>

አብይ ጉንዳናቸው...!!! (በእውቀቱ ስዩም)

አብይ ጉንዳናቸው…!!!

በእውቀቱ ስዩም

“…ጠቅላያችን አንድ ሚሊዮን ጉንዳን ተሸክሜ ነው ያለሁት…” ሲሉ ሰማሁልበል? ለመሆኑ አንድ ሚሊዮን ጉንዳን ስንት ኪሎ ይመዝናል?…
ብቻ አያድርስ ብዬ ልለፈውና …
ከሁለት አመት በፊት” በሰላም  አውለኝ “ የሚል ጥቅስ ግንባሩ ላይ የለጠፈ የህዝብ አውቶብስ አቃጥሎ ፤ በፖሊስ ተይዞ” ለምን እንዲህ አደረግህ ሲባል” ሰላም ባስ” መስሎኝ ነው” ያለው ጎረምሳ  አሁን የወያኔንና  እና የወነግን ባንዲራ  ደርቦ ይዞ  ፎቶ ሲነሳ ታየዋለህ!
 “ገብቶት ነው ? አውቆት ነው? በድለነው ነው?” አለ መንግስቱ ‘ማረ ፋከ ‘ ሃይለማርያም!
ኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰው ግድያና ውድመት በጥፍራም  ብሄርተኝነት ጦስ ምክንያት  የመጣ ቢሆንም መንግስትም ከተጠያቂነት አይድንም፤ በቸልታም ሆነ ባቅመቢስነት የህዝቡን ደህንነት የማስጠበቅ አቅም እንደሌለው ተባኖበታል፤አሁን  ደሞ ‘የጨዋ ልጅ ካፈረ በግ ከበረረ አይመለስም ‘ ሆኖበት የከርቸሌ  ዙሩን አክርሮታል!   ለመሆኑ   ቤትሄለም ታፈሰ  ምን አድርጋ ነው የታሰረችው?    በዚህ አካሄድ ኩኩ ሰብስቤንስ መች እንጠብቅ?
ስሙማ ቅድም ዩቲውብ ላይ “ ተቀበል ቁጥር አራት “ የሚለውን ዘፈን ሳዳምጥ ከሁለት አመት በፊት የነበረውን አንጀባችን ትዝ ብሎኝ ሳቅሁ፤
“ደመቀ አገሩ ገዱ ቢቀናቸው
የለማ ሆነና አቢይ ጉዳያቸው “
ይላል ዘፋኙ!
አቤት ! ወግ ወጉንኮ ይዘነው ነበር፤
አሁን ግጥሙን ትንሽ ማስተካከል የሚያስፈልግ ይመስለኛል፤
“ደመቀ አገሩ ገዱ ቢቀናቸው
የለማ ነገር ነው አቢይ ጉንዳናቸው ፤
ለማንኛውም፤
Abiy must go  forward:-)
Filed in: Amharic