>

የነገው ብሔራዊ ዕዳ....!!! (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

የነገው ብሔራዊ ዕዳ….!!!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
የወጣቱ ዘፋኝ ሞትና አገዳደል በጣም ያሳዝናል፤ ይበልጥ የሚያሳዝነው ግን ‹‹ፖሊቲካ›› የሚሉትን የገደለው ሽብርተኛነት መሆኑ ነው፤ ከሽብርተኛነት የምንሄደው ወዴት ይሆናል? በወጣቱ ግድያ መንስኤ በግፍ የተገደሉ፣ ንብረታቸው የወደመ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችንን ባሰብን ጊዜ ሀዘናችን   መሪር ይሆናል። ለሁላችንም የእግዚአብሔርን ምሕረት እለምናለሁ፤ ለጊዜው ብዙዎቻችን ተርፈናል፤ እኔም መስኮቴ ተለይቶ በድንጋይ በመሰበሩ ብቻ እግዚአብሔርን እያመሰገንሁ እጅግ በጣም ለተጎዳው ለሚከተለው ትውልድ አዝናለሁ።
የተገነባው መፍረሱ እያሳዘነን እንዴት እንደተገነባና በግንባታው ያዘኑና ያለቀሱ መኖራቸውን አንርሳ! እንዲያውም ለወደፊቱ ይኸው የደሀው ለቅሶ የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ አባዜ በያዛቸውና ሕግን መሣሪያቸው ባደረጉ ጉልበተኞች እየተካሄደ ነው፤ የደሀዎች እንባ መሬቱን አጨቅይቶ ጎርፉ ወደሰማይ እየነጠረ ነው፤ ለነገ የምናጠራቅመው ብሔራዊ ዕዳ ነው! ያሳዝናል! የዛሬው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ለነገው የሽብርተኛ ዘመቻ መነሻ ይሆናል፡፡
Filed in: Amharic