>

በሰልፍ ላይ ብቻዬን ብሆን እንኳን የማሰማው ግልፅ መፈክር!!! (ሰይፍአርድ አምደጽዮን)

በሰልፍ ላይ ብቻዬን ብሆን እንኳን የማሰማው ግልፅ መፈክር!!!

ሰይፍአርድ አምደጽዮን

1. * እርቅ የሚያስፈልገው ለአራጅና ለገዳይ ሳይሆን ለባልና ሚስት አለመግባባት ጉዳይ ነው!!
2. * በሜንጫ እና በገጀራ ንፁሃንን በዘር በኃይማኖት እየለየ ለሚጨፈጭፍ አረመኔ ሀይል ህጋዊ እርምጃና ፍርድ እንጂ እርቅና ሽምግልና አይደለም!!
3. * የአማራውን: የጉራጌውን እና የክርስቲያኑን ጭፍጨፋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት ማስቆም ይጠበቅበታል!!
4. * የሩዋንዳው ሁቱ በቱትሲ ማህበረሰብ ላይ የፈፀመው አጠቃላይ አይነት የዘር ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ውስጥ ከመፈፀሙ በፊት ዓለም በግልፅ ሊያወግዘውና ሊመክተው ይገባል!!
5. * ታላቁ እስክንድር ነጋ: ስንታየሁ ቸኮል: አስቴር ስዩም: ይልቃል ጌትነት: ልደቱ አያሌው: ሂሩት ከተፈፀመው እልቂትና አረመኒያዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር ምንም ግንኙነት ስለሌላቸው: በአስቸኳይ ይፈቱ!!
6. * የአብይ መንግስት የሞራል ልዕልና እና ህግን የማስከበር ብቃት ካለው: በኢትዮጵያ ውስጥ የጭካኔ ተግባር ጥምር ግብረሀይል የመሰረቱትን ሊቀሰይጣን ወያኔን እና ሊቀጂኒው ኦነግን ለፍርድ ያቅርብ!!
7. * መንግስት ህግን በማስከበር ሽፋን ህግን መጣስ: ቅልቅልና የግብርይውጣ ተግባሩን በአስቸኳይ ያቁም!!
8. * ቅልቅል ከሰርግ በሗላ የተጋቢ ቤተሰቦችን ለማስተዋወቅ የሚፈፀም ስርዓት እንጂ አረመኔው ሲያዝ ንፁህ ሰው ለመናጆ ሲባል እስርቤት የሚወረወርበት ስልት አይደለም!!
9. * በመንግስት የአስተዳደርና የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ሆነው የዘር ጭፈጨፋ ሲፈፀም በቸልተኝነት: በግዴለሽነት: ያለፉ: በአባሪነት: በስውር በአስተባባሪነት የተሳተፉ እና የሙያና የሀላፊነት ግዴታቸውን ባልተወጡ: እጃቸውን በንፁሃን ደም እና ህይወት ውስጥ የነከሩ ሀይሎችን መንግስት ያለምንም ማቅማማት በወረንጦ እየለቀመ በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ማቅረብ ይጠበቅበታል!!
10. * በማጭበርበር ለስላጥን እርካብ የሚያበቃው ፓርላሜንታዉ የመንግስት ስርዓት ወደ ፕሬዚደንታዊ የመንግስት ስርዓት ሊቀየር ይገባል!!
11. * ዘረኛው ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀር ወደ መልካምድራዊ ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀር ሊቀየር ይገባል!!
12. * መንግስት የወያኔን የእልቂት ሰነድ በአስቸኳይ አስወግዶ: በፍጥነት ብሔራዊ የህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን ያቋቁም!!
13. * መንግስት ለአድርባይና አጨብጫቢ ሳይሆን ለሀቀኞች ክብርና ቦታ ይስጥ!!
14. * ዶ/ር አብይ መናገርና መሆን እንደሚለያይ: ማስመሰልና መተግበር ለየቅል መሆኑ ሊገባህ ይገባል!!
15. * አሸባሪዎች በውሸት ትርክት የሚነግሩንን በወገኖቻችን ላይ በ21ኛው ክፍለዘመን በከፍተኛ ጭካኔ በተግባር ፈፅመው በገሃድ አሳይተውናል!!
16. * ቦኩ ሀራም በናይጄሪያ: ሙርሌ በደቡብ ሱዳን ፅንፈኛው ቄሮ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የሽብር ተግባር የሚፈፅም አሸባሪ ድርጅት ነው!!
Filed in: Amharic