>
5:13 pm - Sunday April 19, 7665

የዘር ፍጅቱን "ግጭት" ብሎ የተፈጸመውን አለማቀፋዊ ወንጀል እንዳልተፈጠረ ከሚክድ አካል ፍትህን መጠበቅ አይቻልም!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የዘር ፍጅቱን “ግጭት” ብሎ የተፈጸመውን አለማቀፋዊ ወንጀል እንዳልተፈጠረ ከሚክድ አካል ፍትህን መጠበቅ አይቻልም!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ በሻሽመኔ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሐረርጌና በዝዋይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ተድበስብሶ እንዲታለፍና ዓለም እንዳያውቀው ታትረው በመስራት ላይ ይገኛሉ። የዘር ፍጅት ፈጻሚዎች ሩዋንዳ እንደተደረገው መታወቂያ እየጠየቁና አስቀድመው ባዘጋጁት የስም ዝርዝር መሰረት የዘር ማጥፋቱን ያካሄዱ መሆኑ እየታወቀ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ  ግን  የዘር ፍጅቱን  ግጭት  አድርገው እያስወሩት ይገኛሉ። የዘር ፍጅቱን ግጭት ብሎ የተፈጸመውን አለማቀፋዊ ወንጀል እንዳልተፈጠረ  ከሚሰራ አገዛዝ  ለግፉዓንና ለሰለባዎቹ ፍትሕ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ  ይህን የሚያደርጉበት ዋናው ምክንያት  ከላይ እስከ ታች ድረስ ያሉት አመራሮች  በሙሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዘር ማጥፋቱ   ተካፋይ ስለሆኑ  ራሳቸውን ከፍርድ ለማሸሽ  ነው።  በዚህ ሴራ ምክንያት  ዘግናኙ ፍጅትና የዘር ማጥፋት ተድበሶብሶ ከታለፈ ሕዝባችን  እየተካሄደ ካለው የዘፍ ፍጅት  የከፋ እልቂት ወደፊት እንደሚጠብቀው ለመናገር ጠንቋይ መቀለብ አይጠይቅም። በመሆኑም በተለይ በውጭ አገር ያለው የሚጣላ ኅሊና ያለው ወገን ሁሉ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ  ተድበስብሶ እንዲታለፍ እያደረጉት ያለውን ፍጅትና የዘር ማጥፋት አለም እንዲያውቀው፤ ከላይ እስከ ታች ያሉ ተጠያቂወች በሙሉ እንዲያዙና ለወንጀላቸው ተመጣጣኝ  የሆነ ፍርድ እንዲሰጣቸው  በመታገል  ወገናዊ  ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።

*     *    *
 በአማራ ላይ የዘር ፍጅት እንዲካሄድ  በኢትዮጵያ ምድር የሲኦል በር በርግዶ የከፈተው ትውልድ አካል የሆነው ግዛው ለገሰ ዛሬ እንኳን በዐይኑ የሚያየውን በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ዐቢይ አሕመድን ስለሚያስቆጣበት ማመንና ማየት  አይፈልግም።
አጥኝዎቹ እንደሚሉት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቁት ፈጻሚዎቹ ብቻ ሳይሆኑ  እንደ ግዛው  ለገሰ አይነት  ወንጀሉን የሚክዱና የሚሸፍኑ አድር ባይና ሆዳም ምሁራን ጭምር ናቸው❗️
እስቲ የዘር ማጥፋት ወይንም Genocideን አለማቀፋዊና አሕጉራዊ ፍቺውን ትተን ዐቢይ አሕመድ ራሱ ለማስከበር በቃለ መሐላ የተቀበለው የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ በምን አኳኋን እንደተቀመጠ እንመልከት። የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 269 ስለ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ምንነት የተብራሩ ዝርዝሮችን አካቷል። አንቀጹን እንደሚከተለው ነው፤
አንቀጽ 269፡ የዘር ማጥፋት፤
ማንም ሰው በሰላምም ሆነ በጦርነት ጊዜ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጎሳ፣ በዘር፣ በዜግነት፣ በቀለም፣ በኃይማኖት ወይንም በፖለቲካ አንድ የሆነን ቡድን በመላ ወይንም በከፊል ለማጥፋት ማሰብ፣ የጥፋቱን ድርጊት ማደራጀት፣ ትዕዛዝ መስጠት ወይንም ድርጊቱን የመፈጸመ እንደሆነ፤ ወይንም
ሀ) በማንኛውም ሁኔታ የማህበረሰቡን አባሎች የገደለ፣ አካላዊ ወይንም የአካል ጉዳት ያደረሰ ወይንም ያጠፋ እንደሆነ፤ ወይንም
ለ) የማህበረሰቡ አባላት በዘር እንዳይራቡ ወይንም በሕይወት እንዳይኖሩ ለማድረግ ማንኛውንም ዘዴ በስራ ላይ ያዋለ እንደሆነ፤
ሐ) የማህበረሰቡን አባላት ወይንም ህጻናት በግዴታ ከስፍራ ወደ ስፍራ ያዛወረ ወይንም የበተነ ወይንም ሊሞቱ ወይንም ሊጠፉ በሚችሉበት የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ያደረገ እደሆነ የዘር ማጥፋት ፈጸመ ይባላል።
ከዚህ በተጨማሪ የተሻሻለው  የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 269 የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ሶስት ነገሮች መሟላት እንዳለባቸው በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ አስቀምጦታል።  እነርሱም:-
1) መግደል፣ በሰውነት ላይ ጉዳት ማድረስ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ደግሞ በቡድን አባላት ላይ የስነ ልቦና ጉዳት ማድረስ፣ በማንኛውም መንገድ ወይም ደግሞ ምንም ይሁን ምን ሰውሮ ማጥፋት፣
2) በአባላት ወይም ደግሞ በልጆቻቸው ላይ ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ መኖር እንዳይችሉ ተከታታነት ያለው ቅስቀሳ ማድረግ እና ይህንን መከላከል ያለመቻል፣ ወይም ደግሞ፣
3) በግዴታ ማፈናቀል ወይም ደግሞ ሰዎችን ወይም ልጆቻቸውን ከቦታዎቻቸው ለሞት በሚያበቃ መልኩ ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም መሰወር፣ ወይም ደግሞ ሆን ተብሎ በጅምላ ወይም በከፊል ብሄርን፣ ብሄረሰብን፣ ጎሳን፣ ዘርን፣ ዜግነትን፣ ቀለምን፣ ኃማኖትን ወይም ደግሞ የፖለቲካ ቡድንን ማጥፋት።
አቶ ግዛው ዐቢይ አሕመድ ራሱ ለማስከበር በቃለ መሐላ በተቀበለው የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ ስለ ዘር ማጥፋት የተጠቀሱት ሁሉ በአማራ ላይ አልተፈጸሙምን? እስቲ ንገረን❗️
Filed in: Amharic