>

የአክራሪ እስልምና ስትራቴጂዎች በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተቃጣ ሴራ...!!!! (እውነት ሚድያ)

የአክራሪ እስልምና ስትራቴጂዎች በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተቃጣ ሴራ…!!!!

እውነት ሚድያ

 

‹‹እኛ እንታገላለን፤ ልጆቻችን ያሸንፋሉ፤ የልጅ ልጆቻችን ዓለምን በእስልምና ይወርሳሉ!›› አላሁ አክበር!!!
 
✍️ አክራሪ እስልምና ክርስትናን አዳክሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመስፋፋት፣ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሲል የተለያዩ ስልቶችን (strategies) ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተጋልጧል፤ በተለይ በ2009 ዓ.ም ያዘጋጁት ምሥጢራዊ ሰነዳቸው በእጃችን ገብቷል!
✍️ በሰው ኃይል ልማትና ግንባታ፡- በልዩ ሁኔታ የሚሰለጥኑ አክራሪ ወጣቶችን ማፍራት!
✍️ በሕዝብ ቁጥር ለመብለጥ መጣር፡- አንድ ወንድ በርካታ ሴቶችን (ቢቻል ክርስቲያኖችን) ያግባ! 
✍️ ምጣኔ ሀብትን በበላይነት መቆጣጠር፡- ለሁሉም ሽጥ፣ ከሙስሊም ብቻ ግዛ! 
✍️ ቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ቦታዎችን መያዝ፡- ከዚህ በኋላ ሀገርን መምራት ያለብን እኛ ነን!
✍️ በሚዲያ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት፡- በብሮድካስትም፣ በማኅበራዊ ሚዲያውም!
✍️ ነባር የክርስቲያን-ሙስሊም ማኅበራዊ ትስስሮችን በመቆራረጥ አዲስ የአክራሪነት ሰንሰለት መፍጠር፡- በተለይ የወሎ ሙስሊም ዓይነት ‹‹ቀዝቃዛ ሙስሊሞችን›› ለአክራሪነት ማንቃት!
✍️ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ያሰቡ በመምሰል አዳዲስ ክልላዊ መዋቅራት እንዲፈጠሩ መደገፍ፡- የኦሮምያ፣ የትግራይ ለሚባሉት ቤተ ክህነቶች ዋና ደጋፊ ሆኖ መቅረብ!
✍️ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነቶች፡- ከኢትዮጵያም አልፈው ሀገሪቱን የሙስሊም እንደሆነች ለሌሎች የዓለም ሀገራት ማሳየት!
✍️ ይህ ሁሉ ካልተሳካ ደግሞ የኃይል እርምጃዎችና የጭካኔ ድርጊቶችን መፈጸም ዋና ዋናዎቹ ናቸው!  
*  *   *
ከዚህን በፊት ባቀረብንላችሁ ጽሑፋችን አረባዊ ጠባይን የተላበሰው አክራሪ እስልምና ከኢትዮጵያውያኑ ሰላማዊ ሙስሊሞች እጅግ የተለየ መሆኑን፣ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ላይ የደቀናቸውን አደጋዎች ጠቁመን ነበር፡፡ በዚህኛው ጽሑፋችን ደግሞ የዚህን አክራሪ እስልምና ስትራቴጂዎች (የሚከተላቸውን የጥቃት ስልቶች) በአጭሩ ለማስቃኘት እንሞክራለን፡፡
አክራሪ እስልምና ክርስትናን አዳክሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመስፋፋት፣ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሲል የተለያዩ ስልቶችን (strategies) ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይልቁንም በኢትዮጵያ ደረጃ ሥር ሰድዶና ተደላድሎ ለዘመናት የዘለቀውን ኦርቶዶክሳዊነት መሸርሸር በቀላሉ የሚሳካ ስላልሆነ በአግባቡ የተጠና፣ አዋጭንቱም ሃይማኖታዊ ብቻ ሣይሆን ሳይንሳዊም በሆነ መልኩ የተመሰከረለትን ልዩ አካሄድ መከተል እንደሚገባቸው በጥንቃቄ ያጤኑ ይመስላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምናስተውላቸው አፈንጋጭ አመለካከቶችና ጽንፈኛ አካሄዶች በተቀናጀ መልኩ እየተመሩ ሲፈጸሙ የቆዩ የእነዚሁ ስልቶች መፈጸም ውጤቶች ናቸው፡፡
በተለይ በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሚገኘው የአክራሪ እስልምና ክንፍ ተዘጋጅቶ ድንገት ሾልኮ የወጣው  የ25 ዓመታት ስትራቴጂ ሰነድ በሦስት ደረጃዎች የተከፈለ ነው፡- የአጭር ጊዜ (5 ዓመታት)፣ የመካከለኛ ጊዜ (15 ዓመታት) እና የረጅም ጊዜያት (እስከ 25 ዓመታት የሚደረስባቸው)፡፡ ይህንኑ ምሥጢራዊ ሰነዳቸውን መነሻ በማድረግና በተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ በመመርኮዝ በመተግበር ላይ ያሉትን ስልቶቻቸውን እንደሚከተሉት አደራጅተን ለማስቃኘት እንሞክራለን፡-
1) የሰው ኃይል ልማትና ተቋማዊ አቅም ግንባታ
ሰነዱ በዚህና ቀጥለው በተቀመጡት ርእሰ ጉዳዮች ደረጃ ተከፋፍሎ ባይቀርብም የበለጠ ግልጽ ለማድረግ በዚህ መልኩ ማደራጀቱ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የስትራቴጂ ሰነዱ በሦስቱም ደረጃዎች ቀዳሚውን ትኩረት የሚሰጠው በሰው ኃይል ልማትና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፍ ላይ ነው፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች ይህንን ዘርፍ የሚመለከቱ ናቸው::
በመጀመርያውና በሁለተኛው እርከኖች ውስጥ፡- 
• ለዘመናት ተለያይተው የቆየ የሙስሊሞችን አንድነት ማረጋገጥ (ዶ/ር ዐቢይ ወደ ሥልጣን እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ውሳጣዊ ክፍፍሎች እንደነበራቸው ይታወሳል፤ አሁንም ድረስ ወሃቢይ እና አል-ሓበሽ በሚሉ የእስልምና አረዳዶች ከፍተኛ ልዩነት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል)፤
• እስካሁን ድረስ በእስልምና ላይ የተደረጉ ተጽዕኖዎችን የሚያጠና፣ የሚያሳውቅና የሚያስፈጽም የሰለጠነ አካል ማዘጋጀት፤
• የእስካሁኑን የአካሄድ ስህተቶችን የሚያጣራ የኡላማ ቡድን በአስቸኳይ ማቋቋም፣ ቀጣይ ሂደቶችንም የሚከታተል አስተባባሪ ቢቻል ከውጭ ማስመጣት፤
• ለእስልምና መርሖዎች ተቆርቋሪዎችን ማዘጋጀት፤
• በየአከባቢው የሚንቀሳቀሱትን ሌሎች ነሷራዎችን [ኢ-እስላማዊ ቡድኖች?] በትኩረት በመከታተል በኡማዎች ተጽዕኖ ሥር እንዲሆኑ ማድረግ፤
• ኡላማዎችና ኡስታዞች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡና እስከ እስላማዊ ዳዕዋ የሚረዱ ሙዕሚኖችን እንዲያሰለጥኑ ማድረግ፤
• በእያንዳንዱ መስጊድ ውስጥ ወጣቶችን የሚያደራጁ አስተባባሪዎችን መመደብ፤
• 200 ሺህ ወጣቶችን በዳዕዋ ማሰልጠን፤
• ከ10ኛ ክፍል በላይ ባሉት ተማሪዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ፤
• በዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ያሉት ተማሪዎችና መምህራን ለእስልምና ትኩረት እንዲሰጡ በትኩረት መሥራት፤
• ወጣት ሙስሊሞችን ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ በሕግ፣ በሳይንስና በምህንድስና ማሰልጠን፤
• እስላማዊ አስተምህሮና ሥነ ምግባርን ተከትለው በዝቅተኛ ዋጋ የሚያስተምሩ ሙዓለ ሕጻናትን በከተሞች ውስጥ  ማስፋፋት፤
• ከመድረሳ እስከ ኮሌጅ ድረስ የቁርዓን ትምህርት ቤቶችን መክፈት፤
• እንደ አልነጃሺ መስጊድና ድሬ ሼክ ሁሴን ያሉትን ጥንታዊ የእስልምና ቦታዎችን ዩኒቨርስቲ ተቋማት አድርጎ መገንባት (ዓለም አቀፋዊ ሥልጠና ማእከላት ማድረግ)፤
• የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ቁጥር ቁጥር በሦስት እጥፍ ማሳደግ፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡
ሦስተኛው (ከፍተኛው) የስትራቴጂው አካል ግን ሙሉ በሙሉ በዚህ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡-
• የተደራጀ፣ የተገነባና የታጠቀ እስላማዊ ተቋም ማየት፤
• በዕውቀት፣ በዲፕሎማሲ፣ በልማትና በተለያዩ መንገዶች ከ15-20 ዓመታት ውስጥ ለውጥ ሊመጣ ካልቻለ ለአላህ የመጨረሻው ጅሃድ (ይፋዊ ጦርነት) ራስን ማዘጋጀት፤
• በእያንዳንዱ ገጠር ከተማና አንድ ሙስሊም ባለበት እንኳን ሳይቀር መስጊድ ገንብቶ በሀገሪቱ ያሉትን የመስጊዶች ቁጥር በ50 እጥፍ ማሳደግ፤ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
2) በሕዝብ ቁጥር ለመብለጥ መጣር (Demographic /Population Conquer):
በዚህ ዘርፍ በግልጽ ከተጻፉት ስትራቴጂዎች ቀዳሚው፡- ‹‹ከምንጊዜውም የበለጠ የሀበሻ ሴቶችን [በዚህ አገባቡ ክርስቲያን የሆኑትን ለማለት ነው] ወደ ውጪ ሙስሊም ሀገራት በመላክ ሙስሊም የማድረግ ሥራን ከኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር መሥራት›› የሚል ነው፡፡ ይህ በከፍተኛ ደረጃ ሲሠሩበት የቆየ፣ አሁንም አጠናክረው የቀጠሉበት ስልታቸው ነው፡፡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ሆነው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የዕለት ጉርስ፣ የዓመት ልብስ ማሟላት ያቃታቸው ክርስቲያን እህቶቻችን በሙሉ የዚህ ሤራ ዋነኛ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ስትራቴጂው የተቀየሰው እዚህ ባሉት አክራሪዎች ብቻ ሣይሆን በአረብ ሀገራቱ ባሉት ተቀባዮችና አስላሚዎች ጭምር ስለሆነ ሌላው ሰው ወደ ውጭ ለመሄድ ከሚያደርገው ጥረት አንጻር ቀለል ያለ ሂደት ተዘርግቶለታል፡፡ ይህንን ሤራ በአቀባይና ተቀባይ መካከል ሆነው የሚያጧጡፉት ደግሞ ኤጀንሲዎቹ ናቸው፤ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት ጉዞ አጀንሲዎች ሙስሊሞች የመሆናቸውም ምሥጢር ይኸው ነው፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጪ መሄድ ላልቻሉት እህቶቻችን ደግሞ ሌላ አማራጭ ወጥመድ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ አንድ ሙስሊም ወንድ (የማስተዳደር አቅሙ እስካለው ድረስ) እስከ ሰባት ሚስቶች ማግባት እንደሚችል ቁርዓናዊ አድርጎ በማስተማር ወንዶቻቸውን ካሳመኑ በኋላ ክርስቲያኖቹን ለሚስትነት እንዲያጩአቸው፣ ከዚያም ሴቶቹ ሙስሊም እንዲሆኑ መገፋፋት ሌላኛው ስልታቸው ነው፡፡ በዚህ መልኩ ከኦርቶዶክሳዊነት አስኮብልሎ፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ ተከብሮ የኖረውን ማተብ አክባሪነት አስለውጦ፣ ሃይማኖትን አስክዶ ወደ እስልምና ማምጣት ደግሞ በቀላሉ እንደማይሳካ ስለሚያውቁት እጅግ አጓጊ ማማለያዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ ለዚህም ሲባል በጀርባ ሆነው ከሚያማክሯቸውና ከሚደግፏቸው የአረብ ሀገራት ከፍተኛ በጀት መድበው ይሰራሉ፡፡ በዚህ መሠረት በተለመደው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃና የኑሮ ትግል ላይ ያሉት እህቶቻችን አማራጭ ሲያጡ የወጥመዱ ሰለባ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ከዚህን በፊት አይተውት የማያውቁት ገንዘብ፣ ንብረትና ቅንጡ አኗኗርም እንደ እጅ መንሻ ሲቀርብላቸው፡- ‹‹መችስ እግዚአብሔር የልቤን ያውቃል፤ ይህንንስ ያመጣው እርሱ ባወቀ፣ በልዩ ጥበቡ ሊረዳኝ አስቦ ሊሆን ይችላል›› በሚል አጓጉል ፈሊጥ ውስጥ ይገባሉ፤ በጥፋቱ ወጥመድ ውስጥ አንገታቸውን ለማስገባትም ይስማማሉ፡፡
ቀጣዩ እርምጃ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ወሊድ ምጣኔ ዘዴ (Family Planning Method) አከታትለው እንዲወልዱ ማድረግ ነው፤ በእነርሱ አስተሳሰብ (ደግሞም በአብዛኛው ተሳክቶላቸዋል) ሴቶች ቶሎ አንድ ልጅ ካልወለዱ ልባቸው የመሸፈት ዕድሉ የሰፋ ሲሆን ደጋግመው ሲወልዱ ደግሞ ከመረጋጋትም አልፈው ‹‹ከዚህ በኋላ ወደየትም መሄድ አልችልም›› የሚል ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህ ጥበብ ተጠቅመው ትተው ወደመጡበት ሃይማኖትና ማኅበረሰብ ዳግም እንዳይመለሱ ያደርጓቸዋል፡፡
ሴቶቹም አንዴ ማተባቸውን በጥሰው፣ ሃይማኖታቸውን ክደው ወዳሰቡት ትዳር አምርተው ልጆችን ደጋግመው ከወለዱ በኋላ ግን ያሰቡት ሁሉ ሀሰት መሆኑን ይገነዘቡታል፡፡ ቃል የተገባላቸው ገንዘብና ንብረትም የሌሎች ስድስት ሚስቶችና ተጨማሪ ቅምጦች ጭምር መሆኑን ይረዱታል፡፡ ይደረግላቸው የነበረው ማባበያና ቅንጦታዊ ገጸ በረከትም በሂደት እየቀጣጠነ ይሄዳል፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደኋላ ለመመለስ ይቸገራሉ፡- ላልተጨበጠ ሀብት ማተባቸውን እንደበጠሱ ሕሊናቸው እየወቀሰ ከመሰቃየታቸውም በላይ አንዴ ጥለውት የወጡት ሃይማኖትና ማኅበረሰብ እንደሚያገልላቸው ያስባሉና፡፡ እናም ያስጀመሯቸውን ‹‹ልጅ ማምረት›› ፕሮጀክት አጠናክረው ይቀጥላሉ፤ ልጆቹም በአባታቸው እምነትና ሥርዓት መሠረት ያድጉና የእስልምናውን ተከታዮች አኀዝ ለማጉላት ሚናቸውን ይወጣሉ ማለት ነው፡፡
አክራሪ ሙስሊሞቹ በወሊድ የሕዝብ ቁጥራቸውን ለመጨመር ከሚያደርጉት ተፈጥሯዊ ጥረት በተጨማሪ ‹‹በዝተው ለመታየት›› የሚያደርጓቸው የታይታ አሰላለፎች (Visibility Demonstrations) ሌላው የዚህ ስልት አካል ነው፡፡ በተለይ እንደ አረፋ በመሳሰሉት ዓመታዊ ክብረ በዓሎቻቸው ላይ ከመላው የገጠር አከባቢዎች መጥተው በአቅራቢያ ወዳሉት ትልልቅ ከተሞች በመምጣት አንድ ላይ ይሰባሰቡና አስቀድመው ባመቻቸቱት የሕዝብ ሚዲያ ውስጥ ይታያሉ፡፡ በዚህ መልኩ በቀጥታ ሥርጭት የሚመለከቷቸው ሕዝብና መንግሥትም፡- ‹‹በአንድ ከተማ ይህን ያህል ብዛት ያለው ሕዝበ ሙስሊም ካለ በሌሎች ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ያሉት ቢጨመሩማ እንዴት ይበዙ!›› እያሉ ይገረማሉ፤ የተፈለገውም ይኸው ስለሆነ ድራማው የመጀመርያ ግቡን መታ ማለት ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ሀገሪቱ በምታደርጋቸው ብሔራዊ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ሂደቶች ውስጥ ጉልሕ ተሳትፎና ከፍተኛ የሤራ እንቅስቃሴ በማድረግ ‹‹የሚፈለገው አኀዛዊ ውጤት›› እንዲመጣ መጣር ነው፡፡ በስትራቴጂ ሰነዳቸው ላይ በግልጽ ከተቀመጡት አንዱ፡- ‹‹በኢትዮጵያ ስታቲስቲካዊ መረጃ የእስልምና የበላይነት [እንዲረጋገጥ]….ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የሚሠራ ቡድን ማቋቋም…›› የሚል ነው፡፡ ይልቁንም አብዛኞቹ አስፈጻሚ አካላት ሙስሊሞች በሚሆኑባቸው አካባቢዎች ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም በተጨባጭ ካለው የቤተሰብ ቁጥር በላይ ማስመዝገብና ከአንዱ ወደ ሌላው እየንተቀሳቀሰ በተደጋጋሚ እንዲቆጠር ማድረግ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ተሳክቶላቸው የሚፈልጉትን ቁጥር በአከባቢው ማስመዝገብ ቢችሉ እንኳን በብሔራዊ ደረጃ (እንደ ሀገር) ተጠናቅሮ የሚመጣው አኀዝ ቁጥራቸውን ስለሚያኮስሰው ‹‹ቆጠራው በአንዳንድ ቦታዎች በአግባቡ አልተከናወነምና ውጤቱን አንቀበልም›› ብለው የህዝብ ተወካዮች ድረስ በይፋ ሲከራከሩ ሰምተናቸዋል፡፡ አስቀድመው ሲሠሯቸው የነበሩአቸውንም የአደባባይ ድራማዎች በማስታወስ፡- ‹‹የእኛ ቁጥር በየክብረ በዓላቱም ላይ እንደምታዩት ከሕዝበ ክርስቲያኑ በላይ ሆኗልና…›› ለማለት ሲዳዳቸውም ታዝበናቸዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ በተጠና መልኩ እያቀደ የሚያስፈጽም ቡድን እንዲኖር የሠሩት ደግሞ በዚሁ የስትራቴጂ ሰነዳቸው መሠረት ነው፡፡
የሕዝበ ሙስሊሙን ቁጥር ለማጋነን የሚደረገው ይህ ሁሉ ጥረት ወደ ቀጣዩ እርምጃ ለመሸጋገር ነው፡- የክርስትና አሻራ የነበረውን የሀገሪቱን አጠቃላይ ታሪካዊ ሥሪት ለመቀየር፤ ክርስቲያናዊ ሽታ ያላቸውን ባህላዊና ክብረ በዓላት ሥርዓቶችን መለወጥ፤ መንግሥታዊ አደረጃጀቶችንና የሥልጣን ክፍፍሎችን በአዲሱ የሕዝቡ ቁጥር አንጻር በመቅረጽ የአንበሳውን ድርሻ ለመያዝ፤ ሁሉንም ነገር ‹‹በሸሪዓ ሕግ መሠረት›› መዳኘት፤ በመጨረሻም ‹‹በእስላማዊ መንግሥት የምትመራ ሀገር›› (Islamic State) እንድትሆን መገፋፋት ነው፡፡
 3) ምጣኔ ሀብትን (Economy) በበላይነት መቆጣጠር
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ማንም በተግባር እንደሚያስተውለው አብዛኞቹን የንግድ ተቋማት የተቆጣጠሩት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ በየሰፈሮቻችን ያሉትን ጥቃቅን ሱቆችን እንኳን ባለቤትነታቸውን መታዘብ እንችላለን፡፡ ይህ በአጋጣሚና በግለሰቦቹ የሥራ ተነሳሽነት ብቻ የሆነ ነው ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ምጣኔ ሀብትን አስመልክቶ ከተቀመጡት አቅጣጫዎች መካከል ጥቂቶቹ፡-
• የንግድ ተቋማትን መግዛትና ማስፋፋት፤
• ከሙስሊም አጋር ድርጅቶች ጋር ለመሥራት የኢንቨስትመንትና ንግድ በሮችን መክፈት፤
• የሙስሊሞችን አክሲዮኖች ማደራጀት፤
• ክርስቲያናዊ ተቋማትን በመግዛት የራስ ማድረግ፤ የሚሉ ናቸው፡፡
በዚሁ አግባብ የሰፈር ሱቆችንና ሱፐር ማርኬቶችን አብዛኞቹን ከመቆጣጠርም አልፈው የዕለት ተዕለት ኑሮአችን የተመሠረተባቸውን አብዛኞቹን ዕቃዎችን ከውጭ የሚያስገቡት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ መሠረታዊውን ሥርዓተ አምልኮችን የምንፈጽምበትን (ሥርዓተ ቅዳሴ የምናከናውንበትን) ዘቢብ ጭምር ከውጭ የሚያስመጡት በብዛት እነርሱ መሆናቸው በብዙ መልኩ ያሳስባል፡፡ እነርሱም የቢዝነስ ጉዳይ ሆኖባቸው እንጂ ‹‹ከዚህ በኋላ ገንዘብ አንፈልግም፣ ዘቢብም አናስገባም›› ብለው ኦርቶዶክስን ለማጥቃት ቢነሱ መዳፋቸው ውስጥ እስካለን ድረስ መዘዙ ቀላል አይሆንም፡፡
ሙስሊሞቹ እርስ በርስ ምጣኔ ሀብታዊ ትስስራቸውን በማጠናከር የሀገሪቱን፣ ብሎም የዓለምን ኢኮኖሚ ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ጥረት የዋዛ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ እንኳን አንዱ ሙስሊም ከሌላው ሙስሊም ብቻ እንጂ ከሌላ እንዳይገዛ የንግድ መሥመሩን ጠርንፈው የያዙባቸው ስልቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- የሙስሊም ነጋዴዎችንና የእስላም ተቋማትን አድራሻ ብቻ ከነምርቶቻቸው የያዘ ‹‹ሐያት›› የሚባል የንግድ መረጃዎች መጽሐፍ (Trade Directory) አዘጋጅተው በዚያው አግባብ ብቻ እየተገበያዩ ነው፡፡ በራሳቸውና ሃይማኖታዊ ተቋሞቻቸው አማካይነት ከሚያደርጓቸው የግዥ ሥርዓቶች ባሻገር ተቀጥረው በሚሰሩባቸው መንግሥታዊና ኢ-መንግሥታዊ ድርጅቶች ውስጥ እንኳን የግዥ ዋጋ ማወዳደርያ ሰነድ (Performa Invoice) እንዲሰበሰብ የሚያደርጉት ከእነዚሁ እስላማዊ ግለሰቦችና ተቋማት ነው፡፡ በሀገሪቱ ያለው የግዥ ሥርዓት ደግሞ በአብዛኛው ዋጋ ማወዳደርያዎቹ ‹‹ሦስት መሙላታቸውን›› እንጂ  ‹‹ለምን ከእነዚህ ተቋማት እንደሆኑ›› አጥብቆ ስለማይመረምር ለመሰል አካሄዶች የተጋለጠ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ከመሰል ጥቃቅን አካሄዶችም ወጥተው ትልልቅ እስላማዊ የፋይናንስ ተቋማትን ጭምር ወደ መመሥረት ተሸጋግረዋል፡፡ ከዚህን በፊት ገጠራማ አካባቢዎችን መሠረት አድርገው ማይክሮ ፋይናንሶችን እየመሠረቱ በርካቶችን በብድርና ተያያዥ ጥቅማ ጥቅሞች ስም ሲያጠምዱ መቆየታቸው አይካድም፡፡ አሁን ደግሞ በሀገራችን ያለውን የሕግ ክፍተትና ሰሞንኛ ቀዳዳዎች እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ በሸሪዓ ሕግ መሠረት የሚሰሩ ‹‹እስላማዊ ባንኮችን›› በመመሥረት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ጽሑፍ እየተጠናቀረ ባለበት ጊዜ (ሚያዝያ 2012 ዓ.ም) እንኳን አራት እስላማዊ ባንኮች አስፈላጊውን ቅድመ-እውቅና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አግኝተው በምሥረታ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡-  ዘምዘም፣ ሂጂራ፣ ዛይድና የመሳሰሉት፡፡
በአጠቃላይ በእነዚህና መሰል ሁኔታዎች ምጣኔ ሀብታዊ አቅማቸውን የሚያጎለብቱ፣ የእምነታቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነትም የሚያግዙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት የሚመራው አካል ደግሞ ሌላውን አናሳ ቡድን የመርገጥ፣  የራሱን እምነትና አስተሳሰብም በሌላው ላይ የመጫን ዕድሉ የሰፋ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡
4) ቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ቦታዎችን መያዝ
በኢትዮጵያ የነበረው ነገሥታትና ንግሥና ታሪክ አክራሪ ሙስሊሞችን እጅግ ያበሳጫቸዋል፤ ሲያሻቸው ተገቢውን የመንግሥት ሥልጣን አላገኘንም ብለው በይፋ አምነው ሲናገሩና ሲጽፉ ሌላ ጊዜ ደግሞ ‹‹አልነጃሺ የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሥ ነበር›› በሚል የፈጠራ ታሪክ የናፈቁትን የሥልጣን ተጋሪነት መቋደስ ይሻሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ባለፉት መሰል ትርክቶች መነታረኩ ብቻ እንደማይጠቅማቸው ተረድተው የዛሬው እውነታ ላይ ለማተኮር እየተገደዱ ነው፡፡
የትኛውም ሥርዓት ቢመጣ ቁልፍ፣ ቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ቦታዎችን መቆናጠጥ አዲሱ የአክራሪ ሙስሊሞች ዋና ትኩረት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ከመቅጽበት ለመሾም በመሯሯጥ ሣይሆን አስቀድመው በሚያደርጓቸው የረጅም ጊዜ ዝግጅቶቻቸው ይታወቃሉ፤ በዚህ ሊደነቁም ይገባል፡፡ በሁሉም የትምህርት መስክና የኃላፊነት ደረጃ ሊሠሩ የሚችሉ ምሁራንን በልዩ ሁኔታ ማብቃት፣ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ መርዳት (sponsor ማድረግ)፣ ተገቢውን ክብካቤና ማኅበራዊ ጥበቃ በማድረግም ለሚያስቡት ቁምነገር ማብቃት የተካኑበት አሠራራቸው ነው፡፡ ‹‹ከከፍተኛ የምኒስትርነትና የመንግሥት ዙፋን ማዕረግ እስከ ታችኛው ድረስ ሥልጣንን መቆጣጠር›› የሚል ግልጽ ስትራቴጂም አስቀምጠዋል፡፡
አሁን ባለው የሀገራችን የአስተዳደር ሥርዓት እንኳን ከቀበሌ አመራር ጀምሮ እስከ ትልቁ የአከባቢው ሥልጣን እርከን ድረስ በአብዛኛው በሙስሊኖች የተያዙባቸው ወረዳዎችና ዞኖች አሉ፡፡ በሐምሌ 2010 ዓ.ም መጨረሻ ላይ በኢትየ-ሱማሌ ክልል ክርስትናና ክርስቲያኖች ላይ የተሰነዘረው አሰቃቂና መጠነ ሰፊ ጥቃትም በክልሉ ‹‹ምክር ቤት ደረጃ›› የታወጀ እንደነበር ማስታወስ ላነሳነው ነጥብ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ለዚያም ነው አብያተ ክርስቲናት ሲቃጠሉ፣ ካህናት ሲሰደዱ፣ ምዕመናን ሲገደሉ፣ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቲያኖች ንብረቶች ሲዘረፉ ለሚመለከታቸው የመንግሥት መዋቅሮች አቤት ብሎ ፍትሕ ርትዕ ያልተጓደለበትን መፍትሔ ማግኘት ያልተቻለው፤ ‹‹ልጁ ቀማኛ፣ አባቱ ዳኛ›› እንዲሉ፡፡
5) የሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪነት 
በሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሚዲያ አውታሮች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ለመታየት መታተር ሌላኛው የአክራሪ ሙስሊሞች ስልት ነው፡፡ ይህ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካታ ተከታዮች ካሏቸው ግለሰቦችና ጦማሮች ጀምሮ መጽሐፍ ጽፈው የሚያሳትሙ፣ በጥናትና ምርምር ስም የተዛቡ ትርክቶችን እየጻፉ በዓለም አቀፋዊ ጆርናሎች ላይ ጭምር የሚያሳትሙ፣ በብሮድካስት ሚዲያ አማካይነት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የሚደክሙ፣ ወዘተ. ሁሉ ያካትታል፡፡
የአክራሪ እስልምናን አስተሳሰብና እንቅስቃሴ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማራመድ ከሚታወቁት መካከል አቶ ጃዋር መሐመድና አህመዲን ጀበል ይጠቀሳሉ፤ ሌሎች በርካቶችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የእንዳንዳቸውን ማንነትና ዓላማ በትክክል ማስረዳት የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ባለመሆኑ፣ አንባቢያንም በግልጽ የሚያውቋቸው ስለሆነ ዝርዝር ጉዳዮን ከመጻፍ ተቆጥበናል፡፡ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ግን በተለያዩ አካሄዶች የተመራ፣ ነገር ግን ተመሳሳይ መዳረሻ ያለው ዓላማቸው ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜያት የሀገሪቱን የፕሬስ ነጻነት መሻሻል እንደ ምቹ ቀዳዳ ተጠቅመው እንደ አሸን እየፈሉ የመጡ ጋዜጦቻቸው፣ እንደ ‹‹ቀሠም›› ያሉ ተንኳሽ መጽሔቶቻቸው፣ ቱባ ሀሰቶች በመጻሕፍት መልክ እየተዘጋጁ የሚታተሙባቸው ኩነቶች፣ በአረብ ሀገራት ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ተቋቁመው መርዛማ የአክራሪ እስልምናን መልእክቶች የሚረጩ የብሮድካስት ጣቢያዎች (ራዲዮና ተለቪዥኖች) ተበራክተዋል፡፡ ወቅቱ የሚዲያ ነው በሚል በእነዚህ ሁሉ አማራጮች ዘመናዊ ጦርነት ከፍተው የውጊያውን ሜዳ ጥብብ፣ ጭንቅ አድርገውታል፡፡  በስትራቴጂ ሰነዳቸውም ላይ፡- ‹‹የህትመት ሥራዎችንና ትርጉሞችን በእጥፍ በማዘጋጀት ለሙስሊሞች መማርያ ማመቻቸት›› ማለታቸው ለዘርፉ ትኩረት መስጠታቸውን የሚጠቁም ነው፡፡ የእነዚህን ሚዲያዎች ተናጠላዊ ዳሰሳ እንደ አስፈላጊነቱ ወደፊት የምንመለስበት ይሆናል፡፡
6) ነባር ማኅበራዊ ትስስሮችን ማፈራረስ፤ የራሳቸውን አክራሪ ሰንሰለት መፍጠር
ነባር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር የነበራቸው ታሪካዊ ማኅበራዊ መስተጋብር ከልብ የመነጨና በተግባርም የተመሰከረለት እንደነበር ይታወቃል፤ ዛሬም ድረስ ቋሚ ምስክሮች አሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ያለ ሙስሊሙ አስተዋጽዖ፣ መስጊዶቹም ያለ ክርስቲያኑ ርብርብ አልተሠሩም፡፡ በደስታውም ይሁን በሐዘኑ ያለ አንዳች ልዩነት አብረው ይካፈላሉ፤ ቤት ያፈራውንም እንደየእምነታቸው አድርገው ይቋደሳሉ፡፡ በዓመት በዓላት እንኳን ‹‹ተረኛ ደጋሽ›› ከመሆን ያለፈ አንዱ እየበላ፣ ሌላው የሚራብበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ሌላውን ትተን በበዓለ ጥምቀት ዛሬም ድረስ የምናስተውላቸውን ጥቂት ቀሪ ትውፊቶቻችንን ስናጤናቸው በየመንገዱ ላይ ቆመው ለክርስቲያኖቹ ውኃና ዳቦ የሚያቀብሉ፣ የታቦት መተላለፊያ መንገዶችን በአክብሮት መንፈስ የሚያጸዱ (ለፖለቲካ ፍጆታ በሚዲያ ፊት የሚቀረጹትን ሳይሆን ከልባቸው የሚደርጉ)፣ ታቦታቱ ወደ መንበረ ክብራቸው ሲመለሱም ‹‹አሃምድሊላህ ታቦታችን በሰላም ገባ!›› በማለት ደስታቸውን በእልልታ እስከመግለጽ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬም ድረስ አሉን፡፡
ይህን የመሰለ ነባር ትውፊታዊ መስተጋብርና በፍቅር ኃይል የተገመደ ማኅበራዊ ትስስራችን ግን አሁን አሁን አደጋ እየተጋረጠበት የመጣ ይመስላል፡፡ ሁለቱ በጋራ ሆነው የሰሯቸውን አብያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥሉ፣ በእንግድነት ተቀብለው ሀገር ያላመዷቸውን ነገሥታት የሚነቅፉ፣ ነባር ማኅበራዊ እሴቶችንም የሚንዱ የአክራሪ እስልምና አቀንቃኞች የበረከቱበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡
ጥሩ ማኅበራዊ ግንኙነት ለመመስረት ሙከራ ያደረጉትን እንኳን ስንመለከት አንዳንዶቹ እውነተኛውን አብሮነት ፈልገው ሣይሆን መልካም መስለው በመታየት እስልምና ጥሩ እምነት እንደሆነ ለማሳየት መሞከራቸው ነው፡፡ ለዚህ ተግባር የተዘጋጁትን ስትራቴጂ ሰነዳቸው ‹‹የበጎ ፈቃደኛ ዳዕዋ አባላት›› (Islamic Mission Coordinators) መሠማራታቸውን ይገልጻል፡፡ የግለሰቦቹ መልካም ማኅበራዊ ግንኙነትና ሰበካ እንዲሁም የበጎ ፈቃደኝነት እርዳታ ግን እስልምና ‹‹ሰላማዊ ሃይማኖት›› ለመሆኑ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም፡፡
በቅርቡ ደግሞ በልማት ስም የሚመሰርቷቸው ማኅበራዊ ተቋማት ጭምር ከዒላማቸው ባፈነገጠ መልኩ የእነዚህ ጽንፈኛ አመለካከቶችና አካሄዶች ማራመጃ መሆን ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ትውልድ የሚታነጽባቸውን ትምህርት ቤቶች ለዚህ የጥፋት ዒላማ ለመጠቀም የመሞከር አዝማሚያዎች አሉ፡፡ አወሊያ የሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች [“Aweliya Islamic Mission Schools”] የዚህ እንቅስቃሴ አካል እንደሆኑ ይታማሉ፡፡
መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ስም እየተቋቋሙና በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ፣ በተጨባጭ ግን የአክራሪ እስልምና አካሄዶች ሰለባ የመሆን ሰፊ አድማስ ውስጥ ያሉም አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- Islamic Relief Worldwide/ International Islamic Relief Organization; Ethiopian Muslims’ Relief and Development Association ከልማት ትኩረታቸውም ባሻገር ሃይማኖታዊ ተልእኮ ጭምር እንዳላቸው ስያሜዎቻቸውም ምስክር ናቸው፡፡
7) ተፈጥሯዊ (ራስን በራስ) የማዳከም ስልቶች (Biological Strategy)
ይህ ስልት ደግሞ አንድ እንዲጠቃ የተፈለገው ተቋም ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ መርዳት (helping the institution to self-suicide) የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የመባሉም ምሥጢር ችግሩን በሚመስል መፍትሔ የመከላከል ስልትን ስለሚከተል ነው፡፡ ለምሳሌ፡-  በሥነ-ሕይወታዊ የጥናት ዘርፍ ትላትሎችን ከግብርና ሰብል ጥቃት ለመከላከል ሲፈለግ ለሰብሉ ጎጂ ያልሆኑ፣ ነገር ግን ትላትሎቹን የሚበሉ ሌሎች እንስሳት የማርባት ዘዴ ማለት ነው፤ በዚህ የተፈጥሮ ሚዛን ይጠበቃል፡፡ ከሌሎች ስልቶች የበለጠም ውጤታማ ነው፡- ኬሚካልን የመሰሉ መፍትሔዎች ለጎጂ ተባዮች ተረጭተው ጠቃሚዎቹንና ሰብሎችን ጭምር የሚያደርቁ ‹‹ጅምላ ጨራሽ›› ናቸውና አይመከሩም፡፡ ተባዮቹን የሚመስሉ ሌሎች ተጻራሪ ተባዮች ሲሆኑ ግን ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ስላላቸው በቀጥታ ከመገናኘታቸውም በላይ ጎጂዎቹ ተባዮችን አዘናግተው (ዘመድ መስለው) እንዲያጠቁአቸው ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
ይህንኑ ሁኔታ ወደ ተቋም ስናመጣው አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጥታና በይፋ የሚሰነዝረውን ጥቃት ቸል ብሎ ብዙም በማይታወቅበት (ለትችት በማያጋልጠው)፣ ነገር ግን የተሻለ ውጤታማ በሚያደርገው መልኩ እንዲያዳክማት የሚያስችለው ነው፡፡ የራሷ አባላትና መዋቅራት ሳይታወቃቸው መልሰው እርሷኑ እንዲያጠቁ ማድረግ የዚህ ስልት አካል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የቅርቡን ‹‹የኦሮምያ ቤተ ክህነት›› እንቅስቃሴን ስንመለከት ሙስሊሞቹ ከምን አንጻር (ምን ስለሚጠቅማቸው) ነው የሚደግፉት? ተብሎ ቢጠየቅ ወደ እውነት የሚቃረበው ምላሽ ይኸኛው ስልት ነው፤ ለእርሷ የተቆረቆሩ በማስመሰል፣ መዋቅርን በመዋቅር የማዳከም ስትራቴጂ፡፡ መሰል ክልላዊ መዋቅሮችን በመደገፍ ዋናውን (ማእከላዊውን) መዋቅር ማዳከም ከተቻለ ከዚያ በኋላ አንድነት ያጣችውንና በተለያዩ አቅጣጫዎች የምትገፋዋን ተቋም በቀላሉ ገፍቶ ለመጣል ይቻላል የሚል ትንታኔ አላቸው ማለት ነው፡፡
ይህ ተፈጥሯዊ ስትራቴጂ ‹‹ራስን በራስ እንዲያጠፋ መርዳት›› መርሕን ስለሚከተል  ቤተ ክህነቱ እንደተጻራሪ ክንፍ በፈረጃቸው የእስልምናና ሌሎች የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች  ከመገዳደር ይልቅ በውስጡ ባሉት ሰዎቹ ተጠቅሞ፣ ስያሜውን በሚመስል ዘዴ፣ የራሱን ተልእኮ የሚያፋጥንለት የሚመስለውን አሠራር መዘርጋት ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ መዋቅርን በመዋቅር፣ ቤተ ክህነትን በቤተ ክህነት፣ ማኅበራትን በማኅበራት፣ አሠራርን በአሠራር ተክቶ ከመጀመርያው አቅጣጫዋ ወደሚፈለገው መሥመር ማስቀየስ፤ በሂደትም ግብዓተ መሬቷን ለመፈጸም እንደማለም ያለ ስልት ነው፡፡
8) ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት
አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ መሠረት ይዞ ለሺዎች ዘመናት የኖረውን የክርስትና ታሪክ ለመናድ በተናጠል፣ በሀገር ውስጥ ባለው አቅምና በውስን አካሄዶች ብቻ እንደማይከናወንለት በውል የተገነዘበ ይመስላል፡፡ የራሱን ስኬቶችና ድሎችም ለሌሎች በተሞክሮ መልክ በማካፈል የጋራ ደስታ መፍጠር ቋምጧል፡፡ እናም ከፍተኛ የፖለቲካ ድጋፍ ማግኘትና ከዓለም አቀፍ መሰሎቹ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ትስስር መፍጠርን የትኩረት አቅጣጫው ማድረጉን ከሚከተሉት የስትራቴጂ ሰነዱ አገላለጾች እንረዳለን፡-
• በፍትህ ሚኒስቴር የተመዘገበ ልዩ የእስልምና ጉዳይ አስፈጻሚን በማስቀመጥ የዲፕሎማሲ ሥራ እንዲሰራ ማድረግ፤
• በመንግሥት ረገድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸውን ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ማቋቋም፤
• ለምሥራቅ አፍሪካ እስላማዊ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ ትብብር መሳካት መታገል፤
• ለመንግሥት ፖለቲካ አድልዎ በማድረግ የእስልምናን ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚቃወሙትን ለይቶ በማወቅ ለዲናቸው እንዲታገሉ ማስታጠቅና ማስጠንቀቅ፤
• የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶችን ከዓለም አቀፍ ወጣቶች የእስልምና ሊግ ጋር ማስተዋወቅና ማስተሳሰር፤
• ዓለም አቀፍ እስላሚክ መድረሳ (ዩኒቨርስቲ) በማቋቋም ከአራቱም አቅጣጫዎች ምሁራን ወደዚህች ሀገር መጥተው እንዲሰለጥኑ ማድረግ፤
• የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ለአፍሪካ እስላማዊ እንቅስቃሴ መሪነት ማዘጋጀት፤
• የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአረብ ሊግና ሌሎች ተቋማት አባል እንዲሆኑ ማድረግ፤
•  ታሪካዊ እስላማዊ ሥፍራዎችን (እንደ አልነጃሺ መስጊድና ድሬ ሼክ ሁሴን ያሉትን) ለዓለም በማስተዋወቅ በኢትዮጵያ የእስልምናን ጥንታዊነት ማሳወቅ፤
• በሸሪዓ ሕግ የሚተዳደሩ ሙስሊም ኡማዎችን [ተቋማትን] በመላው ሀገሪቱ ማየት፤
• ሀገሪቱ [ኢትዮጵያ] የእስልምና ደሴት ሆና ማየት፤
• አንድ የሆነ፣ ለዓለም አርዓያ የሆነ፣ ሌሎችንም ሊያስታርቅ የሚችል ሀበሻዊና አረባዊ እስልምናን ማቋቋም፤ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
9) የኃይል እርምጃዎችና ጭካኔአዊ ጥቃቶች (Coercive Extinction Strategy)
ይህኛው ደግሞ አስቀድመው የተዘረዘሩት ስትራቴጂዎች ሁሉ በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ አልያም የኃይል የበላይነት እንዳላቸው ሲያስቡ የሚወስዱት የመጨረሻው እርምጃቸው ነው፡፡ ውስጥ ለውስጥ ከሚደረጉት ስልቶች ወደ ግልጽ ጥቃትና ይፋዊ ጦርነት መግባት ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ የኃይል እርምጃ መውሰድ ሃይማኖታዊ አካሄድ አለመሆኑን እያስታወሱ ሊሞግቷቸው የሚሞክሩትን አፍ ለማስዘጋት ደግሞ እርምጃውን ‹‹ቁርዓናዊ›› አድርገው ጂሃድ ይሉታል (ስለ እምነት ሲባል የሚደረግ ቅዱስ ጦርነት ያደርጉታል)፡፡ በዚህ መልኩ በአክራሪዎቹ አእምሮው የታጠበ እስላማዊ ትውልድ ደግሞ በተነገረው መሠረት ስለ እምነቱ ዋጋ ቢከፍል ጀነት ሰተት ብሎ የገባ ስለሚመስለው ‹‹ሁሉም ለአላህ እስኪገዛ ድረስ›› በገጀራ ደም ከማፍሰስ፣ በርካቶችን አጥፍቶ ራሱንም ከማጥፋት ወደኋላ አይልም፡፡  ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዓለም አቀፍም፣ በአህጉርም ሆነ በሀገራችን ደረጃ እየተከሰቱ ያሉት አካሄዶች በአብዛኛው ይህንኑ ስልት የተከተሉ ናቸው፡፡ በዚህ ስልት መሠረት አክራሪ እስልምና በተለይ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸማቸውና እየፈጸማቸው ያሉትን ጥቃቶች በቀጣይነት ዝርዝር መረጃዎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
ያም ሆነ ይህ የአክራሪዎቹ የስትራቴጂ መሪ ቃልና የትግላቸው መፈክር፡- ‹‹እኛ እንታገላለን፤ ልጆቻችን ያሸንፋሉ፤ የልጅ ልጆቻችን ዓለምን በእስልምና ይወርሳሉ!›› አላሁ አክበር!!! የሚል ነው፡፡ ይሳካላቸው ይሆን? ውጤቱን በጊዜ ሂደት የምናየው ይሆናል፤ ይቆየን!
እውነትን_በመግለጥና_ሀሰትን_በማጋለጥ_የሀገርን_ሰላምና_የሕዝብን_አንድነት_ለመጠበቅ¬_እንትጋ!
Filed in: Amharic