>
5:14 pm - Thursday April 20, 3634

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ (ዶቼቬሌ - አማርኛ)

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ

ዶቼቬሌ – አማርኛ


የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገለፀ ። ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉች ላይ በመድረስ ነዉ። የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ጉባዔዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል።

 

የኦሮምያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለክልሉ የመንግሥት ቴሌቭዥን «OBN» ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብ ነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል። እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል። አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።

Filed in: Amharic