>

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለሀምሌ 11 ተቀጠሩ (የአማራ ሚዲያ ማእከል)

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለሀምሌ 11 ተቀጠሩ

የአማራ ሚዲያ ማእከል

– “ምግብ እና ልብስ እንዳይገባላቸው ጠያቂም እንዳያያቸው ተከልብለዋል”
ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ 
የኦፌኮ አመራሮችን ሰው እንደሚጠይቃቸው እና ምንም አይነት ገደብ እንደሌለባቸው የሚታወቅ ነው
ዛሬ ሀምሌ 1 ቀን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኢ/ር ይልቃልን ሂደው እንደጎበኟቸው አቶ አዲሱ ለአማራ ሚዲያ ማእከል ገለጹ።
3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን) የታሰሩት ኢ/ር ይልቃል ፍርድ ቤት ቀርበው “በአዲስ አበባ ለተነሳው ሁከት እና ግርግር ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሁነሀል ” በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው ለሀምሌ 11 ቀን እንደተቀጠሩ ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ከዶ/ር ዳንኤል በቀለ መስማታቸውን ገልጸዋል።
ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው መከልከላቸውን እና ምግብም ሆነ ቅያሪ ልብስ ስላልገባላቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ሊጠይቋቸው ሲሄዱ አይቻልም እንደሚሏቸው እና አንዳንዴ ደግሞ እዚህ የለም እንደሚሏቸው የገለጹት ጠበቃ አዲሱ በደንበኛቸው የተፈጸመው  የመብት ጥሰት አሳሳቢ ነው ብለዋል።
የኦፌኮ አመራሮችን ሰው እንደሚጠይቃቸው እና ገደብ እንደሌለባቸው የሚታወቅ ሲሆን በአንጻሩ የኢሀን ሊቀመንበር በሆኑት በኢ/ር ይልቃል ጌትነት ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል።
****
ኢንጂናር ይልቃል  ለአመነበት  አቋሙ ለህዝብ ያለውን ወንድማዊ ስሜት እውቀቱን በእውነት አስመርኩዞ  መንግስት ስሞግት  የኖረ  ሰው ነው  ። ትናንትም ዛሬም ስለ ኢንጂናር ይልቃል ማንናት ልታድበሰብሰው አትችልም ።
ባሳለፊናቸው ሁለት አመታቶች አቅጣጫቸውን ቀይረው በአማራና አማራን ትመስላላችው በተባሉ ንጽሐን ግለሰቦች የሚደረግ ዘር ተኮር ጥቃት  መንግስት እድያስቆም አበክሮ በአደባባይ ይናገር ነበር ።
መንግስት  ኃላፊናቱን  በመወጣት ፈንታ ወንጀለኛችን በማበረታታት ለግለሰቦች ጠባቂ በመቀጠር ሰው የገደለን ንብረት ያወደመን በአደባባይ ለተበዳዩ ህዝብ ስልጣን ሰቶ ሾመው  ! በቀል ገነነ !  በአደባባይ የሰው ልጅ በማናቱ  በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ ።
ዛሬ ኦሮሞያ ክልል 800ያለናሱ  አማራና ዘረ አማራ  የተባሉ ግለሰቦች  ጀዋር  እውቅና በሰጣቸው ቄሮዎች   በአደባባይ  በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል  ንብረት ወድሟል ተዘርፏል ።
ታድያ ለዝህ መጠየቅ ያለበት አብይ ወይስ ኢንጂናር ይልቃል ?
NB አዲስ አበባ በፈለጉት ልክ መጠና ሰፊ ጥቃት ስላላደረሱ  አብይን ይተቹ ኛል ያላቸውን ሁሉ እየለቀመ ከመብላት ወደ ኃላ አይልም ።
Filed in: Amharic