>

ኦነጋውያኑ  ትውልድን ለማሳሳት የካቡትን የውሸት ትርክት መናድ የሚቻለው በእውቀትና በመረጃ ነው!!! (ተድላ ገበየሁ)

ኦነጋውያኑ  ትውልድን ለማሳሳት የካቡትን የውሸት ትርክት መናድ የሚቻለው በእውቀትና በመረጃ ነው!!!

ተድላ ገበየሁ

ኢትዮዽያዊው ምሁር “አባ ጎርጎርዮስ” እንደ አውሮፖውያን ዘመን አቆጣጠር ወደ ጀርመን አገር ተጉዞ ከ1652 እስከ 1658 በመቆየት በዘመኑ ከታወቁት የጀርመን የቋንቋ ምሁራን ጋር በመሆን በግዕዝ ቋንቋ እንዲሁም በአማርኛ የተፃፉ የኢትዮዽያ ጥንታዊ መፃህፍትን ወደ ጀርመን ቋንቋ በመተርጎም ስራ ከፍተኛ ምሁራዊ አስተዋጾ አበርክቷል። በስተመጨረሻ ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮዽያ ለመመለስ ወስኖ በመርከብ ጉዞ ላይ እንዳለ Iskenderun በምትባል የቱርክ ከተማ አካባቢ ይጛዝባት የነበረችው መርከብ ባህር ውስጥ ሰጥማ ወደ አገሩ ሳይመለስ እንደወጣ የቀረ በዘመኑ ከፍተኛ ምሁራዊ ተግባርን ያከናወነ፣ አገሩን በታሪክ መዝገብ ላይ እንድሰፍር ያስደረገ ትልቅ ከሚባሉት የአገራችን የዘመኑ ምሁራን ተርታ ስሙ ህያው ሆኖ ሲዘከር ከሚኖሩት ኢትዮዽያውያን አንዱ ነው። በህይወት ዘመኑ እያለ አብረውት ይሰሩ የነበሩ የጀርመን እና የኤውሮፓ ምሁራን የነበረውን ችሎታና ምሁራዊ ብቃት መስክረውለት አልፈዋል። እኛም በዛሬው ዘመን የምንኖር ኢትዮዽያውያን አሻራውን ትቶልን ያለፈውን ታላቅ ኢትዮዽያዊ ወገናችንን ልንዘክረው እና ልናመሰግነው ይገባል። የምትመለከቱት ስዕላዊ መዘክር (ማስታወሻ) የተሳለው በ-Elias Christopher Heiss በ1681 እ.ኤ.አ ነበር። በሥዕሉ ላይም በላቲ እና በግዕዝ / አማርኛ ቋንቋዎች አባ ጎርጎሪዮስ “ኢትዮዽያዊ” የሚል ተፅፎበታል። በ1681 እ.ኤ.አ አባ ጎርጎሪዮስ “ኢትዮዽያዊ” ለምን ተባለ ብለን እራሳችንን ስንጠይቅ መልሱ አንድና አንድ ነው ። ኢትዮዽያ የምትባል አገር ስለነበረች ነው። በዛ ዘመን ኢትዮዽያ የምትባል አገር ባትኖር አባ ጎርጎርዮስ ኢትዮዽያዊ አይባሉም ነበር። አባ ጎርጎርዮስ “አብሲኒያዊም” አልተባሉም። ለምን ? አብሲኒያ የምትባል አገር በ1681 አልነበረችም። ወያናውያ፣ ኦነጋውያን ኢትዮዽያ የምትባለውን አገር የፈጠረው “ምኒልክ” ነው ይላሉ። ኢትዮዽያ የምትባል አገር በ1681 እ.ኤ.አ ካልነበረች ሸዋ ውስጥ ተወልደው ጀርመን አገር የሄዱት አባ ጎርጎርዮስ “ኢትዮዽያዊ” ናቸው ብሎ ጀርመናዊው ሰአሊ Elias Christopher Heiss ለማስታወሻቸው ባዘጋጀው ሥዕል ላይ እንዴት ለታሪክ ከተበው ? ኢትዮዽያ የምትባል አገር ከመቶ አመት በፊት የተፈጠረች ሳትሆን በጣም ጥንታዊ ሰፉ ግዛት የነበራት፡ ነገር ግን በታሪክዊ ሂደት አንዴ ስትሰፋ ቀጥሎም ስትጠብ፡ ዛሬ የምትገኝበት የግዛት ቅርፅ ላይ የደረሰች ጥንታዊ አገር ናት። ታሪካዊ የግዛቱን ለውጥ ለመመልከት በአፄ ሐይለስላሴ ዘመን የነበረውን የኢትዮዽያ ግዛት እና አሁን ያለውን የኢትዮዽያ ግዛት በማነፃፀር መመልከቱ የታሪካዊ ሂደቱን ለመመልከት ይረዳል ብዬ አምናለሁ።
“The Ethiopians were considered as occupying all the south coasts of both Asia and Africa.” and he adds that “this is an ancient opinion of the Greeks. ” ~ Ephorus
* Ethiopia was the first established country on earth, and the Ethiopians were the first who introduced the worship of Gods, and who established laws.” ~ Stephanus of Byzantium
Filed in: Amharic