራውን አመጽ እንዲያጅብልህ መጠበቅ ተራ ብልጠት ብቻ ሳይሆን ድንቁርና ነው። መጀመሪያ ጥላቻህን እና የጥላቻ ቅስቀሳህን አቁም። ንጹሃን ሲታረዱ እየፎከርክ ስለ ግድያ ስታወራ በቁም ነገር የሚሰማህ ጆሮ ማግኘት ብትቸገር አይገርምም።
የወጣህበትን መሰላል ሰብረህ ወያኔ አይኑ ሲቀላበት፣ጸጉሩን ሲነጭበት የነበረውን ትብብር በስግብግብ እና ተረኝነት አፈር ድሜ አብልተሃል። እሱም ላይበቃህ ንጹሃን ላይ ዘምተህ ስታሳርድ በምን ተአምር ነገ ደህና ነገር ካንተ ይጠብቅ? እንዴት ስው ወያኔን መልሶ ለማንገስ ሕዝብ ላይ ይዘምታል? ለቅሶህ የሚሰማው ንጹሃን እንዲታረዱ መቀስቀስህን ስታቆም ነው። ግደል  ብለህ ቆንጨራና ጠመንጃ ታጥቀህ ውጣ ያልከው ሀይል ዓላማው ምን ነበር?
ዛሬ በጥላቻ የሚያብዱ ራሳቸውን ካልሆኑ ማንን ይወቅሳሉ? ሕዝብማ አድምጠው የዘር እና የወያኔን አጥር ሰብሮ እንዲህ በአደባባይ ደምህ ደሜ መከራህ መከራዬ ነው ሲልህ ነበር።
የጥላቻ ቅስቀሳ አራማጆች ወያኔ ጋር የጀመራችሁት አሸሼ ገዳሜ ተጨማሪ ጥቃት ለማድረስ ንጹሃን ላይ ለመዝመት አግዞ ካልሆነ መቼም ነጻ አያወጣችሁም።
Filed in: Amharic