>

ብልፅግና እንዲስፋፋ ኦርቶዶክስን የማጥፋት በሰነድ የተደገፈ መንግስታዊ ሴራ? (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

ብልፅግና እንዲስፋፋ ኦርቶዶክስን የማጥፋት በሰነድ የተደገፈ መንግስታዊ ሴራ?

ብርሀኑ ተክለያሬድ

ብዙ ወገኖች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የታወጀው እልቂት ስሜታዊ በሆኑና ማሰብ በማይችሉ ወጣቶች የተደረገ እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ። ይህ ሞኝነት ነው  ቀድሞ በህወሓት “ኦርቶዶክስና አማራን ማጥፋት” ተብሎ በሰነድ የተዘጋጀ አሁንም በብልፅግና ፓርቲ “ሀብት ማፍራትን እንደ ኃጢአት የሚቆጥር ሐይማኖት ባለበት ሀገር ውስጥ
 ብልፅግናን ማስፈን ፈታኝ ነው” ተብሎ በኦርቶዶክሳውያን ላይ መንግስታዊ የክተት አዋጅ ከታወጀ ቆይቷል።
ከሰሞኑ የተፈጠረውን እልቂት ተከትሎም “መንግስት ለምን አልተከላከለልንም?” ብሎ የሚጠይቅ አካል ካለ መልሱ “የርዕዮተ አለም ጠላቱ ማን ሆነና” ነው። እናም ዛሬ ቤተክርስቲያን ሞቅ ያለው ሁሉ ክብሪቱን የሚጭርባት፣ታጣቂው ሁሉ የሚተኩስባት፣ሹመኛው ሁሉ  ቦታዋን እየነጠቀ የሚጨቁናት፣ምእመናኗ የሚታረዱባትና የሚፈናቀሉባት ተቅበዝባዥ ሆናለች።
ከዚህ በታች ያያያዝኩት ሰነድ ብልፅግና ፓርቲ በ2012 ዓ/ም ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተዘጋጀ ስልጠና ላይ የቀረበ ማሰልጠኛ ሰነድ ነው። በዚህ መንግስታዊ ሰነድ ላይ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ለብልፅግና የማትመች የለውጥ ጎታች ተደርጋ ተስላለች።  ይህን ሰነድ ያሰለጠነ መንግስትና የሰለጠነ ካድሬ በቤተክርስቲያን ላይ ምን ሊያደርሱ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ ነው እናም የሆነብን ሁሉ ሆኖብናል፤ወደፊትም ይሆንብናል።
እኛስ?
እኛማ ሞቆናል፤ በቀንድ አውጣ ቀፎአችን ለሽሽ ብለን ተኝተናል፤ስራችን ለሰነዱ አስፈፃሚዎች በየምክንያቱ ካባ ማልበስ ሆኗል፤ከምእመናን ሰቆቃና እልቂት ይልቅ ተወስዶ የተመለሰልን ህንፃ የሚያስፈነድቀን ህፃናት ሆነናል፤በመከራው ውስጥ እንኳን አንድ መሆን አቅቶን ስንፈራረጅ ስንከፋፈልና ስንቧደን እንውላለን፤ለፍርሀታችንና አድርባይነታችን “ስንሞት እንበዛለን” “አታሸንፉንም” የሚል ማልበሻ ጥቅስ እየወነገርን ምዕመናንን በማሳረድ ላይ ነን።ይህ ሁሉ እየሆነብንም አልነቃንም። መቼ ይገባናል?
ንቃህ መዋቲ!!!
Filed in: Amharic