>

መንግስታችን ህግና ስርዓትን ማስከበር የማይችል  ደካማና ልፍስፍስ ቢሆንም አገር ለማዳን ሲባል ከጎኑ ልንቆም ይገባል!!! (አህመዲን ሱሌይማን)

መንግስታችን ህግና ስርዓትን ማስከበር የማይችል  ደካማና ልፍስፍስ ቢሆንም አገር ለማዳን ሲባል ከጎኑ ልንቆም ይገባል!!!

አህመዲን ሱሌይማን

ከጋዳፊም፣ ከሳዳምም ከሌሎችም ጋር ቆመዉ የነበሩት ጥቂቶች፣ ዛሬ ሊገቡበት ያለዉን ቅርቃር አርቀዉ ያዩት ነበሩ። ብዙዉ ህዝብ ግን በእንስሳዊ ስሜት ብቻ እንደ መንጋ ሆ እያለ የሚነዳ በመሆኑ፣ እነዛ ጥቂቶች አገሮቻቸዉን በአብዛኛዉ የእንስሳ መንጋ ከመበላት ሊያድኑ አልቻሉም። 
ሶሪያዊ የሆነ አንድ ሰዉ ከአሳድ ጎን በሚቆም ጊዜ እንዴት? ብዬ እራሴን እጠይቅ ነበር። ደግፎት ከጎኑ በመሆን በርታ አይዞህ ሲለዉ ለምን? እላለሁ። አሳድ ጨካኝ አምባገነን መሆኑን ስለማዉቅ ከጎኑ የሚሰለፍ ጤነኛ አይመስለኝም። ነገሩ ለካ ወዲህ ኖሯል። ሌላዉ ሌላዉ ምክኒያቶቻቸዉ እንዳሉ ሆነዉ ከመንግስታቸዉ ጎን የቆሙበት ዋነኛ ምክኒያታቸዉ ሃገራቸዉ እንዳይፈርስባቸዉ በመፍራትና ሊከሰት ያለዉ ቀድሞ ስለታያቸዉ ነበር። ከማላዉቀዉ መለኢካ የማዉቀዉ ሰይጣን ይሻላል በሚል።
ሰይጣኑ ቢያንስ አገሩን አንድ ለማድረግ የሚታትር በመሆኑና እነርሱም አገር አልባ ላለመሆን በመፈለጋቸዉ ነበር ከጎኑ መሆናቸዉ።  ሊከሰት ያለዉ ቀድሞ ስለታያቸዉ ማለት ይቻላል። የሆነዉም የፈሩት ስለነበር።
ከጋዳፊም፣ ከሳዳምም ከሌሎችም ጋር ቆመዉ የነበሩት ጥቂቶች፣ ዛሬ ሊገቡበት ያለዉን ቅርቃር አርቀዉ ያዩት ነበሩ። ብዙዉ ህዝብ ግን በእንስሳዊ ስሜት ብቻ እንደ መንጋ ሆ እያለ የሚነዳ በመሆኑ፣ እነዛ ጥቂቶች አገሮቻቸዉን በአብዛኛዉ የእንስሳ መንጋ ከመበላት ሊያድኑ አልቻሉም።
ብዙዉዎች ሃገራቸዉ በሀይማኖትና በፖለቲካ ሽፋን በተደራጁ አዉሬዎች ፈራርሶ እንዲህ ሊሆን እንደሚችል መጀመሪያዉኑ ሲመከሩ በጥሞና በሰሙና፣ ነገሩን በሰከነ አእምሮ ተረድተዉት በነበረ ኖሮ፣ የፈለገዉ መስዋዕትነት ተከፍሎም ቢሆን ከመንግስታቶቻቸዉ ጎን ቆመዉ አገራቸዉን ባዳኑ ነበር። ቢያንስ ዛሬ ዞሮ መግቢያ ነበራቸዉ። የማንም መሳቂያ በመሆን ከነልጆቻቸዉ ከአገራቸዉ እርቀዉ በሰዉ አገር ጎዳና ለማኝ አይሆኑም ነበር።
ምን ለማለት ነዉ፣ በአገር ቀልድ የለም። በኢትዮጲያ ቀልድ የለም ለማለት ያህል ነዉ።
ሁሉም ነገር በአገር ነዉ። አገር ሲኖር ነዉ። ዛሬ ብዙ ሶሪያዊያን ይሄ ሁሉ እንደሚሆን ብናዉቅ እኮ፣ ከመንግስታችን ጎን በቆምን ነበር ብለዉ እንደሚፀፀቱ ጥርጥር የለዉም። ዉጤቱን አዩታ። ምን ያረጋል ታዲያ ለቅሶ፣ ፀፀትና ቁጭት ብቻ።
ስለዚህ ኢትዮጲያን ከአፍራሽ ኋይሎች ለመታደግ በሚደረግ ማንኛዉም ጥረት ዉስጥ፣ አገርን አንድ አድርጎ ለመቀጠል እስከተጓዘ ድረስ ምንም ያህል ጨቋኝ ነዉ ብዬ ባስብም እንኳ፣ ከመንግስታችን ጎን በተጠንቀቅ እንደምቆም በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ።
ከአገር የሚበልጥ የለም።
በሀይማኖትህና በጎጥህ በተለይ አብዛኞቹን ሀገራቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍርስራሻቸዉን ያወጡት አክራሪዎች ከመሆናቸዉ አንፃር በሀይማኖትህ ተጀቡነህ ና፣ አላማህ ኢትዮጲያ ጠል ሆኖ ህዝብና ህዝብን በማባላት ሃገር ለመበተን እንጂ ለመታደግ ያላለመ እስከሆነ ድረስ፣ እስከ መጨረሻዉ ከመንግስት ጎን እቆማለሁ።
መንግስታችን ህግና ስርዓትን ማስከበር የማይችል አንዳንዴም ለገዳዮች ገጀራ የሚያቀብል ደካማና ልፍስፍስ ቢሆንም፣ መንግስት መንግስት ነዉና ሌላ አማራጭ በሌለበት ከጎኑ መቆም ግድ ይላል። ሌላኛዉ ወገን ሰዉን እንደ ከብት አጋድሞ የሚያርድ በመሆኑ፣ አገር አስተዳድራለሁ ብሎ በወንበር የተቀመጠ ተፃራሪዉ አካል ለአገር መቀጠል የበለጠ ነዉ።
ለኢትዮጲያችን ሁላችንም እንደየ እምነቶቻችን ዱአ እናድርግ።
Filed in: Amharic