>

ከሰሞኑ በሚለቀቁ ቪዲዮዎች የምንሰማው ሰቅጣጭ የፍጅት ዜናዎች...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ከሰሞኑ በሚለቀቁ ቪዲዮዎች የምንሰማው ሰቅጣጭ የፍጅት ዜናዎች…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የገዳ ድርጅት ሥርዓታዊ ያደረገው የጭካኔ ሕግ ውሉዱ እንጂ የሓጫሉን ግድያ ተከትሎ አጋጣሚ ያገነፈለው  ወቅታዊ ክስተት አይደለም! 
እየወጡ ያሉ ለኅሊና የሚሰቀጥጡ፤ ሰው መሆንን የሚያስጠሉ፤ በኢትዮጵያ ምድር ተበርግዶ የተከፈተውን የሲኦል በር በገሀዳዊ ዐይን የሚያሳዩ የፍጅትና የጭካኔ  ቪዲዮዎች  ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት በተደረጉ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳዎች ብቻ የተፈጠሩ አድርጎ ማቅረቡ የተጋረጠውን ችግር ማቃለል ነው። የሰማኒያ ዓመት አዛውንት ከቤታቸው ጎትተው በማስወጣት በዱልዱም ካረዱና አስከሬናቸውን አስር ቦታ በሜንጫ ከቆራረጡ በኋላ የአዛዉንቱን የእጅ  ቁራጮች እንደ አጣና ወደላይ በመስበቅ <<ነፍጠኛ ይውጣ>> እያሉ የሚጨፍሩ፤ አማራ አያሳየን ብለው “አማራ ኦሮሞ መሬት ላይ አይወለድም” በማለት የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር በልጆቿና በባለቤቷ ፊት አንጋለው የሚያርዱ፤ በግፍ ያረዷቸው ንጹሐን  አፈር እንዳይለብሱ <<ኦሮሞ መሬት ላይ አማራ አይቀበርም>> በማለት አስከሬናቸውን አሞራና ጅብ እንዲበላው ያደረጉ  ሀያ ዓመት ያልሞላቸው ቄሮዎች በፕሮፓጋንዳ ብቻ አረመኔ የተደረጉ አይደሉም።
በቪዲዮ ያየናቸውንና ከግፉዓኖች የሰማናቸውን የፍጅትና ጭካኔ አይነቶች  ሁሉ የፈጸሙት ቄሮዎች የገዳ ሥርዓት ሕጋዊ ባደረገው culture of violence እየተኮተኮቱ ያደጉ ናቸው። ቄሮዎቹ የፈጸሙት ፍጅትና ጭካኔ ሁሉ  አደግንበት  የሚሉት የገዳ  ሥርዓት ኦሮሞ ባልሆነውና ኦሮሞ በማይመስለው ላይ እንዲፈጸም  የሚፈቀደውን ሕጋዊና ሥርዓታዊ ጭካኔ  ነው።  ለዚህም ነበር ኦሮሞ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከተፈጸመው ጭካኔ  የዐይን ምስክር የሆኑት አባ ባሕርይ በ<<ዜናሁ ለጋላ>> ምዕራፍ ስምንት ያ ሁሉ ጭካኔ የተፈጸመበትን  ምክንያት ሲያስረዱ  <<እስመ ከመዝ ሕጎሙ>> ወይም <<ሕጋቸው እንዲህ ነበርና>> ያሉት።
ለማታውቋቸው በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኖሩት የጋሞው መነኩሴ አባ ባሕርይ <<ዜናሁ ለጋላ>> በሚል ርዕስ መተኪያ የሌለው የታሪክ  መጽሐፍ የጻፉና  በገዳ ሥርዓት የተመራው የኦሮሞ ገዢ መደብ [ሉባ] ወታደሮች ኦሮሞ ባልሆነውና በወረሩት ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ምድራዊ ጭካኔ በዐይናቸው ያዩ የታሪክ ምስክር ናቸው።  አባ ባሕርይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመዘገቡት የአምስቱ የገዳ ሉባዎች የጭካኔና የአረመኒያዊነት ታሪክ ቄሮ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን  ከፈጸማቸውና  ከሰሞኑ  በቪዲዮ እየወጡ ካሉ በዚህ ዘመን ሊደረጉ ቀርቶ ሊታሰቡ ከማይችሉ  የፍጅት፣ የጭካኔና የዘር ማጥፋት ደርጊቶች ጋር አንደ አይነት ነው።
በፋሽስት ጥሊያን ወረራ ወቅት ጅማ ውስጥ  አባ ጆቢር <<የአማራ አንገት ቆርጦ  ላመጣ 30 ብር እሰጣለሁ>> በማለት ባስነገረው አዋጅ  አማካኝነት የተካሄደው አረመኔያዊ ፍጅትም ተመሳሳይና አባ ባሕርይ የጻፉት የፍጅት ታሪክ  ቅጂ ነበር።  የዚህን ዘመን ፍጅት ታላቁ አርበኛ፣ ሚኒስትርና ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ <<ትዝታ>> በሚል በጻፉት ትውስታቸው ገጽ 166 ላይ አቅርበውታል። ሐዲስ አለማየሁ <<ትዝታ>> የሚለውን መጽሐፋቸውን የጻፉት አባ ጆቢር በአዋጅ ያስፈጸሙት እልቂት ከተካሄደ ከ56 ዓመታት በኋላ ቢሆንም ባይናቸው ያዩትን ያ ትራጄዲ ግን <<ካለፈውም በኋላ ትዝታው የሚያሳዝን፣ የሚዘገንን ነው>> ሲሉ  ነበር ትውስታው ከኅሊናቸው እንዳልወጣ የገለጹት። ልብ በሉ! አርበኛው ሐዲስ ወደ  ሰሜን በዘመቱበት ወቅት የፋሽስትን ጭካኔ ባይናቸው ያዩና የተጋፈጡ ናቸው። ከኅሊናቸው እንደማይጠፋ የነገሩን ግን የአባ ጅፋር ልጅ አባ ጆቢር በሴቶች፣ ባሕጻናትና በአዛውንቶች ላይ በአዋጅ ያስፈጸመው ጭካኔ ነው።
በደርግና በወያኔ ዘመን  በአማራ ላይ የተካሄደውን  ፍጅትና የዘር ማጥፋት  አድራጊዎቹ ኦነጋውያን ራሳቸው  ያረጋገጡትና የተናጋሩት ስለሆነ ሌላ ምስክር አያሻውም። ቀደም ባለው ዘመን  በደቡብ ኢትዮጵያ  የግለሰብ ጭሰኛ የነበሩ የባሌ፣ የሐረርጌና የአርሲ የአማራ ገበሬዎች በደርግ ዘመን <<የመሬት ላራሹ>> ሲታወጅ  በግለሰብ ጭሰኛነት የሚያርሱትና የራሳቸውም መሬት ጭምር በአግዛዙ ተወርሶ የአገዛዙ ጭሰኛ  እንዲሆኑ ተደርገው ያርሱት ከነበረው መሬት አማራ በመሆናቸው ብቻ  “settlers” ወይም ሰፋሪዎች እየተባሉ በኦነግ እንምን አይነት ግፍ ተፈጽሞባቸው እንደተፈጁ ኦነግ  ራሱ የኩባ ወታደሮችን የሶማሌን ወራሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ወገን ሆነው  እንዳይወጉ በ1970 ዓ.ም. ” A letter to the Cubans in Harar” በሚል በጻፈው ግልጽ ደብዳቤ ገጽ 2 ላይ ነግሮናል። ይህንን የኦነግ ደብዳቤ ወደፊት አወጣዋለሁ።
በወያኔ ዘመን የተካሄደውን የአርባጉጉና የበደኖ ፍጅት በኦነግ እንደተካሄደ ኦነግ ራሱ የሽግግር ምክር ቤት ተብዮው ፊት ቀርቦ ያመነውና  የኦነግ አመራር የነበሩት እነ አባ ቢያና  ነዲ ገመዳ ያረጋገጡት ታሪክ ነው።  ኦነግ በበደኖ የአማራ ተወላጆችን፤ በተለይም ሴቶችን፣ ሕጻናንት፣ አዛውንቶችንና አቅመ ደካሞችን በጭካኔ አርዶና በግፍ ፈጅቶ   በማይሞላ ገደል ውጭ እንደጨመራቸው ሽግግር ምክር ቤት ተብዮው  ፊት ቀርቦ ያመነበትን ቪዲዮ ከታች አቅርቤዋለሁ።
እንግዲህ! ከፍ ብዬ ለአብነት በጠቀስኳቸው ዘመናት ሁሉ የተፈጸመው አረመኒያዊ ጭፍጨና አሁን ቄሮ እያካሄደው ያለው ፍጅትና የዘር ማጥፋት  ሁሉ አባ ባሕርይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዐይን ምስክርነት የሰጡበት የገዳ ሥርዓት ሕጋዊ ያደረገው culture of violence ቅጂ ነው። ስለዚህ ከሰሞኑ በአርሲ፣ በባሌና በዝዋይ ቄሮ ያካሄደውን ፍጅት፣ የጭካኔ ጥግና የዘር ማጥፋት  isolated incident የሆነ የተለመደ የአፍሪካ ethnic explosion  ወይም ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት በተደረጉ የኦሮሞ ብሔርተኞች የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳዎች የተፈጠሩ ብቻ አድርጎ ማቅረብ ፈጸሞ ስህተት ነው።  ኦሮሞ አይደለም፤ ኦሮሞ አይመስልም፤ ወዘተ በተባለው የኅብረተሰብ ክፍል ላይ በቄሮ አድራጊነት፣  ኦሮምያ ክልል በሚባለው አገዛዝ ሙሉ ድጋፍ እየተካሄደ ያለው ፍጅት፣  ጭካኔና የዘር ማጥፋት አቃፊና ዲሞክራሲያዊ እየተባለ የሚንቆለጻጸሰው የገዳ ሥርዓት ተቋማዊና ሕጋዊ  ያደረገው culture of violence  ውጤት ነው። እውነታው ይኼ ነው።  አገር ያለውና ይህ እውነት በመነገሩ አገር የሚፈርስ የሚመስለው ሰነፍ  ቢኖር እድሜ ይስጠው እንጂ  የግፉአን እጣ ፈንታ በቅርቡ ቤቱን ስለሚያንኳኳ  አገርና መንግሥት እንዳለው ያኔ ሲደርስበት ያየዋል።
ከታች የታተመው ማስረጃ በበደኖ በንጹሐን የአማራ ተወላጆች ላይ የተካሄደውን ፍጅትና ጭፍጨፋ ኦነግ ራሱ እንደፈጸመው  የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት  ተብዮው ፊት ቀርቦ ያረጋገጠበት ታሪካዊ ቪዲዮ ነው።  በድምጽና ምስል ላይበራሪዬ እንዲኖረኝ የምሻውን ይህን ታሪካዊ ቪዲዮ በጠየቅሁት ጊዜ ከግል ማህደሩ ፍልጎ ለላከልኝ ለወንድሜ ለታማኝ በየነ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
Filed in: Amharic