>

በኦሮሚያ ክልል አሁንም እየጠፋ ያለው የዜጎች ህይወት አሳዛኝም፤ አሳሳቢም ነው!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

በኦሮሚያ ክልል አሁንም እየጠፋ ያለው የዜጎች ህይወት አሳዛኝም፤ አሳሳቢም ነው!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

ወላይታ ላይ በብርሃን ፍጥነት ደርሶ ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረግ ላይ የነበሩ ወጣቶች ላይ የጥይት ናዳ ያዘነበው መከላከያ አሁን ሚዛናዊነቱ የሚታይበት ጊዜ ነው  !!
 
 ዜጎች ሃሳባቸውንም ሆነ ተቃውሟቸውን ፍጹም ሥልጡን እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ሊገልጹ ይገባል። የመንግስት የጸጥታ ጏይሎችም ያልተመጣጠነ የጏይል እርምጃ በዜጎች ላይ  ከመውሰድ መታቀብ ይኖርባቸዋል። በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎች የጥቃት ሰለባ እንዳይሆኑ መንግስት ተገቢውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል። ባለፋት ሁለት ቀናት ሕጻናት እና ሽማግሌዎችን ጭምር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በጸጥታ አካላት በተሰነዘረ ጥቃት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተዘግቧል።
በተቃውሞ ሰልፍ ስም የሌሎች ዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል እና ንብረት ለማውደም የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችን በሕግ ጥላ ስር እንዲውሉ የማድረግ ጏላፊነቱን መንግስት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።  የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በሻሸመኔ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች የተከሰቱት አይነት የጭካኔ  የጥቃት እርምጃዎች እንዳይደገሙ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግም ይገባል።
ቄሮ የተባለው  ስብስብ በአርሲ ዶዶላና በሐረርና ሻሸመኔ አንዳንድ ቦታዎች መንገድ መዝጋት ጀምሯል። ወላይታ ላይ በብርሃን ፍጥነት ደርሶ ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረግ ላይ የነበሩ ወጣቶች ላይ የጥይት ናዳ ያዘነበው መከላከያ አሁን ሚዛናዊነቱ የሚታይበት ጊዜ ነው  !!
ሌላው:– ከወላፈኑ እርቀው ዜጎችን ለግጭትና ለጥቃት የሚያነሳሱ ጏላፊነት የጎደላቸው አካላትም ከእኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል።
Filed in: Amharic