>

ከሀጫሉ ግድያ ጀርባ ያለውማን ነው (በኤልያስ ደግነት)

ከሀጫሉ ግድያ ጀርባ ያለውማን ነው?

 

በኤልያስ ደግነት /ኤልሻድ የሺ/

 


ሰላም በሀገር ውስጥም በውጭም የምተገኙ ኢትዮጵያዊያን እንዴት አላችሁ የሃጫሉን ሞት ተከትሎ ጭፍን ብሔርተኞ የመከኑ ትውልዶች ባደረሱት የነፍስ ማጥፋት እና የንብረት ውድመት ከልብ የተሰማኝን ሃዘን እና የልብ ስብራት ለመግፅ እወዳለሁ፡፡

 

ወዲህ ደግሞ የብሶት መወጫ የናፍቆ ማስረሻ የሆነው …ተጓዡ ዓባይ ውሎ አዳሩን ከቤት አድረጎ …እራትም መብራትም ሊሆን በመቃረቡ …እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን፡፡

ኢትዮጵያ ከሚነገሩላት ብዙ ሺ ገድላት እና አስገራሚ የስልጣኔ ታሪኮች ጎን ለጎን በየ ዘመኗ  ለወንበር ሲባል ያልተነገሩ ምናልባትም ሆን ተብሎ የተደበቁ የመገዳደል፣የመጠፋፋ ታሪኮች አሏት፡፡ ይህ የመጠፋፋት እና የመበላላት ሴራ ዓይን አፍጦ፣ጥርስ አግጦ እጅጉን ጎልቶ መታየት የጀመረው ግን ንጉሳዊውን ስርዓት ገርስሶ መንበረ ሰልጣኑን በተቆጣጠረው የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር  ወይም በደርግ ዘመነ መንግስተ ነው፡፡

ህዳር 14 ቀን 1967 ደርግ /ቤት

የደረግ መንግስት በጠቅላላ ጉባኤ እና በቋሚ ኮሚቴነት ንዑሳን ኮሚቴነት የተዋቀሩትና ሥልጣን በብቸኝነት ይዘዋል ያሉት ቡድኖች  “ለፖለቲካ እስረኞች የፖለቲካ ውሣኔ ለመስጠትበዚህቀን በደርግ /ቤት ጠቅላላ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ሰው መግደልን አጀንዳ አድርገው  ተወያይተው ለመግደልም ተስማምተው በእነርሱ ቁጥጥር ስር የነበሩ ሰዎችን ፊውዳል ፣ መኳንንትና መሣፍንት ስለሆኑ ደማቸውን የንፁህ ሰው ደም እንደፈሰሰ አንቆጥረውም ጨቋኞች ናቸው በማለት እንዲገደሉ በአንድነት ወስነውና ውሣኔውን እንዲያስፈፅሙ ለእስረኛ ኮሜቴና ለደርግ አባላት ትዕዛዝ ሰጥተው ከሕግ ውጭ በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ውስጥ ቢለሙም ቢከፉም ዕድሜያቸውን ሙሉ ሀገር ለማቅናት ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ 59 ሰዎችን  በጥይት ተደብድበው አንዲገደሉ ተደረገ…በዚህም ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ብሎ የጀመረው ደርጉ እጁንም ሀገሩንም በደም ጎርፍ ነክሮ መንገዱን ጀመረ፡፡

በለስ የቀናው ቀጣዩ የህውሓት መንግስት ደግሞ መቀመጫውን ካደላደለ በኃላ እንዳይነቀል ሁኖ በመላው ሀገሪቱ ስሩን በመስደድ ሕዋሶቹን አደራጅቶ ካበቃ በኃላ በመንበረ ስልጣኔ መጡ ያላቸውን ወይም ተንኮል አስበውብኛል ብሎ የጠረጠራቸውን ሰዎች ሁሉ እንዳይሆኑ ሆነው እንዲጠፉ ሲያደርግ …ገሚሶቹንም ፈፁም ከሰብዓዊ ሕሳቤ ውጩ በሆነ መልኩ ክፉኛ በማሰቃየት ለአካል ጉዳት እና ለስነልቦና መዘባረቅ ሲዳርግ ተመልክተናል፡፡

የኢሓዴግ መንግስት  ለስሙ የአራት አውራ ፓርቲዎች ጥምረት ተብሎ ቢጠራም ሀገሪቱንም ሆነ ፓርተጊዎቹን የጡት አባት ሆኖ እንዳሻው ሲዘውር የነበረው ህውሓት ነበር፡፡ለዚህም ነበር የኢሓዴግ መንግስት ከማለት ይልቅ የህውሓት መንግስት ሲባል የሚደመጠው፡፡ የህውሓት መንግስት ባሳለፋቸው 27 ዓመታት በሙሉ ለስልጣኑ መቀጠል አጠራጣሪ ናቸው …ያላቸውን የገዛ ወንድሞቹን …የበረሃ ጓዶቹን ሁሉ ከመብላት ወዳ ኃላ ብሎ አያውቅም ለዚህም እንደ ዋነኛ እማኝ ሃየሎም አርዓያን ማንሳት ከበቂ በላይ ነው፡፡ህውሓት አውራ ከሚባሉ አጋር ድርጅቶች ውስጥ እንኳን እንደ ፓርቲ የሚነቅፉት ግለሰቦች ቢኖሩ እንኳ እነሱንም ታምራዊ በሆነ የፖለቲካ አሻጥር ጠልፎ ሲጥላቸው ይስተዋላል፡

የህውሓት መንግስት ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ መልኩ በኦሮማራ ጥብቅ ጥምረት ከሰልጣ ከተወገደ በኃላ ወደ ስልጣን የመጡት ዶ/ር ዓብይ ከሕዝቡ ያገኙት ድጋፍ እና አድናቆት እጅጉን አስገራሚ ነበር፡፡ ዶ/ሩ ገና ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ሀገር ያሻግራል ትውልድ ይቀይራል ያሉነትን መደመር የተሰኘ ፍልስፈና ይዘው መጡ  …መደመር መልካም ነገሮችን መደመር፣እርኩስ ምግባሮችን መቀነሥ ከሆነ የጠ/ ዶክተር አብይየመደመርፍልሥፍና ለማደግ፣ለመለወጥ እና ለመበልፀግ የሚፈልግ፣ግለሰብ፣ቡድን እና በአጠቃላይም የብልፅግና ጥማት ያላቸው ሁሉ፣ሃሳቡን በብርቱ ይፈልጉታል።በዚህ ብርቱ  ፍላጎታቸውም  መሠለኝ ፣ይህ የመደመር ሃሳብ ከጠ/ሚሩ እንደቀረበ ጥቂት
የማይባሉ ዜጎች  ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ተደምሬያለሁ በማለት ሃሳባቸውን በከፍተኛ የሀገር መውደድ ሥሜት የገለፁት።መቼም ጠቅላይ ሚኒሰትር  አብይ ከሁለት ዓመት በፊት ወደሥልጣን እንደመጡ የነበረውን ድጋፍ፣አድናቆትና ሙገሳ
አይረሱትም። እንዴት ይረሳል?የመደመርን ሃሳብ ከቅንነት፣ከመልካምነት፣ከእድገት ከብልፅግና  እና ኢትዮጵያን እንጂ ግለሰቦችን ካለማንገሥአኳያ አይተው ነው ዜጎች እንደ አንድ ሰው በማሰብ ያኔ ግልብጥ ብለው በመውጣት፣ከጫፍ እስከ ጫፍ እኔም
ተደምሬለሁ !በማለት  የጠ/ / አብይን  ሥም በሥሜት ተሟልተው ደጋግመው በመጥራት ለዓላማቸው ሥኬት ከጎናቸው እንደሚቆሙ ዜጎች ያረጋጉጡት።

ምንም እንኳ የዶ/ር ዓብይ መንግስት በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ቢያገኘም ውሎ ሲያድር ግና አኩራፊ አካለት መገዳደል ወደተባል የቀይ መስመር ጨዋት የገቡት ሳይውሉ ሳያድሩ ነበር፡፡ ዶ/ሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በአደባበይ ከተሞከረባቸው የሰኔ 16 የግድያ ሙከራ መለስ ያልተሰሙ ያልተነገሩ ብዙ የግድያ ሙከራዎች እንደተሞከሩባቸው ውስጥ አዋቂዎች ያመላክታሉ፡፡ 

ለዛሬ የዶ/ር ዓብይ መንግስት ያለፋቸውን ያልተነገሩ ብዙ ሺ አሻጥሮችን እና ግድያዎችን ለጊዜው ወደ ጎን አድርገን ለዛሬ ግን ከሶስቱ ሰኔዎች የግድያ ሙከራ ጀርባ ማን እንዴት ሊያደረገው ቻለ የሚለውን መላ ምታዊ አንደምታችንን አንቃኝ፡፡

መላ ምት አንድ የህውሓት እጅ

የህውሓት ሰዎች ከማዕከላዊው መንግስት ተገፍተው አንድ ቀን እንኳ መለስ ብለው ወዳልተመለከተቱት የገዛ ሕዝባቸው ዘንድ ገብተው ከተሸሸጉ በኃላ ሌት እንቅልፍ ቀን እረፍት አጥተው የተነጠቁትን ስልጣን ለማስመለስ የማይሰቅሉት ኮረሪማ፣የማይጥሉት ደንቃራ የለም፡፡ለዚህም ከሰኔ 15 የቦንብ ውርወራ ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የዶ/ር ዓብይን መንግስት ለማሳጣት በብዙ መልኩ ብጥብጥ ሲፈጥሩ፣ሲያስፈጥሩ፣ሕዝብን ከሕዝብ ሲያጋጩ ፣ሲያፈናቅሉ መታየታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ምንም እንኳ የእስከ ዛሬው የህዉሓት ሰዎች ሙከራ ባይሳካም ቅሉ ዛሬም ቢሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ችግር እና ሁከት በመፍጠር ወደ ቀደመ መንበረ ስልጣናቸው ለመመስ የማያደርጉት ጥረት እና ሙከራ የለም፡፡ዛሬም ከመሸጉበት መቀሌ ሆነው አዳዲስ የተንኮል እና የሴራ ስትራቴጂካዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን በተመለከተ ሲዶልቱ ውለው ሲዶልቱ እንደሚያድሩ እሙን ነው፡፡

ከዚህ አንፃር የሰሞኑ የአጫሉ ሁንዴሳን የግድ ሴራ እነሱ ሊያደርጉት ይችላሉ ከሚያስብሉ አንኳር  አንኳር ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ባልታቀደ እና ባልታሰበ መልኩ ሕብረት ፈጥሮ ጉድ የሰራቸውን የኦሮማራ ጥምረት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በመበጣጠስ አጋርነታቸውን ማፈራረስ እና ጉልበታቸውን ማዳከም  ነው፡፡ለዚህ ዕቅዳቸው መሳከታ ደግሞ አርቲስቱ በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ቴሌቪዥን  የሰጠው ቃለ መጠይቅ ለክፉ ውጥናቸው መሳካት መሪም ማላከኪያ ምክንያትም ሆኗቸዋል፡፡

ሀጫሉ በቃለ መጠይቁ እነዚህን እርጅናም ጥላቻም የተጫናቸውን የህውሓት ሰዎች እና ትላንት ከትላንት ወዲያ በህውሓት የጠገቡ ገራፊዎች የፊጢኝ ታስረው ሲገፉ፣ጥፍራቸው ሲነቀል፣የሃይላንድ ውሃ ሲንጠለጠልባቸው እና ሲኮለሹ ከርመው ዛሬ ምንም እንዳልተፈጠረ አድረገው ለሆዳቸው በማደር ሄደው ስራቸው በመወሸቅ አብረው እየሰሩ ምንም አላደረጉንም ነበር በማለት በየሚዲያው የሚተረተሩትን የኦሮሞ ሊቃውንት ነን ባዮችን እና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ከፍ ዝቅ አድርጎ መንቀፉ በሁለቱም ወገን ጥርስ ሊያስነክስበት ችሏል፡፡

ሌኛው እና ዋነኛው ደግሞ አጤ ምኒሊክን በተመለከተ የሰጠው አስተያየት የህውሓት ሰዎች የኦሮማራን ጥምረት ለማፈራረስ ሲጠብቁት ለነበረው አጋጣሚ ጥሩ ጊዜ እና ጥሩ መገጣጠም ሆኖላቸዋል ማለት ይቻላል፡፡የተገኘውን አጋጣሚ የበለጠ ወደመጠቀም ከመግባታቸው በፊት በመጀመሪ ደረጃ ነገርየውን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት በማረገብ በሁሉቱ አካላት ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻን እና ቅራኔን መፍጥረ ከግድያው በኃላ ወደ እነሱ የሚቀሰረውን ጣት ቁጥር እንደሚቀንሰው አውበዋል፡፡ለዚህ ደግም በየቦታው በታትነው ዳጎስ ያለ ክፍያ እየከፈሉ ያሰማሯቸው ዲጂታል ወያኔ የተሰኙ የማህበራዊ ድህረ ገፅ አሸባሪዎቻው አማካኝነት አንድም እንደ ኦሮሞ አንድም እንደ አማራ በመሆን…የሚኒሊክ ሐውልት ይፍረስ…በሚሉና በሌሎች አስከፊ እና ጠያፍ ቃላትን በመጠቀም ነገርየውን በማጦዝ ሰማይ አደረሱት ብሎ መገመትም ይቻላል፡፡

 መላምት ሁለት ጃዋር እና አንጃዎቹ

ከግራኝ አህመድ በኃላ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተፅኖ ፈጣሪ  እና ፍፁም የፖለቲካ ምሁር እንደሆ አድርጎ የሚናገረው አቶ ጃዋር ሞሐመድ ከዚህ ቀደም ተራ የኦሮሞ ጽንፈኛ ወይንም ቅድሚያ ለኦሮሞ/ኦሮሞ ፈርስት/ የሚል አክቲቪስት ከመሆን የዘለለ ሌላ ምንም ዓይት የስልጣን ፍላጎት እንደሌለው ሲናገር ከቆየ በኃላ ያቺ ተከብቤያለሁ ብሎ የብዙ ንፅሁንን ዜጎች ሕይወት ካስቀጠፈባት ቀን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመግባት ማሰቡን ተናግሯል፡፡ ከዚህ በኃላ  ነው እንግዲህ የዶ/ር ዓብይን ዙፋን ከሌሎቹ ፖለቲከኞች በተለየ መልኩ በምኞት በቅርብ እርቀት ይመለከታት የጀመረው፡፡

ከዛች ተከብቤያለው ካለባት የሴራ ምሽት ጀምሮ እንደው ዝም ብሎ በግብታዊነትም በጭፍንም አደባባይ የወጡለትን ሀገር ያመሰሉትን ወጣቶች መያዙ ብቻ ስልጣነ መንበሩን እጁ ያስገባለት ይመስል ምርጫው ካልተደረገ ሞቼ እገኛለሁ፣ከመስከረም 30 በኃላ ሁላችንም እኩል ነን ይሉት ፈሊጥ ይዞ ከች አለ፡፡

ታድያ ይህ ባለመሆኑ እንደው ዝም ብለን በመላ ምት ከሆነው እና ሊሆን ከነበረው ነገር ስንነሳ የዘንድሮው ምርጫ በኮቪድ ምክንያት በመራዘሙ የተበሳጨ ይመስላል…ይመስላልም ቢቻ ሳይሆን በደንብ አድርጎ ተበሳጭቷል፡፡ ያለማት ያቀዳት የአራት ኪሎ ወንበር ህልም ሆናበታለች፡፡ስለዚህ ነገሩን ከስሩ አደፍርሶ በድፍርሱ መኃል የሱን ጉሽ ዓላማ ማሳካት አስቦ እጅጉን በተሰላ …በተጠና  መልኩ ሃጫሉን በገዛ ሚዲያው ቅርቃር ውስጥ ሊያስገባው እና ሊያስገድለው ሞክሯል ብለን ብንጠረጥር በሌላ ነገር አንጠረጠርም፡፡

ለዚህም ዋነኛ ማስረጃ አድርገን ብናነሳ..

1 ለምን ባልተለመደ መልኩ ኢንተርቪው እንዲሰጥ ተደረገ

2 ለምን ከኦነግ ሸኔም ሆነ ከሌሎች አካላት የሚደርስበትን ነገር የገለፀበትን ቃለ ምልልስ ተቆረጠ

3  ስልን የምኒሊክ ነገር አፅንኦት ተሰጥቶት አንዲያወራው ተገፋፋ

4 ከአንዳንድ መረጃዎች እንደሚሉት ከሆነ ሃጫሉ ከቃለ መጠይቁ በኃላ የሰጠሁት ኢንተርቪው ከሰው ጋር እያጋጨኝ ነው አውርዱልኝ ብሎ ሲጠይቅ ስለምን እንቢ ተባለ የሚሉት ጥያቄዎች የጥርጣሬያችንን መንገድ ይጠርግልናል፡፡

ስለዚህ ድግመን ስንጠረጥር ጃዋርም ሆነ በቀለ ገርባ ወይም ህዉሓት ጋር ያምቻ ጋብቻ የፈጠሩ ፅንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች በሃጫሉ ቃለ መጠይቅ እጅጉን ተከፍዋል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቀድመው ላሰቡት የብጥብጥ ጠላ ሃጫሉ ወሳኝ ጥንስስ ሆኖ ስላገኙ አጋጣሚውን ተጠቅመው አስገደሉት፡፡ ካስገደሉም በኃላ  ቀብሩ አዲስ አበባ እንዲሆን ተነጋረው ወስነዋል፡፡ ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ሃጫሉን ለመቅበር ከየ ከተማው የሚተመው ቄሮም ይሁን ተከፋይ የነ ጃዋር እና በቀለ ገርባ ጀሌዎች እንደጉድ ወደ አዲስ አበባ ይተማሉ..በዚህ መኃል አዲስ አበባ ከመድረሳቸው በፊት የገቡ መሳሪያዎች፣ገጀራዎቸ፣ሜንጫዎች በነፍስ ወከፍ ይታደላሉ፡፡ የሚመጣውን ሃይል የትኛውም የአዲስ አበባ ሕግ አስከባሪ ሊቆጣጠረው ሰለማይችል በአጫሉ ሁንዴሳ ሰበብ የሚኒሊክ ሃውልት ይፈርሳል …አዲስ አበቤው ደግሞ ለምን በሚል ይነሳል ..ቀሪው ቄሮ ደግሞ ወደ አራት ኪሎ ይተማል ..አዲስ አበባ ትበጠበጣለች  ያኔ ሄሉ ነገር እንዳልነበር ይሆንና፡፡ 

እዚህ ጋር ሌላ መላ ምት እንሰንቅር …

የግብፅ ረጅም እጅ

ከላይ የተነሱ መላ ምቶች ሊሆኑ ባይችሉ እንኳ በሌላ ይሆናል ሊሆን የሚችለው ይህ መላ ምት ነው፡፡ከዚህ ቀደም ጃዋርም ሆነ ኦነግ ከግብፅ ጋር የህውሓትን መንግስት ለመጣል አብረው ለመስራ የተስማሙበትን አንድ መድረክ ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ምናልባት ከዶ/ር ዓብይ መምጣት በኃላ ሁሉ በር ክፍት ሆኖ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ያ ውላቸው ተቋረጠ ሊባል ይችል ይሆል፡፡ ምንም ያህል ውላቸው ቢቋረጥ ዛሬ ሰማንያቸውን ሊያድሱበት የሚያስችላቸው ኮመን ኢነተረስት /የጋራ ጥቅም/ስላላቸው በምንም ተዓምር …የቱም ሀገር ፈርሶ …ምኑም ያህል ሰው አልቆም ቢሆን እንኳን  ጥቅሜ ያሉትን ከማስከበር ወደ ኃላ አይሉም፡፡

እዚህ ጋር ህዉሓትንም ከግብፅ ጋር መጠርጠሩ ምንም አጥያት የለውም

ጃወርም ሆነ ኦነግ  ምናልበትም ህውሓት እራሷ..የአብይን መንግስት መገርሰስ ይፈልጋሉ

 ግብፅ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ሀገር ታምሶ …ኑሮ ተቃውሶ ውሃው ሳይሞላ የግድቡ ነገር እንዲታጎል ትሻለች፡፡ ለዚህም ለጃዋርም ሆነ ለኦነግ ምናልባትም ለህውሃት ዳጎስ ያለ የስራ ማስኬጂያ ብር እየለገሰች  ሀገር ማመሷን ..ሕዝቡን ማተራመሷን ከፍላበታለች ብለን ልናስብ እንችላለን፡፡

ምንም እንኳን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሃጫሉ ገዳይ ኦነግ ሸኔ ነው ብሎ መግለጫ ቢሰጥም …የተባለው እነውነት ቢሆንም ኦነግ ሸኔ ብቻውን ይኔን አደረገው ወይ ብለ መጠርጠር ይቻላል እና ነው፡፡ ምክንያቱም ህዉሓት ኦነግ ሸኔን እያሰለጠነች እና እያስታጠቀች ስለመሆኑ መስማት ከጀማመርን ሰንበትበት ብለናል እና ነው፡፡

መለስ ብለን ደግሞ ሌላ ጥያወቄ እናንሳ

ጥያቄ አንድ

ጃዋር ከቤተሰብ ፈቃድ ውጪ አስክሬን አስመልሶ ወደ ኦሮሚያ ባህል ማዕከል ለምን ለማስወሰድ ሞከረ…በማዕከሉ የነበሩ ከፍተኛ የብልፅግና አመራሮች እንደ ባህር ዳሩ ግድያ ባሉበት ሊጨረሱ እና የዶ/ር ዓብይን ስልጣን ባዶ በማስቀረት መንበሩን ማዳከም ታስቦ ይመስለናል፡፡ በዛውም አዲስ አበባ እንዲቀበር በማድረግ ከላይ የተነሳው ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ከኦነግ ሸኔ ጎን ጃዋር አለ ያስብላል

ጥያቄ ሁለት

እነዛ ሁለቱ በትግረኛ የሚነጋገሩት ሰዎች እነማን ናቸው …እንዴት ሚስጥሮቻቸውን በትግረኛ ሊናገሩ ቻሉ ሌላው ጥያቄ ነው፡፡ በርግጥ በትግረኛ መነጋገራቸው ሆን ተብሎ ምናልባት ህውሓት እጇ የለበትም ተብሎ  እንዳይታሰብ የተደረገ ነገርም ሊሆን ይችላል፡፡ከግድያው ሴራ ጎን ለጎን አስገዳይ ወይ መልማይ የተባሉት እነዛ ሁለት ግለሰቦች በኦሮሚኛም አትግረኛም የመናገራቸው ነገር ጠለቅ ያለ ሌላ ሴራ አለው፡፡

በጥቅሉ ወይ በደምሳሳው ተመልክተን የነገር ክር ስንመዝ …የመዘዝነውን ደግሞ ደግመን ስንጠቀልለው አንዳች ምስል ይሰጠናል

የህዉሓት ሸኔን ማሰልጠን

የሸኔ ገዳይነት

የመልማዮች ትግረኛ እና ኦሮሚኛ ተናጋሪነት

የኦ ኤም ኤን ሆን ብሎ ሃጫሉን  ወጥመድ ውስጥ ማስገባት 

የጃዋር እና የበቀላ ገርባ አስክሬን ለማስመለስ መሞከር

የኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተሰብሮ በግድ መገባት

የበቀለ ገርባ በተይዘናል ቄሮቸን ለአመፅ ማነሳሳተ 

የበግብጽ ውሃው እንዳይሞላ በአሻጥር የተሞላ እንቅስቃሴ

ይህ ሁሉ ነገር ሲታይ ሲመረመር …ሲመዘን 

ህዉሓት፣ኦነግ ሸኔ፣ጃዋር እና በቀሌ በግብፅ ዳጋሽነት በዕቡ ድብቅ ጋበቻ ሳይፈፅሙ እንዳልቀሩ የሚያመላክቱ ነገሮች ናቸው፡፡

ሃሴቤን አልቋጨሁም…በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ

እስከዛው ግና ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቿን ይጠብቅ!!

Filed in: Amharic