>

¨ብልፅግናን ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው! ¨ አቶ ሽመልስ አብዲሳ [ሀብታሙ አያሌው]

“ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን!”
የአቶ ሽመልስ አብዲሳ
* ብልፅግናን ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው!
* ……አምስት  ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም። ለኦሮምኛ ብለን ነው! አማርኛ እየደከመ ነው፣ እየቀነሰ ነው!
*….ኦሮምኛ ከአማርኛ በላይ እየተነገረ ነው። በቤንሻንጉል 37 በመቶ ኦሮምኛ ይነገራል፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ……ይነገራል። አማርኛ እየቀነሰ ነው……!
ሀብታሙ አያሌው
ኢህአዴግ የተሰራው ለህውሃት ነውና የተሰራበት ምክንያት ደግሞ ስልጣን ላይ ለመቆየት ነው። እኛም ብልፅግናን የሰራነው ከስልጣን ለመውረድ አይደለም። ብልፅግና ደግሞ ወደዳችሁም ጠላችሁም የኛ ነው። እኛ ነን የሰራነው። ለእኛ እንደሚሆነን አድርገን። በተመሳሳይ መንገድ ህወሃት ኢህአዴግ እንዲመቸው አድርጎ ነበር የሰራው። ኢህአዴግ ገና ሲፈጠር የቀድሞዎቹ የኦህዴድ መስራች ሰዎች ለመታገል ሞክረዋል። ግን አልቻሉም። ያልቻሉበት ምክንያት ደግሞ ጠብመንጃ ስለሌላቸው፣ ሀይል ስለሌላቸው ነበር። ኢህአዴግ ሳይመሰረት በፊት አሁን የምናወራውን ነገር አንስተው ነበር።
አሁን ዶ/ር ቢቂላ ያነሳውን ነገር ሁሉ አንስተው ነበር። እነ ኢብራሂም መልካ ተገምግመው የተባረሩት በዚህ ነው።  ስለ ውክልና እና ስለ ፍትሃዊነት ስለ ጠየቁ። ግን majorityን minority የሚያደርጉበት instrument ስለሆነ፤ minorityን majority አድርገው እዚህ ሀገር ላይ የማዕከላዊ መንግስት ስልጣንን ለመቆጣጠር ሲባል ነው አሳምረው የሰሩት። ከተሰራበት መንገድ ውጭ እንዳያድግ ደግሞ ሲንከባከቡት ኖሩ። በመጀመርያ ዙር የተንከባከቡት በሞግዚት ነበር። እነ ሰለሞን ጢሞ፣ እነ ቢተው በላይና በመሳሰሉት ሲንከባከቡት ነበር። ሞግዚትን እንደምንም በትግል ማሸነፍ ሲቻል ደግሞ internally click ገነቡ ማለት ነው። በclick ደግሞ ሲንከባከቡት ቆዩ። ይሄ እውነት ነው። ስለዚህ በ2008 ክረምት ውስጥ ሊቀመንበር መቀየር ሲቻል ነው ትግሉ አንድ አቅጣጫ የያዘው። እንደ ህውሃትም እንደ ኢህአዴግም <<እኛ ሳናውቅ ሊቀመንበር ቀየራችሁ እኛ ሳናውቅ ፕሬዝዳንት ሾማችሁ>> ብለው ያበዱ ጊዜ ማለት ነው። ማበዳቸውም ልክ ነበር። ስለዚህ ቁጭ ተብሎ አማራጭ ሲሰላ በሶስት መንገድ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ተባለ።
አንደኛው አብዮት እናካሂድ ተባለ። አንዱ አማራጭ እሱ ነበር። አብዮት አይሆንም ሌላ ችግር ያመጣል። እንደዚያ ዓይነት ዝግጅት አልነበረንም። plus ሁልጊዜ ከዜሮ መጀመር ነው የሚሆነው ተብሎ አብዮት ለፍጥነት ጥሩ ነው ጣጣ የለውም፣ ጭቅጭቅ የለውም ፣የጨረስከውን ጨርሰህ ወደ አንድ አቅጣጫ ታወጣለህ፣ ማሰር ያለብህን አስረህ እንደማለት ነበር። ያ መንገዱን ቢያቃልልንም <<ለኦሮሞ ሌላ ጠላት፣ ለኦሮሞ ሌላ ቁስል ፣ሌላ ቂም ሌላኛው አካል ላይ ይፈጥራል>> ብለን ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ አብዮት አይበጀንም፣ አያዋጣንም ተብሎ ነው ተጠንቶ የተተወው። ይህ አማራጭ እንዲቀር የተደረገው።
ሁለተኛው በevolutionary መንገድ ለውጥ ማምጣት ነው። ቀስ በቀስ። ያም <<ሰዎቹ ጉልበት ስላላቸው፣ ስልጣን ስላላቸው  easily መልሰው ሊያፈርሱን ስለሚችሉ፣ የሚላላክላቸው ስለማያጡ፣ ከኛ ውስጥም የሚላላክላቸው ብዙ ስለሆነ፣ ብዙ ሰልፍም ስላለ፣ ግዜ ከሰጠናቸው ደግመው regain  ማድረግ ይችላሉ>> ብለን በevolutionary መንገድ መለወጥ አይቻልም ተባለ።
ሶስተኛው ለውጥ ማምጫ መንገድ reform ነው reform ትንሽ ፍጥነትም አለው። structurally ነገሩን ለመቀየርም የተመቻች መንገድ አለው። in between ስለሆነ። ሌላውንም ህዝብ ሳያስደነብሩ፣ ዘመድ እያበዙ፣ እያፈሩ፣ የኦሮሞን ጥያቄና ፍላጎት በreform መንገድ መመለስ እንችላለን ተብሎ ነው reform የተመረጠው። ይህ ነው በ 2009 በድርጅት conference ወስነን የገባንበት ይሄን ሪፎርም።  basically ብዙ ሪፎርም አለ ነገር ግን ሪፎርሙን በሙሉ መንገድ ለማካሄድ ኦሮሚያ ውስጥ መጀመርያ ላይ ሰዎቹን ለማስደንገጥ፣ እረፍት ለመንሳት አከጀዳ ለነሱ ለማቀበል፣ እነሱን corner ለማድረግ፣ ብዙ ነገር አድርገናል። የመሬቱን ታስታውሳላችሁ፣ የማዕድኑን ታስታውሳላችሁ፣ የህገ ወጥ ንግድን ታሳታውሳላችሁ፣ ስለ ኮንትራባንድ ታስታውሳላችሁ፣ ስለ አዲስ አበባ ታስታውሳላችሁ፣ ስለ አፋን ኦሮሞ ብዙ አጀንዳዎችን ፈጥርን እረፍት ለመንሳት።
እእእእ ቄሮ ስለምትሉትም፣ ትንሽ ያው እነ ፍቃዱን እና እሱን አያካትትም እንጅ እኔ ቄሮ ነኝ። ይህን ቄሮን ወደድክም ጠላህም ኦህዴድ ነው የፈጠረው። እዚህ ውስጥ ያላችሁ young የሆናችሁትን ያሳየን ኦህዴድ ነው። ትምህርት ቤት በሙሉ ኦሮሚያ እንዲከፈት ተደርጎ እንዲማር የተደረገው በኦህዴድ ነው። የዚህ ዘመን ቄሮ conscious ስለሆነ fearless ሆኖ እንዲሄድ ያደረገው ስለ ተማረና conscious ስለሆነ ነው።
So, አብዮቱ በሚካሄድበት ግዜ በነበሩት አመታት፣ ብዙ ነገሮች አሉ ማለት ነው ወደፊት በታሪክ የምንፅፈው። ሰልፍ እየበተንም እያወጣንም ነበር ማለት ነው። አሁን ሁሉም ሰው እንዲህ አድርገን፣ እንዲያ አድርገን እያለ የሚያወራው አይደለም ማለት ነው። ከውጭም ከውስጥም ሁሉንም coordinate አድርገን ቁማሩን በደንብ ነው የተጫወትነው። ቁማሩን ስለተጫወትን ነው ነው የበላነው መጨረሻ ላይ፣ እንጂ በስጥታ የሰጠን ሰው፣ እባካችሁ እንጅ ምነው ብሎ የሰጠን የለም። ይህ clearly መታወቅ አለበት።
ፖለቲካ ደግሞ እናንተ ሰዎች ተንኮል ነው ሌላ ነገር አይደለም፣ ምን ያክል ተንኮል ትችላለህ ነው፣ ምን ያክል በ intrigue መጫወት ትችላለህ ነው፣ ምን ያክል power calculusሷን properly calculate አድርገህ መጫወት ትችላለህ ነው። ልክ ፍቄ እንዳለው በስሜት አይቻልም በስሜት እማ ተሞክሯል hundred years, ማሸነፍ የሌለው ትግል ብዙ አድርገናል፣  ማሸነፍ የሚችል ትግል ያመጣነው calculate ተደርጎ ስለተሰራ ነው ማለት ነው። ዘመድ ለማብዛት calculate ተደርጎ ብዙ ነገር ተሰርቷል፣ ደቡብ ብዙ ተሱርቷል፣ ባህርዳር አባይ ተኪዶ ብዙ ሰርተናል፣ ብዙ ነው ማለት ነው፣ የምንችለው convince አድርገን፣ ያልቻልነውን confuse አድርገን።
አሁን የሚያስቸግረው ምንድነው ሌላው ሰው ለምን confused ሆነ ብላችሁ ትጨነቃላችሁ ፣ ምን አገባችሁ? በእንደዚህ አይነት ጨዋታ ነው መጨረሻ ላይ ህወሃት ወደሚሄድበት ግራ ገብቶት ያሰለፈውን ሃይል ሁሉ ከእጁ አውጥተን፣ ደቡብንም ከእጁ አውጥተን፣ የአማራን ፓርቲንም ከእጁ እውጠተን፣ እኛ ውስጥም የሚላላኩትን መርምረን አባርረን፣ አባርረን ነው ራሳችንን አፅድተን ተሰልፈን አማራጭ አሳጥተነው ወደ ምርጫ እንዲገባ የተደረገው። ህዝቡ ተደራጅቷል፣ አብዮት ነው ያለው፣ እሳት ነው እየነደደ ያለው፣ internally ደግሞ እሱ የሚንጠለጠልባቸውን ሁሉ በትነንበት አንድ ሰው እንዳይኖረው አድርገን የኛ ሰው ሲወጣ እና ሲገባ የሚያወራውን ሁላ እእእእ የምንችለውን በምንችለው።
አሁን የቤት እመቤት ነን ማለት ነው፣ seriously ማለት ነው፣ እንዲህ በዋዛ አልመጣም፣ ምክንያቱም የሚላላክ ብዙ ስላለ ነው ዛሬም ለመላላክ ሰልፍ የገባው፣ መላላክ ደግሞ ከኛ በላይ የሚችል የለም። so wisely ነው ማለት ነው የተቀበልነው፣ በጨዋታ ነው የተነጠቅነው (×2)። ፓርቲ ሰራን ይሄው፣ የሰራነው ፓርቲ እንደ ምሁር እንድትረዱ የምንፈልገው፣ ጅማሬውም ፍፃሜውም የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም እና ፋይዳ እና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን ጥቅም እና ፋይዳ ማስከበር ነው። ከዚህ ውጭ ምንም አላማ የለውም።
ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራሙ ፍቃዱ እንዳብራራው የመተዳደርያ ደንቡ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም እንዲመልስ ነው የተሰራው፣ እንዳትሳሳቱ የመጀመርያው እና ዋናው በዚህ ፓርቲ ውስጥ ያለን ተሳትፎ በህዝብ ብዛት እና በብሄር ብዛት እንዲሆን ተብሎ ነው የተቀመጠው። በፊት በዛ መላላክም ተሳትፎአችን ትንሽ ነው፣ አሁን ተሳትፎአችን በህዝባችን ልክ ዴሞክራቲክ በሆነ መንገድ እንዲሆን አደረግን ማለት ነው፣ አንደኛው ይህ ነው። ሁለተኛው የፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትሉ በምርጫ ጉባኤ ይካሄድ ብለን ነው የወሰንነው። So, አርባ ፐርሰንት ቢሆን እኛ ያለን ተሳትፎ በህዝብ ቁጥራችን ልክ ፓርቲው ውስጥ ያለን፣ ያ አርባ ፐርሰንት ካልመረጠህ ፕሬዝዳንት (ሊቀመንበር) አይደለም ምክትልም ለመሆን አትችልም ማለት ነው።
ስለዚህ የሃገር ባለቤትነትን ጉዳይ ከስልጣን ጋርም ያለውን በአሰራር ዘግተነዋል ማለት ነው። ብልፅግናን minimum ካሁን በኋላ የሚመራው ኦሮሞ መሆን አለበት ካልሆነ ደግሞ ኦሮሞ ሊፈቅድለት ይገባል። እንደዚያ አይነት ፓርቲ ነው የገነባነው።
ሁለተኛ ያነሳችሁት አፋን ኦሮሞን የተመለከተ አንድ ዳታ ልስጣችሁ። በ87 አፋን ኦሮሞ በ12 በ13 % ከአማርኛ በታች ነበር። አሁን አፋን ኦሮሞ ኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛን ከ 10% በላይ ይበልጠዋል። የአማራን ብሄር አላልኩኝም እኔ አፋን ኦሮሞ በተናጋሪ አማርኛ ቋንቋ ይበልጣል ነው ያልኩት። አማርኛ ነው አፋን ኦሮሞን በተናጋሪ ብዛት የሚበልጠው ብላችሁ ካሰባችሁ ትልቅ ስህተት ውስጥ ናችሁ። ቤንሻንጉል 37% አፋን ኦሮሞ ይናገራል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ሶማሌ ውስጥ፣ ነው ያልኩት። አማርኛ እየሞተ ነው የመጣው፣ ወደታች ነው እየሄደ ያለው።   So,  አፋን ኦሮሞ ይዋጣል ይሞታል ምናምን የምትሉ፣ ኦሮሞ ይዋጣል የምትሉ ስነስርዓት ያዙ። ኦሮሞ እኮ የሆነ handicapped ነገር አይደለም ኦሮሞ፣ ወይም ክኒን አይደለም ኦሮሞ። ድሮም አልተዋጠ፣ በአፋኝ ስርዓት ውስጥም አልተዋጠም፣ forget it። ኦሮሞን ልክ እንደ wheelchair እነሱ በ AC ውስጥ oxygen ሰጥተውት፣ መርፌ ወግተው እያኖሩት እንዳሉ አስመስለው የሚያወሩልን እነሱ እየዋሹ ነው፣ እየዋሹ ነው ያሉት። ኦሮሞን እኔ አላኖረውም አንተም አታኖረውም ፣ እኛ ላይ  depend አያደርግም የሱ ኑሮ፣ ይህን እወቁ። So, እዚህ state building ውስጥ የሚወጡ ህግጋት፣ የሚወጡ ስትራቴጂዎች፣ የሚወጡ ስርዓቶች፣ የሚወጡ ሲስተሞች ነው ኦሮሙማችንን በውስጡ treat የምናደርገው፣ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰብ ወደ center የምናመጣው።
አምስት  ቋንቋ ስንል ለሌላው ክልል ተጨንቀን አይደለም፣ ትግርኛና አማርኛ already አሉ። ፌዴራል ውስጥ በቂ ነው ያለው። ሶስት አምጥተንበት ለማውረድ ነው። ገባችሁ ለማመጣጠን። ሁለቱ almost 90% አላቸው፣ አሁን ሁሉም institution ውስጥ፣ አሁን እኛ የፌዴራል ቋንቋ እናድርግ ስንል ሶማሌኛ፣ ኣፋርኛ፣ እና አፋን ኦሮሞ ስንል በኋላ ፕሮፖርሽናል ይሆናል ማለት ነው። የፌዴራል public service፣ ፕሮፖርሽናል ሲሆን ሶስቱ ይገባል ማለት ነው። ሁለቱ የሚጨመር ነገር የለውም ማለት ነው ይወርዳል እንጂ! ሶስቱ ናቸው የሚገቡት ማለት ነው። So, እኛም እንደኛ፣ ሁሉም እንደ ራሱ፣ ይኖረዋል ማለት ነው። ስለዚህ የሚወጡ ሲስተሞችን እና ህግጋትንም በዛ መንገድ ነው። ሃጂ የአፋን ኦሮሞ ጉዳይ የእኛን መሞት አይፈልግም።  አፋን ኦሮሞ ተመልሷል ሰዎች።
የቋንቋ ፖሊሲ ከሁለት ወይም ከሶስት ሳምንት በኋላ ለካቢኔ ይቀርባል። ተጠናቅቋል። ለፌዴራል ካቢኔ ማለት ነው። ፓርቲዎች ወስነዋል። ስድስት ክልሎች ነው እንዲወስኑ የምንፈልገው። እነዚያ ስድስቱ ክልሎች ደግሞ አሁን እንደ ድሮው አይደለም ፓርቲው ስር ነው የሚተዳደሩት። ብልፅግና ስር፣ ስለዚህ ህግንም ሆነ ምንንም ለማስተካከል ምርጫ ድረስ መድረስ ያለብን አይመስለኝም። ስለዚህ ብልፅግና የአፋን ኦሮሞን ጉዳይ መልሶታል።
ስለዚህ ለstate building ዕድል አለን፣ ያለንን ስልጣን ተጠቅመን፣ እኛን የምትመስል state መገንባት እንችላለን ነው አንደኛው፣ ብልፅግናን ለዚህ ነው እየገነባነው ያለነው። ሁለተኛው ብልፅግናን እየገነባን ያለነው ለnation building ነው፣ የቀድሞው (የሰዎቹ) nation building aborted ሆኗል። መቶ አመት ተሞክሮ፣ አንድ ብሄር፣ አንድ ሃይማኖት ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ሃይማኖት የሚባለው ወድቋል። አሁን እኛ እንደ ኦሮሞ እኛን የምትመስል ኢትዮጵያ መልሰን reconstruct ለማድረግ ፣ superstructure ውስጥ  ኦሮሞነትን ለመትከል እድል አለን ማለት ነው። እሱ ላይ መስራት እንችላለን። እንደምታውቁት ድንበሩም አልቋል አዋጁም ተጠናቋል፣ አዋጁ ግን ምንም አይጠቅመንም እውነቱን ነው የምነግራችሁ፣ ብናፀድቀውም ለስም ነው እንጅ long lasting solution አያመጣም።
አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን።
ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው የፌዴራሉን መንግሥት ኦሮሚያ ስለተቆጣጠረው ነው። የፌዴራሉ መንግስት መከፈል አለበት ብለን ከሌላው ህዝብ ጋር ተጨንቀንበት እየሰራን ነው።
ስለዚህ ይሄንን ስናደርግ irrelevant ትሆናለች አዲስ አበባ። ሶስተኛ አዲስ አበባ ላይ ያለው ሌላ economic option መፍጠር ነው። ለዚህ በቂ ዝግጅት አድርገናል። አሁን በቅርቡ ለጨፌ እናቀርባለን እድሉ ስላለን። ይሄንን አድርገን ነው እንጅ የምንፈታው ሰውም ማባረር አንችልም። ሰው መግደልም አንችልም። ማጫረስም አንችልም። እንዲህ አድርገን ነው ነገሩን የምንፈታው ብለን ነው እየሄድን ያለነው። ስለዚህ ከፈጣሪ ጋር፣ ከእውነት ጋር፣ እየሰራን ካለነው ስራ ጋር፣ ከእናንተ ጋር ከሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ጋር ብልፅግና ይቀጥላል። የኦሮሚያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!
ምስራቅ አፍሪካን እንመራለን! ኢትዮጵያን እንደምትመቸን አድርገን እንገነባታለን! እየገነባናትም ነው። ስለዚህ መክዳት፣ መከዳት የሚባለው ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፣ እንዲህ አይነትም ቦታ የለም፣ እንዲህ አይነት አመለካከትም የለም ይህንኑ ለማለት ነው በርቱ! በግልፅ ስለተናገራችሁን አመሰግናለሁ ልላችሁ እፈልጋለሁ።
Filed in: Amharic