>

የድኽረ ሰቆቃ አዕምሮ ጭንቀት ሁከት- መታወክ (Post truama stress disorder- PTSD) እና መፍትሄው (ታጠቅ መ.ዙርጋ )

የድኽረ ሰቆቃ አዕምሮ ጭንቀት ሁከት- መታወክ (Post truama stress disorder- PTSD) እና መፍትሄው  

 

ታጠቅ መ.ዙርጋ  

 

ማሳሰቢያ፦ይህ  ጽሁፍ  ከላይ ባለው አርእስት ይጻፍ እንጂ ሌሎች በንዑስ እርእስት የጻፍኳቸው መልዕክቶች የያዘ  ነው። ሺመልስ አብዲሳ ‘ኦርሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ግራ እያጋባን/ <confuse> እያደርግን ነው የምንገዛቸው’ ካለው በተጻራሪ ፤ አንባቢ ይህ ጽሁፍ ሲያነብ ግራ እንዳይጋባ ግልጽ ላድርገው በማለት ነው ላሳስብ የወደድኩት ። ይህ በዚህ ትቼ ወደ አርእስቴ መልዕክት አመራለሁ ።    

 

አንዴም ሆነ ተደጋጋሚ ሰቆቃ (truama) የተፈጸመባቸው ወይም  በአስቃቂ ገጠመኞች ያለፉ  ሰዎች ፣ያንን ሰቆቃ ሲፈጸም ያዩ ወይም በቦታው  የነበሩ ፤ የአዕምሮ ዋግምት/ ህክምና ካላገኙ

ለዓመት፣ ለዓመታት ወይም ዕድሜያቸው በሙሉ  ለአዕምሮ  ጭንቀት  ሁከት ይጋለጣሉ። 

ስለሆነም  ያንን ጭንቀትና ሁከት የሚያስታግስ ወይም የሚያሽር  ዘመናዊና ሳይንሳዊ  የአዕምሮ ዋግምት(counselling) ያስፈልጋቿል::

ለዘመናዊ ዕድገት መሰረት በሆኑ – በኢኮኖሚ ፣ በሁለግብ ሳይንሳዊ (ኢንዱስትሪ ፣ኪነ ጥበብ፣ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣በመገናኛ፣ በማኅበራዊ ጤና) ወዘተርፈ አደጉ በሚባሉ በምዕራባውያን አገሮች፤ የማኅበረሰባቸውን  የአዕምሮ ጤና (mental health) ትልቅ  ትኩረት ይሰጣሉ። ከጦርነት ለሚመለሱ ወታደሮቻቸው፣ ከመኪናና ከሌላ  አደጋ ለተረፉ፣ የቤተሰብ ጸብ ላለባቸው ፣በወላጆች የዘውትር ጭቅጭቅ ምክንያት አእምሯቸው ለተጎዱ ሕጻናት ወዘተርፈ  የአእምሮ ዋግምት (counseling ) ይሰጧቿል ።

ሀ)  በአገራችን በየግዜው በአክራሪ ብሄርተኞች ፦ ስቆቃ፣ጭፍጨፋ፣ግድያ ተሞክሮባቸው  ለተረፉትና በዚያ ኩነት (episode) ለተሸብሩትን   

ለ)  በሰኔ 23/10/2012 በአሩሴ፣ በሃረርጌ፣በባሌ፣በሻሸመኔ ፣ በሶደሬ ወዘተርፈ በአገር በቀል (IISIS) አይስሶዎችና  ጽንፈኛ ብሄርተኞች -በአስቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈው ከሞት የተረፉትን ፣ ቤተሰብ ተጨፍጭፎ የተገደለባቸውንና በሥፍራው ተገኝተው ያንን  ሰቆቃ ያዩ  ዜጎች በአዕምሮ ዋግምተኞች፣በሥነ ልቦና ሞያተኞች ማለት በ (counselor,psychologist,psychiatrist et, team) ህክምና  አግኝቷልን? ይህ ሳይሆን ቢቀር  ሊገጥማቸው ከሚችሉ ችግሮች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

 

  • የኩነቱ ነጸብራቅ/ትውስታ ደጋግሞ ወደ አምሯቸው እየመጣ ይረብሻቿል
  • ተናዳጅ፣ ብስጩ፣ፈሪ፣ ሥጋታም ወዘተ.. ይሆናሉ
  • በቀላሉ ስሜታዊ መሆንና መቆጣት
  • ትኩረት ማጣት ወይም ሃሳብን ለሰብሰብ መቸገር (lack of concentration)
  • የመልስ አስጣጣቸው  የተጋነና የሚያስፈራ ነው  
  • በጣም ተጠራጣሪ መሆን፤ በቅዠት መቸገር፣ የስሜት መደንዘዝ
  • ያ ሰቆቃ የሚያስታውሱ ፥ ቦታዎች፣  ሰዎች ፣ ድርጊቶች  ወዘተ..ማየት አለመፈለግ
  • እንቅልፍ ማጣት፤ ደጋግም ከመኝታ መነሳት ወዘተርፈ   

በገዢዮቻችን መመርያም ሆነ በእነዚህ ዘርፎች በሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን ተነሳሽነት፤ እነዚህን ለሰቆቃ የተዳረጉትን ወገኖቻችን የአዕምሮ ህክምና መስጠት ይጀመር አይጀመር፣ ይታሰብ አይታሰብ ፣ይታቀድ አይታቀድ ወዘተርፈ የማውቀ ነገር የለም። በዚህ ዘርፍ የቀሰምኩት ቁንስል እውቀት ስላለኝና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አዕምሮዬ  ግድ ስላለኝ ነው ይህንን የማሳስበው ። 

< > በሰኔ 23/2012 በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ  አካባቢዮች የተፈጸሙ  አረመኔያዊ (barbaric)ተግባሮች ፦የ(ዘር ፣ጎሳ፣ ብሄር እና የሃይማኖት ቡድን) የመመንጠር/ የጂኖሳይድ ወንጀል ክስ ለመመስረት ብቃት ይኖራቸው ይሆን ?

 

  • ስለይህ  ንዑስ  አርእስት ያለኝ ግንዛቤ እጅግ በጣም ባጭሩ ፦በአንድ (ዘር ፣ጎሳ፣ ብሄር እና የሃይማኖት ቡድን)  ላይ ያነጣጠረ የፍጅት ዘመቻ (genocide) የሚወሰነው {determined} የሚሆነው በተገደሉ የነዚያ ፦ ዘር፣ ጎሳ፣ብሄር እና የሃማኖት ቡድን አባላት ቁጥር መብዛትና ማነስ አይደለም ፡፡ በጄኖሳይድ አውድ የተጨፈጨፉትና የተገደሉት ጥቂቶች ቢሆኑም በዋናነት የሚታየው -ጥቃቱ፣ ግድያውና ጭፍጨፋው ባጋጣሚ (random) የተደረግ ሳይሆን ፤ አንድን {ዘር፣ጎሳ፣ ብሄር እና የሃይማኖት ቡድን ለመደምሰስ ፦(ታስቦበት፣ ታቅዶበትና ተሲሮበት) የተከናውነ ለመሆኑን በማስረጃ አስደገፎ በማሳመን ነው ።
  • ሌላው በጄኖሳይድ አውድ -በአንድ {ዘር፣ጎሳ፣ብሄር እና የሃይማኖት ቡድን  ላይ ፍጅት (genocide)  ተፈጸመ የሚያስብለው /የሚያሰኘው  ምን ምን ሲፈጸም ነው? ለመፈጸሙስ  ማስረጃ/ዎች አለ? አሉን? የሚለው ነው ።
  • እ.ኤ.አ  በ 1948 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ባደርጉት ውል (Convention)የመጀመርያውን የዘር ፍጅት (genocide)ትርጉም  ተሰጠ/ተቀመጠ ። የጂኖሳይድ ወንጀለኞችን መከላኬና መቅጫ

 ንድፈ ሃሳብ  በውሉ ተካተተ ።  ውሉ/ኮንቬንሸኑ የተስማማባቸውን  የጂኖሳይድ  ገቢሮች

የያዙ አምስት መስፈርቶች ተነደፉ። ማለት ግድያው፣ ጭፍጨፋውና  ምንጠራው ፦ዘርን ፣ጎሳን፣ ብሄር እና የሃይማኖት ቡድን በመደምሰስ  (ዝንባሌ፣ጽንሰ ሃሳብ፣ ተሳሻሽነት ወዘተርፈ )ማአቀፍ ከተፈጸመ/ሙ ። 

 መስፈርቶቹ ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ናቸው ፦

  1. Killing members of the group
  2. Causing serious bodily or mental harm
  3. Deliberately inflicting conditions of life calculated to bring about the group`s physical destruction in whole or in part
  4. Imposing measures intended to prevent births
  5. Forcibly transferring children

ወደ አማርኛ ሲተረጎም ፦

  1. የቡድኑ አባላት መግደል
  2. የከፋ አካላዊ ወይም የአዕምሮ ጉዳት ማድረስ
  3. ሆንተብሎ  ኅይወትን የሚያሰቃዩ ሁኔታዎች በመፍጠር፣ በተቀነባበረ ወይም በሰሌት  ኢላማ ለተደረገው ቡድን ፤ሙሉ ወይም ከፊል አካል ማጥቃት/መደምሰስ
  4. በስሌት ወይም በዕቅድ እንዳይወልዱ ወይም እንዲመክኑ ማድረግ /መጫን
  5. በጉልበት/በሃይል  ህጻናቶቻው/ልጆቻቸው  መንጠቅ፣  ወደ ሌላ አካባቢ መውሰድ ፤ እንደማልት ይመስለኛል።
    • ከነዚህ ውስጥ  ከላይ በጠቀስኳቸው  በሰኔ 23-2012  በኦሮሚያ አካባቢዮች  ያልተገበረ ምን አለ? በተባሉ ቦታዎች  ስላልነበርኩ ሙሉ በሙሉ መመስከር አልችልም።  ነገር ግን ከተለያዩ  ሚዲያ አውታሮች  ከሰማሁት አኳያ  ያልተገበረው ፤ ምናልባት በቁጥር አምስት (5) የተነጠበው ይሆናል ። 

 

  • እንደ  እኔ እይታ ከአንድ እስከ አራት (4) ያሉትን መስፈርቶች ( ዘር ፣ ጎሳ፣ ብሄር፣ የሃይማኖት ቡድን የማጥፋት/የጂኖሳይድ ወንጀል ክስ ያሟላሉ ባይነኝ። ምናልባት በቁጥር አራት (4) የተነጠበው  በጥያቄ ምልክት ይቀመጥ ይሆናል። ይሁን እንጂ የአማራ ህጻን በኦሮሞ  ቀየ  ተወልዶ ማየት አንፈልግም በማለት እናቲቱ በማረዳቸው ፤ ዘር በማምከን ጽንሰ ሃሳብ  ይካተት  ይሆናል። 
  • ይህ ክስ በየትኛውም ብቃት ባለው/ላት  ኢትዮጵያዊ/ት ቢጀመር ፣ጉዳዩ እዳር አድርሶ ውጤታማ ለማድረግ  ፤ ውስብሰብ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች ይኖራሉ። ስለሆነም  የዚህ  ክስ መሳካት አስተዋጾ  ይኖራቸዋል በሚባሉ ዘርፎች ሁሉ  መተባበር ይኖርብናል።

 

 

 

  • በሰኔ 23/2012 – በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች   ስለተፈጸመው  ዘግናኝ (heinous )ተግባር የኦሮምኛ ዘፈን  ዘፋኙ  የአቶ  አሊ ቢራ  አቋም  ከአንድ አርቲስት ወይም የኪነት ሰው የሚጠበቅ ነውን? 

 

ዘፋኝ  አሊ ቢራ የሃጫሎን ሞት ተከትሎ  በኦሮሞ አይስሶችና ጽንፈኛ ብሄርተኞች – ጎሳ፣ ብሄርና የክርስትና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ፣ግዲያ፣ ሰው እንደ ቄራ ከብት ማረድ እና  የእነዚህን  ቡድኖች ፦ሃብትና  ንብረት መዝረፍና  ማውደም አግባብ ነብር ማለቱ፤ እሱ ራሱ በቦታው ቢኖር ኖሮ የጭፍጨፋውና የግድያው ተካፋይ ይሆን ነበር ማለት ነው ።እንድ እሱ አባባል  የሃጫሎ ሞት እንደ ለአድባር እንደሚታረዱ  በጎች  የበርካታ  አማሮችን፣ጉራጌዎችን፣የኦርዶክስ ክርስትና ተከታዮችን  ህይወት መገበር ነበረበት ወይም ያስፈልግ ነበር ማለት ነው ።  

ስብዕና የሌለው አርቲስት በደመነፍስ የሚተውን ወይም የሚዘፍን አርቲስት ነው ። ከእነዚህ አንዱ አሊ            ቢራ ነው ። 

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለመሸንሸንና የሕዝባችንን  አንድነት ለማናጋት ቀንና ለሊት የሚኳትኑ ሃይሎች በራሳቸው ተንኮል ተጠልፈው ይከስማሉ!

 ሉዓላዊና ያልተደፈረ ሃያል አገራችን ፤ ሉዓላዊና ያልተደፈረ ሃያል ሕዝባችን ላለማስደፈር የሚጠይቀውን መሰዋዕትነት  ሁሉ ለመክፈል እንዘጋጅ ! 

የአክራሪ ብሄርተኞች ሥውርና ይፋ ደባ ለአገርና ለሕዝባዊ አንድነት በሚታገሉ ሃቀኛ የኢትዮጵያ ልጆች ይከሽፋል!

Filed in: Amharic