>

ዘር ማጥፋትን መካድ ከዘር ማጥፋት እኩል ወንጀል ነው! (በመስከረም አበራ)

ዘር ማጥፋትን መካድ ከዘር ማጥፋት እኩል ወንጀል ነው!

 በመስከረም አበራ

ኢትዮጵያ  ውስጥ ብዙሃን ዘውግ ነኝ ለማለት የመቶ ሚሊዮኑን ህዝብ ከግማሽ መዝለቅ ያስፈልጋል፤ከሃምሳ ሚሊዮን የሚበልጥ ቁጥር ያለው  ዘውግ ደግሞ የለም፡፡ስለዚህ በሀገር ደረጃ ሲታሰብ ብዙሃን ዘውግ የለም፡፡ብዙሃን ነኝ ባይ ዘውግ ያለው በየክልሉ ነው፡፡ ቁምነገሩ ግን በክልል ቀርቶ በሃገር፣በሃገር ይቅርና በዓለም ብዙሃን መሆን ሰው የመግደል ስልጣን የማይሰጥ መሆኑ ነው፡፡
ሁለተኛ ቁምነገር ዘር ማጥፋትን መካድ ከዘር ማጥፋት እኩል ወንጀል ነው! ዘር ማጥፋትን የሚክድ የዕድል ነገር አልገጥም ብሎት በቦታው አልተገኘም እንጅ ሰው እንደ ከብት በታረደበት ቦታቢገኝ ኖሮ ከማረድ ወደኋላ አይልም፡፡
ሶስተኛ ቁምነገር ዘር ማጥፋት የሚባለው የአንድ ዘውግ መሞት ብቻ አይደለም፡፡ የዘር ማጥፋት አጭር ትጓሜ ይህ ነው “Genocide is defined as the deliberate and systematic destruction of a racial, religious, political, or ethnic group”   በዓለም የውርደት ታሪክ የሆነው የሩዋንዳ ዘር ማጥፋት በቢለዋ የከተፉት ቱትሲዎች ብቻ አልነበሩም፤ሲዘገብም የሚዘገበው ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የታረዱበት ዘር ማጥፋት ተብሎ ነው፡፡
እኛ ሃገርም በዘውጋቸው፣ወይ በሃይማኖታቸው ወይ በሁለቱም ማንነታቸው ምክንያት ስም ዝርዝራቸው ተይዞ፣መታወቂያቸው እየታየ ሰዎች ታርደዋል፡፡እውነታው ይህ ነው! ይህን መመደበቅ፣ማድበስበስ ሰውበላነት ነው፤ከሁሉም በላይ ወንጀል ነው፡፡
በሃገሬ ስለታየው ውርደት ከዚህ በላይ ምንም ማለት አልችልም፤አዝኛለሁ፣የምሰማውን መቋቋም የማልችል ደካማ ሆኛለሁ፣መንፈሴ ሳስቷል…….
Filed in: Amharic